Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ሀይድ ህግጋት ክፍል-8

‎󾭚ስለ ሀይድ ህግጋት 󾭚
               ክፍል-8 

የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልእክት ቁ• 12

የወር አበባሽ ከመፆም ያቅብሻል
~~~~~~~~~~~~~~~~~

# ባሳለፍናቸው ክፍል 6 እና 7 ህግጋት የወር አበባ ላይ ያለች እንስት ዚክር ማድረግን እና ቁርኣን መቅራትን፣ ማድመጥን፣ እንዲሁም ቁርኣንን መንካትን በተመለከተ አላህ ያገራልንን ያህል ላስገነዝባችሁ ተሞክሯል። 

   እነሆም ለዛሬ ሀይድ ላይ ስትሆን ፆምን እንዴት እንደምታስተናግድ የሚያብራራውን መልእክት ያንብቡት። አላህ ባወቅነውም ተጠቃሚዎች ያድርገን።

#ፆምና የወር አበባ

   የወር አበባ ላይ ላለች እንስት የፍላጎትም ይሁን የግዴታ ፆምን መፆም ይከለከላል። ብትፆምም ትክክለኛ አይደለም።

   በወር አበባዋ ወቅት ያለፋትንም እለታት ነፃ በሆነች ግዜ በመፆም ማካካስ ግድ ይሆንባታል።

   ይህም ከምእመናን እናት ከኣዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በተነገረን  መሰረት

لحديث عائشة رضي الله عنها : ( كان يصيبنا ذلك ـ تعني الحيض ـ فنؤمر بقضاء الصوم ولا نؤمر بقضاء الصلاة ) متفق عليه .

« ያ ነገር (የወር አበባ) ያገኘን (ይመጣብን) ነበር።  ፆምን በሌላ ግዜ ፆመን እንድንተካ እንታዘዛለን ። ሰላትን ግን ሰግደን እንድንተካ አልታዘዝንም። » 
ቡካሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

   አንዲት ሴት በመፆም ላይ ሳለችም የወር አበባዋ ቢመጣባት ፆሟ ይበላሽባታል።

   ይህ ክስተት የተከሰተባት ከመግሪብ በፊት በደቂቃ ልዩነትም ቢሆን ፆሟ ፈራሽ ነው።

  የጀመረችው ፆምም የግዴታ ፆም ከነበረ በሌላ ግዜ በመፆም መተካት ይኖርባታል።

#ፆምን ለመከልከል የወር አበባው በግልፅ መፍሰስ አለበት።

   አንዲት ሴት በመፆም ላይ እያለች ከመግሪብ በፊት የወር አበባዋ የመምጣት ስሜት ወይም እንቅስቃሴው ተሰምቷት ነገር ግን ደም መፍሰስ የጀመራት ከመግሪብ በኋላ ከሆነ ፆሟ የተሟላ በመሆኑ ከሊቃውንት አስተያየቶች አንፃር ትክክለኛው ንግግር ፆሟ አይበላሽም የሚለው ነው።

   ምክንያቱም ገና በሆድ ውስጥ ያለውን ደም በመመርኮዝ የወር አበባ ውሳኔ አይሰጥበትም።

   ለዚህም ደጋፊ አስረጅ የሚሆነን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በህልሟ ወንዶች እንደሚያዩት (በህልም ግንኙነት መፈፀምን) ያየች ሴት ገላዋን መታጠብ ይኖርባታልን ተብለው ሲጠየቁ …

(نعم إذا هي رأت الماء) 

« አዎን ፈሳሽ ካየች » ብለዋል።

  ማለትም ከእንቅልፏ ስትነቃ ባየችው ህልም ሰበብ ከብልቷ ፈሳሽ ፈሷት ካየች ትታጠባለች ብለዋል።

   ገላ የመታጠብን ወይም ጀናባ የመሆንን ውሳኔ ያስተሳሰሩት የዘር ፈሳሽ ወጥቶ ከመታየት ጋር እንጂ በልቦና ወይም በሰውነት ውስጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ባለመሆኑ የወር አበባም ወደ ውጭ ሳይወጣ በሰውነቷ ውስጥ እንቅስቃሴ በማድረጉ ብቻ የመምጣት ውሳኔ አይሰጥበትም።

   ሀይድ ላይ እያለች ጎህ ከቀደደ ከፈጅር በኋላ ወዲያው ሀይዷ አብቆቶ ብትጠራም እንኳ መፆሟ ትክክል ባለመሆኑ ልትፆም አይገባም።

   ከፈጅር በፊት ከጠራችና የታጠበችው ግን ከፈጅር በኋላ ቢሆንም እንኳ ፆሟ ትክክለኛ በመሆኑ መፆም ትችላለች።

   የሚታየው የታጠበችበት ወቅት ሳይሆን የወር አበባው አብቅቶ የጠራችበት ወቅት በመሆኑ ውሳኔውም ከዚሁ ጋር ይሄዳል።

   ይህም ማለት ጀናባ የሆነ ሰው ፈጅር ከመድረሱ በፊት ለመፆም ኒያ ካሳደርና የታጠበው ግን የፈጅር ወቅት ከገባ በኋላ ቢሆንም ፆሙ ትክክል ነው።

   ይህንንም በማስመልከት ከኣዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በነገረችን መሰረት:

 لحديث عائشة رضي الله عنها قالت :
 ( كان النبي صلى الله عليه وسلم يصبح جنباً من جماع غير احتلام ثم يصوم في رمضان ) متفق عليه

« ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በህልም አይተው ሳይሆን (ኢህቲላም ሳይሆን) ለሊቱን የግብረስጋ ግንኙነት ፈፅመው ሳለ ገላቸውን ሳይታጠቡ ያነጉ ነበር። ረመዳንም ከሆነ ይፆሙ ነበር። »
ሙተፈቁን አለይሂ

  ከዚህ የምንወስደው ፈጅር ከመግባቱ በፊት ከወር አበባ ብትጠራና ወዲያው ለመፆም ብትነይት ከዚየም ገላዋን የታጠችው ከፈጅር በኋላ ቢሆን ምንም ችግር የለውም።

إذا طهرت المرأة بعد طلوع الفجر فللعلماء في إمساكها ذلك اليوم قولان:

القول الأول:
 إنه يلزمها الإمساك بقية ذلك اليوم ولكنه لا يحسب لها بل يجب عليها القضاء، وهذا هو المشهور من مذهب الإمام أحمد ـ رحمه الله ـ.

« ጎህ ከቀደደ በኋላ ከሀይድ የጠራች እንስት ፆሟን መቀጠልን በተመለከተ በኢስላም ሊቃውንት መካከል ሁለት አይነት አስተያየት ይገኛል።

①ኛው አስተያየት

   በኢማሙ አህመድ ረሂመሁላህ መዝሃብ ግልፅ እንደሆነው የእለቱ ፆም ባይቆጠርላትም እንኳ ቀሪውን ግዜ  ፆሟን ሳታፈርስ መጨረስ ይኖርባታል። በሌላ ግዜ ቀዷእ ማውጣት ግድ ይሆንባታል የሚል አቋም ይገኛል። 

والقول الثاني:
 إنه لا يلزمها أن تمسك بقية ذلك اليوم؛ لأنه يوم لا يصح صومها فيه لكونها في أوله حائضة ليست من أهل الصيام، وإذا لم يصح لم يبق للإمساك فائدة، وهذا الزمن زمن غير محترم بالنسبة لها؛ لأنها مأمورة بفطره في أول النهار، بل محرم عليها صومه في أول النهار،
 والصوم الشرعي هو: «الإمساك عن المفطرات تعبداً لله عز وجل   من طلوع الفجر إلى غروب الشمس» وهذا القول كما تراه أرجح من القول بلزوم الإمساك، وعلى كلا القولين يلزمها قضاء هذا اليوم.

②ኛው አስተያየት

   ልትፆመው የሚገባት እለት ስላልሆነ የእለቱን ቀሪ ክፍል ፆማ መጨረስ አይጠበቅባትም የሚል ነው።
 
   ምክንያቱም የእለቱ መጀመርያ ላይ ሀይድ ላይ ስለነበረች ፆም ከሚመለከታቸው ሰዎች አትመደብም።
  
   ስለሆነም ፆሙ ትክክለኛ እስካልሆነ ድረስ ቀኑን ሙሉ ፆመኛ ሆና ማሳለፏ ጥቅም የለውም።

   ገና ከንጋቱ እንዳትፆም የሚያደርጋት ትእዛዝ ስለመጣት ይህ ወቅት ለሷ በፆም ክብሩን ልትጠብቅ የሚገባት ወቅት አይደለም።

   እንዲያውም ከንጋት ጀምሮ መፆሙ ሀራም ሆኖባታል።

   #ሸሪኣው ያዘዘው ፆም ማለት
 
« ለአላህ በመታዘዝ ንጋት ጎህ ከቀደደ ጀምሮ እስከ ምሽት ፀሃይ መጥለቅ ድረስ ፆምን ከሚያስፈጥሩ ነገሮች መቆጠብ ነው።  »

   ከላይ ለማስረዳት እንደተሞከረው ከፈጅር በኋላ ወዲያው የጠራች ብትሆንም የእለቱን ፆም እንደ ፆመኛ ማሳለፍ አለባት ከሚለው አስተያየት አንፃር መፆም የለባትም የሚለው ብልጫ ያለው ነው።

   የጎደለባትን ፆም በተመለከተ በሁለቱም አስተያየት ሰጪ ምሁራን ዘንድ የእለቱን ፆም ቀዷ ማውጣት ግዴታዋ ነው። »

والله أعلم وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
#ተከታዩን_ሊንክ_በመጫን_ፔጁን_ላይክ(Like)_ያድርጉ

www.facebook.com/tenbihat
_______
󾔧abufewzan
23ረቢዕ አል-ሳኒ1436
13Feb2015‎

💥ስለ ሀይድ ህግጋት 💥
ክፍል-8
የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልእክት ቁ• 12
የወር አበባሽ ከመፆም ያቅብሻል
~~~~~~~~~~~~~~~~~
# ባሳለፍናቸው ክፍል 6 እና 7 ህግጋት የወር አበባ ላይ ያለች እንስት ዚክር ማድረግን እና ቁርኣን መቅራትን፣ ማድመጥን፣ እንዲሁም ቁርኣንን መንካትን በተመለከተ አላህ ያገራልንን ያህል ላስገነዝባችሁ ተሞክሯል።
እነሆም ለዛሬ ሀይድ ላይ ስትሆን ፆምን እንዴት እንደምታስተናግድ የሚያብራራውን መልእክት ያንብቡት። አላህ ባወቅነውም ተጠቃሚዎች ያድርገን።
‪#‎ፆምና‬ የወር አበባ
የወር አበባ ላይ ላለች እንስት የፍላጎትም ይሁን የግዴታ ፆምን መፆም ይከለከላል። ብትፆምም ትክክለኛ አይደለም።
በወር አበባዋ ወቅት ያለፋትንም እለታት ነፃ በሆነች ግዜ በመፆም ማካካስ ግድ ይሆንባታል።
ይህም ከምእመናን እናት ከኣዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በተነገረን መሰረት
لحديث عائشة رضي الله عنها : ( كان يصيبنا ذلك ـ تعني الحيض ـ فنؤمر بقضاء الصوم ولا نؤمر بقضاء الصلاة ) متفق عليه .
« ያ ነገር (የወር አበባ) ያገኘን (ይመጣብን) ነበር። ፆምን በሌላ ግዜ ፆመን እንድንተካ እንታዘዛለን ። ሰላትን ግን ሰግደን እንድንተካ አልታዘዝንም። »
ቡካሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
አንዲት ሴት በመፆም ላይ ሳለችም የወር አበባዋ ቢመጣባት ፆሟ ይበላሽባታል።
ይህ ክስተት የተከሰተባት ከመግሪብ በፊት በደቂቃ ልዩነትም ቢሆን ፆሟ ፈራሽ ነው።
የጀመረችው ፆምም የግዴታ ፆም ከነበረ በሌላ ግዜ በመፆም መተካት ይኖርባታል።
‪#‎ፆምን‬ ለመከልከል የወር አበባው በግልፅ መፍሰስ አለበት።
አንዲት ሴት በመፆም ላይ እያለች ከመግሪብ በፊት የወር አበባዋ የመምጣት ስሜት ወይም እንቅስቃሴው ተሰምቷት ነገር ግን ደም መፍሰስ የጀመራት ከመግሪብ በኋላ ከሆነ ፆሟ የተሟላ በመሆኑ ከሊቃውንት አስተያየቶች አንፃር ትክክለኛው ንግግር ፆሟ አይበላሽም የሚለው ነው።
ምክንያቱም ገና በሆድ ውስጥ ያለውን ደም በመመርኮዝ የወር አበባ ውሳኔ አይሰጥበትም።
ለዚህም ደጋፊ አስረጅ የሚሆነን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በህልሟ ወንዶች እንደሚያዩት (በህልም ግንኙነት መፈፀምን) ያየች ሴት ገላዋን መታጠብ ይኖርባታልን ተብለው ሲጠየቁ …
(نعم إذا هي رأت الماء)
« አዎን ፈሳሽ ካየች » ብለዋል።
ማለትም ከእንቅልፏ ስትነቃ ባየችው ህልም ሰበብ ከብልቷ ፈሳሽ ፈሷት ካየች ትታጠባለች ብለዋል።
ገላ የመታጠብን ወይም ጀናባ የመሆንን ውሳኔ ያስተሳሰሩት የዘር ፈሳሽ ወጥቶ ከመታየት ጋር እንጂ በልቦና ወይም በሰውነት ውስጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ባለመሆኑ የወር አበባም ወደ ውጭ ሳይወጣ በሰውነቷ ውስጥ እንቅስቃሴ በማድረጉ ብቻ የመምጣት ውሳኔ አይሰጥበትም።
ሀይድ ላይ እያለች ጎህ ከቀደደ ከፈጅር በኋላ ወዲያው ሀይዷ አብቆቶ ብትጠራም እንኳ መፆሟ ትክክል ባለመሆኑ ልትፆም አይገባም።
ከፈጅር በፊት ከጠራችና የታጠበችው ግን ከፈጅር በኋላ ቢሆንም እንኳ ፆሟ ትክክለኛ በመሆኑ መፆም ትችላለች።
የሚታየው የታጠበችበት ወቅት ሳይሆን የወር አበባው አብቅቶ የጠራችበት ወቅት በመሆኑ ውሳኔውም ከዚሁ ጋር ይሄዳል።
ይህም ማለት ጀናባ የሆነ ሰው ፈጅር ከመድረሱ በፊት ለመፆም ኒያ ካሳደርና የታጠበው ግን የፈጅር ወቅት ከገባ በኋላ ቢሆንም ፆሙ ትክክል ነው።
ይህንንም በማስመልከት ከኣዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በነገረችን መሰረት:
لحديث عائشة رضي الله عنها قالت :
( كان النبي صلى الله عليه وسلم يصبح جنباً من جماع غير احتلام ثم يصوم في رمضان ) متفق عليه
« ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በህልም አይተው ሳይሆን (ኢህቲላም ሳይሆን) ለሊቱን የግብረስጋ ግንኙነት ፈፅመው ሳለ ገላቸውን ሳይታጠቡ ያነጉ ነበር። ረመዳንም ከሆነ ይፆሙ ነበር። »
ሙተፈቁን አለይሂ
ከዚህ የምንወስደው ፈጅር ከመግባቱ በፊት ከወር አበባ ብትጠራና ወዲያው ለመፆም ብትነይት ከዚየም ገላዋን የታጠችው ከፈጅር በኋላ ቢሆን ምንም ችግር የለውም።
إذا طهرت المرأة بعد طلوع الفجر فللعلماء في إمساكها ذلك اليوم قولان:
القول الأول:
إنه يلزمها الإمساك بقية ذلك اليوم ولكنه لا يحسب لها بل يجب عليها القضاء، وهذا هو المشهور من مذهب الإمام أحمد ـ رحمه الله ـ.
« ጎህ ከቀደደ በኋላ ከሀይድ የጠራች እንስት ፆሟን መቀጠልን በተመለከተ በኢስላም ሊቃውንት መካከል ሁለት አይነት አስተያየት ይገኛል።
①ኛው አስተያየት
በኢማሙ አህመድ ረሂመሁላህ መዝሃብ ግልፅ እንደሆነው የእለቱ ፆም ባይቆጠርላትም እንኳ ቀሪውን ግዜ ፆሟን ሳታፈርስ መጨረስ ይኖርባታል። በሌላ ግዜ ቀዷእ ማውጣት ግድ ይሆንባታል የሚል አቋም ይገኛል።
والقول الثاني:
إنه لا يلزمها أن تمسك بقية ذلك اليوم؛ لأنه يوم لا يصح صومها فيه لكونها في أوله حائضة ليست من أهل الصيام، وإذا لم يصح لم يبق للإمساك فائدة، وهذا الزمن زمن غير محترم بالنسبة لها؛ لأنها مأمورة بفطره في أول النهار، بل محرم عليها صومه في أول النهار،
والصوم الشرعي هو: «الإمساك عن المفطرات تعبداً لله عز وجل من طلوع الفجر إلى غروب الشمس» وهذا القول كما تراه أرجح من القول بلزوم الإمساك، وعلى كلا القولين يلزمها قضاء هذا اليوم.
②ኛው አስተያየት
ልትፆመው የሚገባት እለት ስላልሆነ የእለቱን ቀሪ ክፍል ፆማ መጨረስ አይጠበቅባትም የሚል ነው።
ምክንያቱም የእለቱ መጀመርያ ላይ ሀይድ ላይ ስለነበረች ፆም ከሚመለከታቸው ሰዎች አትመደብም።
ስለሆነም ፆሙ ትክክለኛ እስካልሆነ ድረስ ቀኑን ሙሉ ፆመኛ ሆና ማሳለፏ ጥቅም የለውም።
ገና ከንጋቱ እንዳትፆም የሚያደርጋት ትእዛዝ ስለመጣት ይህ ወቅት ለሷ በፆም ክብሩን ልትጠብቅ የሚገባት ወቅት አይደለም።
እንዲያውም ከንጋት ጀምሮ መፆሙ ሀራም ሆኖባታል።
‪#‎ሸሪኣው‬ ያዘዘው ፆም ማለት
« ለአላህ በመታዘዝ ንጋት ጎህ ከቀደደ ጀምሮ እስከ ምሽት ፀሃይ መጥለቅ ድረስ ፆምን ከሚያስፈጥሩ ነገሮች መቆጠብ ነው። »
ከላይ ለማስረዳት እንደተሞከረው ከፈጅር በኋላ ወዲያው የጠራች ብትሆንም የእለቱን ፆም እንደ ፆመኛ ማሳለፍ አለባት ከሚለው አስተያየት አንፃር መፆም የለባትም የሚለው ብልጫ ያለው ነው።
የጎደለባትን ፆም በተመለከተ በሁለቱም አስተያየት ሰጪ ምሁራን ዘንድ የእለቱን ፆም ቀዷ ማውጣት ግዴታዋ ነው። »
والله أعلم وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
‪#‎ተከታዩን_ሊንክ_በመጫን_ፔጁን_ላይክ‬(Like)_ያድርጉ
www.facebook.com/tenbihat
_______
abufewzan
23ረቢዕ አል-ሳኒ1436
13Feb2015