ከኢቃም ቀድመው ይምጡ
ለሰላት ክብር ይስጡ!
ምንም እንኳ ይህ ሸሪዓዊ ግዴታ ሴቶችን የሚመለከት ባይሆንም ወንድሞቻችሁንና ቤተሰብ አባላትን ታስታውሱበት ዘንድ ጠቃሚ ነው በማለት በዚህ ፔጅ ለቀነዋል። በዚሁ አጋጣሚ ሴቶችም በተለያዩ የቤት ውስጥ ስራዎች በመጠመድ የሰላት ሰአትን ከማሳለፍ ወይም ከማዘግየት መጠንቀቅ ይገባል። ሰላትን በወቅቱ መጀመሪያ ላይ መስገድ ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነው።

عَنْ أُمِّ فَرْوَةَ رضي
الله عنه قَالَتْ : سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ
وَسَلَّمَ : أَيُّ الْأَعْمَالِ أَفْضَلُ ؟ قَالَ : ( الصَّلَاةُ فِي
أَوَّلِ وَقْتِهَا ) ، والحديث صححه الألباني في صحيح أبي داود 426
ኡሙ ፈርዋህ እንዲህ ብላለች፤ «የአላህ መልእክተኛ ከስራዎች ሁሉ በላጩ የትኛው ነው? ተብለው ተጠየቁና "ሰላትን በወቅቱ መጀመሪያ ላይ መስገድ"በማለት መለሱ»
አቡዳውድ የዘገቡት ሱሆን አልባኒም ሰሂህ መሆኑን አረጋግጠዋል።
☞ የጀማአ ሰላት>> ወደ መልእክቱ...
በተለያዩ አሳሳቢ ባልሆኑ ጉዳዮች ተጠምደን ለሰላት አዛን እየሰማን ወደ ጥሪው ቦታ ወዲያው ባለመጓዛችን በርካታ ትሩፋቶችን እናጣለን።
በዚህም ኢቃም ሲደረግ የመንመጣ፣ ሰላት ተጀምሮ የምንደርስ፣ ሊያልቅና ካበቃም በኋላ የምንገኝ ብዙሃን ነን።
መስጅድ በአቅራቢያው እስካለና አዛን እስከተሰማ ድረስ የወንድ ልጅ መስገጃ ስፍራው በጥሪው ቦታ ነው።
ይህንን አስመልክቶ ለሰላተል ጀማዓ ላይ ለተገኙት በርካታ ብስራትንና ማበራታዎችን፣ ላልተገኙት ደግሞ ማስጠንቀቂያዎችን መጥቀስ ይቻላል።
ዋናው ጉዳይ ግን በሰማነውና ባወቅነው ተግባሪ የመሆናችን ችግር እንጂ በዚህ ረገድ የእውቀት ማነስ ባብዛኛው የለም።
عَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ :
( مَنْ سَمِعَ النِّدَاءَ فَلَمْ يَأْتِهِ فَلَا صَلاةَ لَهُ إِلا مِنْ عُذْرٍ ) .
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁም) በተወራልን መሰረት የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ኣሉ።
« የአዛን ጥሪን የሰማና ወደ ጥሪው ቦታ ያልመጣ ዑዝር (ሸሪዓዊ ምክንያት) ካለው ሰው በቀር ሰላት የለውም። »
[ሸሪዓዊ ምክንያት ሲባል: ወደ መስጂድ የማያስኬድ የደህንነት ችግርና በሽታን የመሳሰለ።]
رواه ابن ماجه (793)
صححه الألباني في صحيح الجامع (637) .
______________
አዛንን ሰምተው ስለመገኘት ርቀትን በተመለከተ ሊቃውንት በሰጡት ማብራርያ መሰረት ያለ ማይክሮፎን አዛንን መስማት በሚያስችል ርቀት ላይ ያለ ሰው መስጂድ ተገኝቶ በጀማዓ መስገድ ግዴታ ይሆንበታል።
ሸይኽ ሳሊህ አልዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ላንድ ሰው ከቤቱ እስከ መስጂድ ያለው ርቀት ገደብ ኣለውን ተብለው ለተጠየቁት ሲመልሱ:
« በሸሪዓ የተገደበ ርቀት የለውም። ርቀቱን የሚገድበው በተለምዶ የሚታወቀውና ያለ ድምፅ ማጉሊያ አዛን የሚሰማበት ርቀት መሆኑ ነው።»
"أسئلة الباب المفتوح"
( سؤال رقم 700 ) .
_________________
ለጀማዓ ሰላት ክብር መስጠት ይገባልም። በቸልተኝነትና በስንፍና እንዲሁም ለራሳችን ዑዝር በመስጠት ወደ ኋላ መቅረት ያወቃቅሳል።
ሱፊያን አልሰውሪ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:
قال سفيان الثوري رحمه الله :
”مجيئك إلى الصلاة قبل
الإقامة توقير للصلاة “
فتح الباري لابن رجب 3/533
« ኢቃም ከመደረጉ በፊት ለሰላት (ወደ መስጂድ) መምጣትህ ለሰላት ክብር መስጠትህ ነው። »
ሱፊያን አልሰውሪ: (ረሂመሁላህ)
abufewzan)18Feb15/ 28-04-1436
www.facebook.com/tenbihat