Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰካራም “ምሁሮች” gtm


ሰካራም “ምሁሮች”
ማንነቱን ረስቶ
እርሱነቱን ከድቶ
ክብሩን አንኮታኩቶ
ማይንዱን አሻግቶ
ከነቻቺ ሰፈር ከቀለጠው መንደር
ወረደ ሊጨፍር ገባ ሲንደረደር
ከወደራስ ቅሉ ለላይኛው በኩል በያዘው ብርጭቆ
ባዶነትን ገዝቶ ባዶነት ገልብጦ ባዶነትን ሰርቆ
ሠብአዊ ክብሩን በርካሽ አራግፎ ቸብችቦ አስረክቦ
መርገምት ውርደት ርክሰት ይሻለኛል ብሎ በራሱ ቀንጥቦ
ልክ እንደ ብርጭቆው ከወደታች ሰፍቶ ከወደላይ ጠቦ
ቅንነት ተርቦ
አሳብ አጥቶ ኖሮ ክፋትን አስቦ
ተንኮልን አንግቦ
በብርጭቆው ስፋት እራሱን አግቶ አድማሱን ገድቦ
ተግቶ ተግቶ ምላሱ ተሳስሮ መጭመቂያ ጋን ሆኖ
ጭራቅ አውሬነቱ ከፊቱ እየታየ ማንነቱ ገንኖ
“ኡሁ” ሲል አንድ ጋን፣ ሲያነጥስ ሌላ ጋን
ከተናገረማ ጭራሽ አደረገው አገሩን ጋን በጋን
“ኡሁ! አሁ! ኡሁ!” ተበከለ አየሩ
“ህው” አለ አትሞስፈሩ
“ኢኮው” አስተጋባ “ኡሁ” አለ ሰፈሩ
ተጨነቀ ምድሩ፡፡
በደቂቃዎች ጋፕ አክሮባት ሰራና ወጥቶ ወርዶ ዘሎ
በቲቪ መስኮት ላይ ድቅን አለ ድንገት ያገር ሊቅ ተብሎ
ባዶ ማንነቱን በሱፍ በክራቫት በጨርቅ ጠቅልሎ
አቤት!
መድረኩ ሲደላው በግላጭ ሲያገኘው ስንቱን ቀጣጠፈው
የዘመናት ቂሙን ሲያቁር የቆየውን ድንገት ዘረገፈው
ርካሽ አላማውን እኩይ እሳቤውን
ለነገ ሳያስቀር ዘቅዝቆ አራገፈው፡፡
አቤት እንቶ ፈንቶ!
የሐቅ ድርቅ ይዞት እውነት ጋር ተጣልቶ
ከሐሰት ተጋብቶ
በቁም እየቃዠ አጀንዳ ቢስ ሆኖ የሚያወራው አጥቶ
ሒጃብን ከሰሰው ከጭቆና ቀንበር መገለጫ አካትቶ
የወርቋ ወርቅ ልብስ መሆኑን ዘንግቶ
ማፈሪያ አጥቶ ኖሮ አይኑን ግንባር አርጎ ህሊናውን ረስቶ፡፡
የሱ አልበቃ ብሎ ብጣሽ ልባሽ አጥቶ ህሊናው መራቡ
መልበስን ይከሳል ሊያግድም ይፈትላል ያሴራል በህቡ?
ምነውና ታዲያ “የሴቶች መብት” ብሎ ሴትን ማዋከቡ?
ምነውሳ ታዲያ ስለ ክብር አላዝኖ ጂልባብን መስደቡ?


                                                        ኢብኑ ሙነወር