Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከተውሂድ ጥሪ በፊት እና በኀላ???

ከተውሂድ ጥሪ በፊት እና በኀላ???
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከነብይነታቸው በፊት "ሙሃመዱል አሚን (ታማኙ ሙሃመድ)" ነበር የሚባሉት። ከአላህ ትዕዛዝ መጥቶላቸው ነብይ ሆነው የታዘዙበትን መልክት ቁሉ ላኢላሃ ኢለላህ ቱፍሊሁ "ከአላህ በስተቀር በሃቅ የሚመለክ የለም በሉ ትድኑ (ነፃ ትሆኑ) ዘንድ" የሚለውን መልክት ይፋ ሲያደርጉ
1) ዩሁዳዎች ቅናት ይዟቸው አስተባበሉ ተውራት ላይ ስለ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከመነገሩም ጋር፣ ወንድ ልጆቻቸውን ከሚያውቁት በላይ እሳቸውን ከማወቃቸውም ጋር፣
2) ሙሽሪኮች ደግሞ አማልክቶቻችንንየሚሳደብ፣ እብድ፣ ገጣሚ፣ ደጋሚ እና የመሳሰሉትን ብለው ወረዱባቸው።
ከዚህ ክስተት ትልቅ ትምህርት እንወስዳለን፣ እሱም ነብያት በሄዱበት የሄደ የነሱ መከራ አምሳያ ከፊሉ ሊደርስበት ይችላል።
ሌላው አንድ ሰው ከቅርብም ከሩቁም ስድቡም፣ ትችትም፣ ማንቋሸሹም የሚደርስበት ነብያት በሄዱበት መንገድ ሲጓዝ እንጂ ነብያት የሄዱበትን ተቃርቆ ሌላ አርስት ውስጥ ቢገባ የሚያወድሱት ሊኖሩ ይችላሉ።
ዳዕዋ ፍሬው ወይንም ውጤቱ የሚለካው በተከታይ ብዛት አይደለም። አንድ ዳዕዋ ችግር አለበት የሚባለው በተቃዋሚው ብዛት አይደለም። ይህ በሆነ ኖሮ ነብየላህ ኑህ አለይሂ ሰላም ያን ያህል ተጣርተው የተከተላቸው ጥቂት ሰው ብቻ ነው።
ሌላው አስገራሚ ነገር በነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት ዳዕዋ ተደርጎላቸውም ያላመኑ ሞልተዋል።
ማጠቃለያ
=======
አንድ ሰው ነብያት በተጣሩበት ከተጣራ፣ ያስቀደሙትን ካስቀደመ፣ ያወገዙትን ካወገዘ ይህ ዳኢ አኽላቅንም፣ ሂክማንም ተላብሷል፣ ነብያት ያወረሱት እውቀትም ስለሆነ በእውቀትም ወደ አላህ ከሚጣሩት ነው በአላህ ፈቃድ።
አላህ ነብያት በሄዱበት መንገድ ያስጉዘን፣ ያስቀደሙትን እና ትኩረት የሰጡትን ከሚሰጡ ያድርገን።