Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሶስት አስገራሚ ጉዳዮች

*** ሶስት አስገራሚ ጉዳዮች ***
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

① «ሀይማኖተኛ» ሆነው ሰበካቸውን በውሸት ላይ የሚገነቡ!

ሀይማኖተኛም ይሁን ሌላ፤ መቼም ሰው ነውና በግል ጉዳዮች አንዳንድ ጊዜ ውሸት ከአንደበቱ ሊያመልጠው ይችላል፤ ግድየለም!

በተደጋጋሚ ሆን ብሎ መሰረት የሌለውን የሀሰት ወሬ ከመቅጠፍ አልፎ በትጋት የሚያሰራጭ «ሀይማኖተኛ» ግን እንደ አሸን ፈልቷል።

በማስረጃ መርታት የተሳናቸውን አካል  «ሊያርዳችሁ ነው»፣ «ሊያጠፋችሁ ነው» ሲሉ ተቀናጅተው ስሙን ያጠፋሉ። የሌላውን እምነት ተከታዮች ለማጠልሸት የውሸት ፎቶም ያቀናብራሉ። (ባሁን ዘመን ማንም ሊለየው የሚችለውን የለማጅ ፎቶሾፕ ስራ ያቀርባሉ።)

ሙሰይለማህ የተባለው በታላቁ ነብያችን ዘመን ነብይነትን የሞገተው ሀሰተኛ ግለሰብ «አላህ ለኔም ያወረደልኝ ምእራፍ አለ» ብሎ ለዐምር ኢብኑ'ል‐ዓስ መነባነቡን ሲያሰማው ዐምር እነዲህ ነበር ያለው፡‐
«በአላህ እምላለሁ፤ እየዋሸህ መሆኑን እኔ እንደማውቅ አንተ በርግጥ ታውቃለህ!»

የሀይማኖት አንዱ መገለጫ እውነተኝነትን ማስተማር አልነበር?! 

ወገን ሆይ! ሀይማኖት የእልህ መወጫ አይደለም! የርካሽ ፖለቲካ መደበቂያም አይሆንም።
—————

② ከላይ የጠቀስኳቸው ቅቤ አንጛቾች በተለያየ አጋጣሚዎች ሀሰታቸው ተጋልጦ ጭምብላቸው ሲወልቅ ያለምንም ሀፍረት መልሰው የበፊቱን ጭምብላቸውን ማጥለቃቸው!

ደግሞ ስለወደፊቱ ሲተነብዩ ጊዜው ሲደርስ ቅጥፈታቸው እንደሚጋለጥ እያወቁ በድፍረት መዘላበዳቸው!

ክስተቱ ካለፈም በኋላ አይናቸውን በጨው አጥበው፣ በለምዳቸውን ተጀቡነው መቆረባቸው!

የእኛ ነብይ እንዲህ ብለዋል፡‐
«ሰዎች ከደረሱበት የመጀመሪያዎቹ ነብያት  ንግግር አንዱ፡‐ "የማታፍር ከሆነ ያሻህን ስራ!"»
—————

③ (ከሁሉም ይበልጥ የሚደንቀው) በውሸትና በስርአት አልበኝነት የታወቀ ግለሰብን በጭፍን የሚደግፈውና ከኋላው የሚጉተለተለው መሃይም ብዛት!
እንደምሳሌ፡‐ የነእንትናን ፖስት ላይክ እና ሼር የሚያደርጉትን ቁጥር ተመልከት!

መቼም ተጣሪ ሁሉ ተከታይ አያጣም።
በእልህና በጎጠኝነት የሚገፋ ጭፍን ተከታይነት ግን የማህበረሰብ ነቀርሳ ነው።

‐ በእኛ መፅሀፍ ላይ ከእውነተኞች ጋር እንድንሆን ታዘናል፡‐

{ يَٰأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَكُونُواْ مَعَ ٱلصَّدِقِينَ }

{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ሁኑ፡፡}

‐ የሌሎቹን ባላወቅም የእኛ መመሪያ ከጭፍን ወገንተኝነትና ለጠላትም ይሁን ፍትህን ከማዛባት ይከለክላል፡‐

{ يَٰأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ كُونُواْ قَوَّمِينَ لِلَّهِ شُهَدَآءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا يَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰٓ أَلَّا تَعۡدِلُواْۚ ٱعۡدِلُواْ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ }

{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በፍትህ መስካሪዎች ሆናችሁ ለአላህ የቆማችሁ ሁኑ!  ሰዎችን መጥላት ፍትህን እንዳትተገብሩ አይገፋፋችሁ፤ ፍትህን ተግብሩ፤ እርሱ ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህ  ስለምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነውና፡፡}

والسلام

#ማህበረቅዱሳን
#ZemedkunBekele
#እዩጩፋ
#ወዘተ

Post a Comment

0 Comments