Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለእህቴ! ጥቂት ስለ ሰልፍ




بسم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله
ለእህቴ!
አሙ ከብሸህ የተባለች ሶሐብያህ ረዲየላሁ ዐንሃ ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሙስሊሞች ሰራዊት ጋር ለመውጣት ጠይቃ ይከለክሏታል፡፡ ይህኔ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ እኮ መዋጋት አስቤ አይደለም፡፡ የምፈልገው ቁስለኞቹን ማከም፣ በሽተኞቹን መንከባከብ ነው” አለቻቸው፡፡
እሳቸውም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡-
" لولا أن تكون سنة، يقال: خرجت فلانة! لأذنت لك ولكن اجلسي في بيتك "
“እከሌ ወጣች እየተባለ ምሳሌ ተደርጎ እንዳይያዝ ባልሰጋ ኖሮ እፈቅድልሽ ነበር፡፡ ነገር ግን ከቤትሽ ተቀመጪ!!!” አሏት፡፡
(አስሶሒሐህ፡ 2740)
እርግጠኛ ነኝ ሊጠቀሙብሽ የሚፈልጉት የሰልፍ አርበኞች ይህን ሐዲሥ ብዙ ይጠመዝዙታል፡፡ ጠብቂ፡፡ አጥጋቢ መልስ መያዝሽን ግን በሚገባ አስቢበት፡፡ ነገ መርማሪው ውስጠ-አዋቂው አላህ ነው፡፡ እራስሽን አታዋርጂ፡፡ መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
" لا ينبغي لمؤمن أن يذل نفسه، قالوا: وكيف يذل نفسه؟ قال: يتعرض من
البلاء ما لا يطيق "
“ሙእሚን እራሱን ሊያዋርድ አይገባውም” ማለታቸው ላንቺም ነው፡፡ “እንዴት እራሱን ያዋርዳል” ተብለው ሲጠየቁ “ለማይቋቋመው ፈተና እራሱን ማጋፈጡ ነው” ብለዋል፡፡ (አሰሒሐህ፡ 613)
ያንቺ መውጣትም እራስሽን ከማዋረድሽ ባለፈ ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ “ብልጥ ማለት በሌላው ላይ ከሚደርሰው የሚማር ነው” ይባላል፡፡ እስካሁን ከደረሰብን መማር ካልቻልን ከስረናል ማለት ነው፡፡
ለሰልፍ ቀስቃሾች!!!
በሚደርሰው ሁሉ ከአላህ ፊት እንዳትጠየቁ ከወዲሁ በንፁህ ህሊና፣ በተረጋጋ መንፈስ አስቡበት፡፡ የሰው ህይወት ቢጠፋ፣ አካል ቢጎድል፣ መሳጂድ በከሃዲዎች ቢረከሱ፣ እህቶቻችን ላይ አሳፋሪና ክብርን የሚነኩ ነገሮች ቢፈፀሙ፣ ሌሎችም ኢስላምንም ሙስሊሞችንም የሚጎዳ ወይም የሚያጎድፍ ነገር ቢፈፀም ፈፃሚው ብቻ ሳይሆን የናንተም እጅ እንዳለበት እንዳትዘነጉ፡፡ ይህንን ነብያዊ ሐዲሥ በጥንቃቄ አስተውሉ፡፡ የመልእክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ ሳያከብሩ ለዲን መቆርቆር የለም፡፡ ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፡- “በአንድ ወቅት መንገድ ወጣንና አንዱን ሰው ድንጋይ እራሱን ፈነከተው፡፡ ከዚያም ጁኑብ ሆነና ጓደኞቹን “ተየሙም ማድረግ የምችልበት ፍቃድ” ታገኙልኛላችሁ” ሲል ጠየቀ፡፡ “አይ ውሃ መጠቀም እየቻልክ (ለተየሙም) ፈቃድ አናገኝልህም” አሉት፡፡ በውሃ ታጠበና (ቁስሉ አገርሽቶበት) ሞተ፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ በመጣን ጊዜ ጉዳዩ ሲነገራቸው፡-
قتلوه قتلهم الله ألا سألوا إذا لم يعلموا فإنما شفاء العي السؤال؟
#ገደሉት_አላህ ይግደላቸውና! ካላወቁ አይጠይቁም ነበር? የአለማወቅ መድሃኒቱ መጠየቅ ነው?!” አሉ፡፡ አልባኒ “ሰሒሕ” ብለውታል፡፡ አስተውሉ የተሳሳተ ፈትዋ ሰጥተውት ስለሞተ ነው “ #ገደሉት_አላህ ይግደላቸውና” ያሏቸው፡፡ ዛሬ ግን ሞት፣ ጥፋት፣ ውርደት ወዳለበት ቦታ ነው ሰዎች እየተቀሰቀሱ ያሉት፡፡
ወንድሜ ሆይ እህቴ ሆይ! ምንስ ቢደርስብን እንዴት እንዲህ ይባላል ለዲን አይደል የምንወጣው ጂሃድስ ላይ ስንት ነገር ይደርስ የለ” እንደሚባል እጠብቃለሁ፡፡ ክርክር ማስረዘም አልፈልግም፡፡ ከተቀበልክ ታላላቅ የሱና ዑለማዎች ሰልፍ እንደማይፈቀድ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ላይ የተለየ አቋም ያንፀባረቁት ያለጥርጥር ስሜት የሚጋልባቸው የቢድዐ ጭፍራዎች ብቻ ናቸው፡፡ ደግሞም አስተውል! ጂሃድን ምሳሌ እያደረግክ ጥፋትህን አትጨምር፡፡ በጂሃድ ውስጥ አነሰም በዛም የማሸነፍ እድል አለ፡፡ ለዚያም ነው አልፎ አልፎም ቢሸነፉ ሙስሊሞች ጠላቶቻቸውን ድባቅ እየመቱ የመጡት፡፡ በሰልፍ ውስጥ ግን ማሸነፍ የሚባል ሽታውም የለም፡፡ ያለጥርጥር የምትቃወመው አካል ካላዘነልህ በስተቀር የሚከተለው አደጋ ነው፡፡ ደግሞም ያለነው አፍሪካ መሆኑ አይረሳ፡፡ የህዝብ ጩኸት የቁራ ጩኸት የሆነበት ምድር፡፡ የመብት ጥያቄ በጥይት አረር ምናልባት ከቀለለ በወጠምሾች ዱላ የሚመለስበት ምድር፡፡ እናም እናስተውል፡፡ እስካሁን የደረሰው ይብቃን፡፡ በቁንፅል አስተሳሰብ ላይ ተመርኩዘን፣ በስሜት እየጠየቅን፣ በስሜት እየመለስን፣ በስሜት እየፈረድን እራሳችንን ወገናችንንም ለከፋ አደጋ ባናጋልጥ ጥሩ ነው፡፡ “ዝም ብለን እንመልከት ወይ” አትበለኝ፡፡ ለምን ወደ ከፋው እንሄዳለን ነው ያልኩት፡፡ ዲናችንንም ወገናችንንም የማንም መጫወቻ አናድርገው:: ረጋ ብለን ይህን የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ ንግግር እንመልከት፡፡
وَالْعَجَبُ مِنْ قَوْمٍ أَرَادُوا بِزَعْمِهِمْ نَصْرَ الشَّرْعِ بِعُقُولِهِمْ النَّاقِصَةِ وَأَقْيِسَتِهِمْ الْفَاسِدَةِ . فَكَانَ مَا فَعَلُوهُ مِمَّا جَرَّأَ الْمُلْحِدِينَ أَعْدَاءَ الدِّينِ عَلَيْهِ فَلَا الْإِسْلَامَ نَصَرُوا وَلَا الْأَعْدَاءَ كَسَرُوا
#የሚደንቀው_በሰንካላ_አእምሯቸው_በብልሹ_እይታቸው_ተመረኩዘው_ሸሪዐን_ለመርዳት_የሚሞክሩ_ሰዎች_ሁኔታ ነው፡፡ #የሚሰሩት_ስራ_አፈንጋጭ_የኢስላም_ጠላቶች_በኢስላም_ላይ_እንዲረማመዱ_አድርጓል ፡፡ ኢስላምንም አልረዱ:: ጠላቶቹንም አልረቱ::” (መጅሙዑልፈታዋ፡ 9/253)
ጌታዬ ሆይ! እኔንም ወገኖቼንም ከክፉ ሁሉ ጠብቀን፣ እውነቱንም አሳየን፡፡ በዲናችንም አትፈትነን፡፡ በየትኛውም ቦታ በዲናችንን የሚፈትኑንንም አካላት አንተው ብቃን፡፡ ላንተ የሚሳንህ የለምና፡፡
وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 19/2007)



አድራሻዎቻችን ይቀላቀሉ

ፌስቡክ           ቴሌግራም         ዩቲዩብ