Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር ሲሰግድ አቋቋማቸው እንዴት ይሆናል?

አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር ሲሰግድ አቋቋማቸው እንዴት ይሆናል?
ሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒይ (አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውን ጀነተልፊርደውስ ያድርገውና) ይህንን ጥያቄ ተጠይቀው ሲመልሱ፤
«አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር ሲሰግድ፤ በመካከላቸው የአንድ ሰፍ ርቀት ይኖራል። ማለትም እሱ አዚህ ጋር ከሰገደ አሷ ደግሞ ወደኋላ ራቅ ብላ ሱጁድ ስታደርግ ከርሱ ቅርብ በምትሆንበት ርቀት ላይ ትሰግዳለች እንጂ በአንድ ሰፍ አይሰግዱም። ለዚህም መረጃው ከአነስ የተዘገበው ሰሂህ ሀዲስ ሲሆን «እኔና አንድ ልጅ ከረሱል በስተጀርባ ስንሰግድ አሮጊቷ ከጀርባችን (ሰገደች)» አልሀዲስ
አሮጊቷ የአነስ እናት ነበሩ
نص الإجابة:
يصلي الرجل مع امرأته ، يكون بينهما قدر صف ، يعني هو يصلي ههنا قدام وهي تصلي خلفه إلى حد أن تسجد قريباً منه من بعده ، ولا يصليان صفاً واحداً .
لما جاء من حديث أنس في الصحيح : صليت أنا وغلام خلف رسول الله - صلى الله عليه وعلى آله وسلم - والعجوز خلفنا .
والعجوز هي : أم أنس .