Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንባር፣ ክርና የመሳሰሉ ነገሮችን ማጥለቅ

'‎አንባር፣ ክርና የመሳሰሉ ነገሮችን ማጥለቅ

ዓረቦች ከኢስልምና በፊት በነበረው የድንቁርና ዘመን ክፋትን ለመመከት፣ መልካምን ለማግኘት ወይም ከቡዳ ለመጠበቅ ሲሉ አንባርና የመሳሰሉትን ነገሮች ያደርጉት ነበር፡፡ 

  አላህ እንዲህ ብሏል፡-

وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ  قُلْ أَفَرَأَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ إِنْ أَرَادَنِيَ اللَّهُ بِضُرٍّ هَلْ هُنَّ كَاشِفَاتُ ضُرِّهِ أَوْ أَرَادَنِي بِرَحْمَةٍ هَلْ هُنَّ مُمْسِكَاتُ رَحْمَتِهِ  قُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ  عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ الْمُتَوَكِّلُونَ

«ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን (ጣዖታት) አያችሁን? (ንገሩኝ) አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው፡፡ «አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል፡፡ (አል ዙምር 38)

  በሌላም አንቀጽ እንዲህ ይላል፦

قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِهِ فَلَا يَمْلِكُونَ كَشْفَ الضُّرِّ عَنكُمْ وَلَا تَحْوِيلًا 

«እነዚያን ከእርሱ ሌላ (አማልክት) የምትሏቸውን ጥሩ፡፡ ከእናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን (ወደ ሌላም) ማዞርንም አይችሉም» በላቸው፡፡ 
አል ኢስራህ 56

ከዒምራን ኢብኑ ሁሰይን እንደተዘገበው ‹‹ነብዩ   አንድ ሰውዬ እጁ ላይ ከመዳብ የሆነ አንባር አጥልቆ ሲያዩት “ይህ ምንድነው?” ብለው ጠየቁት “ለድካም በሽታ ነው” አላቸው:: እሳቸውም እንዲህ በማለት ወቀሱት “አውልቃት! ድካምን እንጂ አትጨምርልህም። እጅህ ላይ እያለች ከሞትክ አትድንም፡፡›› 
አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል

ከሁዘይፋ ኢብኑል የማን እንደተዘገበው ‹‹አንድን ሰው በመታመሙ እጁ ላይ ክር አስሮ አየውና ከበጠሰበት በኋላ ይህን አንቀጽ አነበበ፦

وَمَا يُؤْمِنُ أَكْثَرُهُم بِاللَّهِ إِلَّا وَهُم مُّشْرِكُونَ 

‹‹አብዛኞቻቸውም፤ እነሱ አጋሪዎች ኾነው እንጂ በአላህ አያምኑም፡፡›› (ዩሱፍ 1ዐ6)

√ ሸሪዓዊ ብይኑ፤
አንባር፣ ክርና የመሳሰሉትን ማጥለቅ ሸሪዓዊ ድንጋጌው ሀራም (ክልክል) ነው። 

ይህንን ሲያደርግ በራሱ ያለ አላህ ፈቃድ ተፅእኖ ያሳድራል የሚል እምነት ካለው ከአላህ ውጭ አስተናባሪ ጌታ አለ ማለቱ በመሆኑ በአላህ ጌትነት ላይ ትልቁን ሽርክ  አጋርቷል ማለት ነው::

ነገሮች ሁሉ በአላህ እጅ እንደሆኑና ያጠለቀው ነገር ግን ለፈውስ ምክንያት ብቻ እንደሆነ ቢያምን ደግሞ ትንሹን ሽርክ ፈፅሟል፡፡ ምክንያቱም ሰበብ ያልሆነን ነገር እንደሰበብ ቆጥሮ በልቡና በስራውም ከአላህ ሌላ ወደሆነ አካል ዞሯል፡፡ ይህ ደግሞ ወደ ትልቁ ሽርክ ለመሸጋገር በር የሚከፍት ነው፡፡

ሸይኽ ኡሰይሚን እንዲህ ብለዋል፤

«وما لم يثبت كونه سببا شرعيا ولا حسيا لم يجز أن يجعل سببا ، فإن جعله سببا نوع من منازعة الله تعالى في ملكه وإشراك حيث شارك الله تعالى في وضع الأسباب لمسبباتها» مجموع الفتاوى 1/144

« ሸሪዓዊ ወይም ተጨባጭ የፈውስ ምክኒያት ያልሆነን ነገር ለፈውስ ምክኒያት አድርጎ መቁጠር አይፈቀድም። የፈውስ ምክኒያት አድርጎ መቁጠር የአላህን ስልጣን መቀናቀንና ማጋራትም ይሆናል።»

«وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِين»ِ  الشعراء ٨٠

«በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡» ሹዓራዕ 80

http://www.facebook.com/emnetihintebiq‎'

http://www.facebook.com/emnetihintebiq