Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ሀይድ ክፍል - 7

‎♦ ስለ ሀይድ  ክፍል - 7♦ 

የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•9

የእንስቶች ወርሃዊው ዙር ህግጋት  ```````````````````````````````````````
     የወር አበባ (ሀይድ) ከምን 
       󾔧 ያቅበኛል ? 󾮙
         """""""""""""""""""""

    አንዳንድ እህቶቻችንና ወንድሞች በክፍል- 6 በሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርአንን መቅራት ትችላለችን? በሚለው ትምህርት  ላይ ላነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራርያ ይሆን ዘንድ፤

① ሀይድና ጀናባ ውስጥ ላሉ ቁርኣን መንካት እንዴት ይታያል?

 እና

② ሀይድ ላይ ሆና ማንበብ የምትችለው መቼ ነው?

 የሚሉ ተጨማሪ መልእክቶችን ጋብዘንዎታል።

         󾓿                   󾔁

① ሀይድና ጀናባ ውስጥ ላሉ ቁርኣን መንካትን በተመለከተ
```````````````````````````````` 
   ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተወራው 

 عن أبي بكر بن محمد بن عمرو بن حزم عن أبيه عن جده أن النبي صلى الله عليه وسلم كتب إلى أهل اليمن كتاباً وكان فيه " لا يمس القرآن إلا طاهر". [ورواه مالك مرسلاً بلفظه].

« ንፁህ ካልሆነ (ሰው) በስተቀር ቁርኣንን አይንካው። »

  የሚለውን ሙርሰል ሀዲስ ምሁራን ተቀብለውታል። 

   ይህንንም በማስመልከት ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ቀጣዩን አስተላልፈዋል።

{ ኢማሙ አህመድ እንዳሉት ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቁርኣንን ንፁህ ያልሆነ አይንካው የሚለውን ለየመን ህዝቦች በፃፉት ደብዳቤ ላይ ማስፈራቸው ጥርጥር የለበትም። 

   እንዲሁም ይህ ቃል የሰልማን አልፋሪሲ እና የአብደላህ ኢብኑ ዑመር ብሎም የሌሎች ሰሃቦች ጭምር ነው። 
ከሰሃቦች መካከልም ይህንን የሚቃረን አይታወቅም። }

ሲሉ ቁርኣን በአካል ቀጥታ መነካት እንደሌለበት አስረድተዋል።

   እንደሚታወቀው ንፁህ ሲባል የቃሉ ትርጉም ሁሉንም አይነት ንፅህና ያጠቃልላል። 

   ከሽርክና ወንጀሎች መፅዳትን፣ ከነጃሳዎችና ቆሻሻዎች መፅዳትን፣ እንዲሁም ከትንሹ ሀደስና ከትልቁም መፅዳትን ያጠቃልላል።

  *** በዚህም መሰረት ሀይድ ላይ ላለች ሴት ቁርኣንን ለሂፍዝም ሆነ ለትምህርት መንካት አይፈቀድላትም። ነገር ግን ሳትነካው መቅራትን በተመለከተ በቁጥር  6 መልእክታችን እንዳሰፈርነው ውስን በሆኑ ሁኔታዎች ብታነብ ችግር የለውም።

   አንዳንድ ሊቃውንት እንደሚሉትም ቁርኣንን ለመንካት ፣ ለመያዝ አማራጭ የሌለው አስገዳጅ ነገር ከተፈጠረ እንኳን መነካት ያለበት ቀጥታ በአካል ሳይሆን በጨርቅና በመሳሰሉት ሽፋን መሆን አለበት።

   ይህንን በማስመልከት ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ አክለው ሲያስረዱ:

« ንፁህም ባይኮን  መፅሀፉ ሳይነካ ከመፅሀፉ ወይም ከሰሌዳ ላይ ቢነበብ ይፈቀዳል። »

   በሌላ በኩል፤

" لا تقرأ الحائض، ولا الجنب شيئاً من القرآن " فهو حديث ضعيف. 

«  ሀይድ ላይ ያለች ሴትም ትሁን ጀናባ የሆነ ሰው ከቁርኣን ምንም ነገር አይቀራም»  
   
   የሚለው ሀዲስ ደዒፍ የሆነ ሀዲስ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።

   ጀናባ ላይ ያለ ሰውን በተመለከተ ግን 

 هناك حديث صحيح أن النبي صلى الله عليه وسلم  لا يمنعه شيء عن القرآن إلاَّ الجنابة 

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
« ቁርኣንን ከመቅራት ከጀናባ በስተቀር የሚከለክል የለም »

    ወንድም ይሁን ሴት ጀናባ እስከሆኑ ድረስ ቁርኣንን በልባቸውም ሆነ ከፅሁፍ ላይ ማንበብ አይፈቀድም።
እንዲሁም ቁርኣንን መንካትም አይፈቀድላቸውም።

                    󾀿󾀿󾀿󾀿󾀿

N:B- እንደሚታወቀው ቁርአን ለማንበብ መንካቱ ግዴታ አይደለም። በሂፍዝ መቅራት አንዱ ሲሆን፤ ብዙ ኡለማዎች እንደተስማሙበት የሙስሀፍ ህግጋት አይመለከቱትምና ከተፍሲርና የቁርአን ፍቺ ካላቸው መፅሀፎችን በመጠቀም መቅራት ትችላለች። 

     ባሁኑ ጊዜም የተለያዩ ተች የማያስፈልጋቸው ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አሉ፤ እነዚህን መጠቀም ችግር እንደሌለው አያጠራጥርም። ነገር ግን የተለያዩ ተች ሰወክሪን ሞባይሎችና መሳሪያዎች ላይ መቅራትን በተመለከተ ታላቁ አሊም ሸይኽ አብዱልከሪም አልኹደይር ተች ማድረግ ወይም በእጅ መንካት እንደማይፈቅ  ተናግረዋል። በድምፀወ የሚታዘዝ ወይም የሞባይሉን በተኖች በመጠቀም ከገፅ ወደገፅ መሄድ የምንችልበት ከሆነ ግን ችግር የለውም። 

②  ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን ሳትነካ መቅራት የምትችልባቸው ሁኔታን በተመለከተ የሸይኽ ሷሊህ አል ዑሰይሚን ረሂመሁላህ ማብራርያ
``````               `````             ``````
« ሀይድ ላይ ያለች ሴት ለአስገዳጅና አስፈላጊ ጉዳይ ቁርኣንን ማንበብ ትችላለች።

   ለምሳሌ
1~ መምህር ብትሆንና ተማሪዎቿን ለማስተማር ፣ እንዲሁም 

2~ ተማሪ ሆና ቁርኣንን ለመማር ስትል ፣ ወይም 

3~ ልጆቿን ለማስተማር ስትል 
እነሱ የሚቀሩትን ታርማለችም ቀድማቸውም ታነብላቸዋለች።

   ባጠቃላይ አስፈላጊ ሁኔታ ከገጠማት ማንበብ ይፈቀድላታል ፤ ችግርም የለበትም።

  በተጨማሪም የቀራችው ቁርኣን እንዳይረሳት ለማስታወስ ስትል ማንበብ ትችላለች። በዚህም ሀይድ ላይ መሆኗ ችግር አይፈጥርባትም።

   ሀይድ ላይ ያለች እንስት ቁርኣንን ሳትነካ ማንበብን በተመለከተ በምሁራን መካከል ሶስት አይነት አስተያየቶች ይገኛሉ።

1# አንዳንድ ምሁራን ሀይድ ላይ ያለች ሴት ያለ ምንም አስፈላጊ ጉዳይ ቁርኣንን ማንበብ ትችላለች ሲሉ

2# ሌሎች ደግሞ አስፈላጊ ጉዳይ እንኳ ቢገጥማት ቁርኣንን ማንበብ ሀራም ይሆንባታል ይላሉ

3# ሶስተኛው አቋም ደግሞ እንደ ማስተማር፣ መማርና እንዳተረሳው በመስጋት ቁርኣንን ማንበብ የሚያስፈልጋት ጉዳይ ሲገጥማት ብታነብ ችግር የለባትም። የሚል ነው። 

   ይህ ሶስተኛው አስተያየት ተቀባይነት ያለውና ሚዛን ደፊ አቋም ሊባል የሚገባው ነው። 

 مجموع فتاوى ورسائل الشيخ محمد صالح العثيمين - المجلد الحادي عشر - باب الحيض. 

                            󾀿󾀿󾀿󾀿󾀿

 ☞ ለማጠቃለል፤

 ― በሀይድ ጊዜ ቁርኣንን መንካትን በተመለከተ  ቀጥታ በእጅ ወይም በሌላ አካሏ መንካት አይፈቀድም። በጓንትና መሰል ጨርቅ በመጠቀም መቅራት ለችግር ግዜ ተፈቅዷል።

 ― ጀናባ ላይ የሆነ ወንድም በተመሳሳይ መንካት አይፈቀድለትም።

 ― ከሚቀራ ሰው ጋርም ይሁን ለብቻ ቁርአኑን ሳትነካው መቅራትን በተመለከተ አስፈላጊ የሚሆንባቸውን ሁኔታዎች ገልፀን በሌላ ጊዜያት አለመቅራቷ የተሻለ መሆኑን የሊቃውንት ማብራርያን አስፍረናል። 

― ከሞባይል ላይ የቁርአንን ፅሁፍ ተች በማድረግ መንካት አይፈቀድም። በሌላ መንገድ ስክሪኑን ሳይነካ ቁርአኑን መግለፅና ሶፍርዌሩን መጠቀም ከተቻለ ችግር የለውም።

  ስለሆነም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ያላችሁ ቁጥር 6 እና 7 የሀይድ ማብራርያን ደጋግመው ቢያነቡ ምላሹን እዚያው ያገኛሉ።

ባረከላሁ ፊኩም
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን
______________

وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
#ተከታዩን-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ

www.facebook.com/tenbihat

               إن شاء الله ይቀጥላል
_________
󾔧Abufewzan احمد سيرة
19 ረቢዕ አልሳኒ 1436   8 Feb15
…‎

ስለ ሀይድ ክፍል - 7
የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•9
የእንስቶች ወርሃዊው ዙር ህግጋት ```````````````````````````````````````
የወር አበባ (ሀይድ) ከምን
ያቅበኛል ?
"""""""""""""""""""""
አንዳንድ እህቶቻችንና ወንድሞች በክፍል- 6 በሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርአንን መቅራት ትችላለችን? በሚለው ትምህርት ላይ ላነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራርያ ይሆን ዘንድ፤
① ሀይድና ጀናባ ውስጥ ላሉ ቁርኣን መንካት እንዴት ይታያል?
እና
② ሀይድ ላይ ሆና ማንበብ የምትችለው መቼ ነው?
የሚሉ ተጨማሪ መልእክቶችን ጋብዘንዎታል።
📗 📙
① ሀይድና ጀናባ ውስጥ ላሉ ቁርኣን መንካትን በተመለከተ
````````````````````````````````
ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተወራው
عن أبي بكر بن محمد بن عمرو بن حزم عن أبيه عن جده أن النبي صلى الله عليه وسلم كتب إلى أهل اليمن كتاباً وكان فيه " لا يمس القرآن إلا طاهر". [ورواه مالك مرسلاً بلفظه].
« ንፁህ ካልሆነ (ሰው) በስተቀር ቁርኣንን አይንካው። »
የሚለውን ሙርሰል ሀዲስ ምሁራን ተቀብለውታል።
ይህንንም በማስመልከት ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ቀጣዩን አስተላልፈዋል።
{ ኢማሙ አህመድ እንዳሉት ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቁርኣንን ንፁህ ያልሆነ አይንካው የሚለውን ለየመን ህዝቦች በፃፉት ደብዳቤ ላይ ማስፈራቸው ጥርጥር የለበትም።
እንዲሁም ይህ ቃል የሰልማን አልፋሪሲ እና የአብደላህ ኢብኑ ዑመር ብሎም የሌሎች ሰሃቦች ጭምር ነው።
ከሰሃቦች መካከልም ይህንን የሚቃረን አይታወቅም። }
ሲሉ ቁርኣን በአካል ቀጥታ መነካት እንደሌለበት አስረድተዋል።
እንደሚታወቀው ንፁህ ሲባል የቃሉ ትርጉም ሁሉንም አይነት ንፅህና ያጠቃልላል።
ከሽርክና ወንጀሎች መፅዳትን፣ ከነጃሳዎችና ቆሻሻዎች መፅዳትን፣ እንዲሁም ከትንሹ ሀደስና ከትልቁም መፅዳትን ያጠቃልላል።
*** በዚህም መሰረት ሀይድ ላይ ላለች ሴት ቁርኣንን ለሂፍዝም ሆነ ለትምህርት መንካት አይፈቀድላትም። ነገር ግን ሳትነካው መቅራትን በተመለከተ በቁጥር 6 መልእክታችን እንዳሰፈርነው ውስን በሆኑ ሁኔታዎች ብታነብ ችግር የለውም።
አንዳንድ ሊቃውንት እንደሚሉትም ቁርኣንን ለመንካት ፣ ለመያዝ አማራጭ የሌለው አስገዳጅ ነገር ከተፈጠረ እንኳን መነካት ያለበት ቀጥታ በአካል ሳይሆን በጨርቅና በመሳሰሉት ሽፋን መሆን አለበት።
ይህንን በማስመልከት ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ አክለው ሲያስረዱ:
« ንፁህም ባይኮን መፅሀፉ ሳይነካ ከመፅሀፉ ወይም ከሰሌዳ ላይ ቢነበብ ይፈቀዳል። »
በሌላ በኩል፤
" لا تقرأ الحائض، ولا الجنب شيئاً من القرآن " فهو حديث ضعيف.
« ሀይድ ላይ ያለች ሴትም ትሁን ጀናባ የሆነ ሰው ከቁርኣን ምንም ነገር አይቀራም»
የሚለው ሀዲስ ደዒፍ የሆነ ሀዲስ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
ጀናባ ላይ ያለ ሰውን በተመለከተ ግን
هناك حديث صحيح أن النبي صلى الله عليه وسلم لا يمنعه شيء عن القرآن إلاَّ الجنابة
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
« ቁርኣንን ከመቅራት ከጀናባ በስተቀር የሚከለክል የለም »
ወንድም ይሁን ሴት ጀናባ እስከሆኑ ድረስ ቁርኣንን በልባቸውም ሆነ ከፅሁፍ ላይ ማንበብ አይፈቀድም።
እንዲሁም ቁርኣንን መንካትም አይፈቀድላቸውም።

N:B- እንደሚታወቀው ቁርአን ለማንበብ መንካቱ ግዴታ አይደለም። በሂፍዝ መቅራት አንዱ ሲሆን፤ ብዙ ኡለማዎች እንደተስማሙበት የሙስሀፍ ህግጋት አይመለከቱትምና ከተፍሲርና የቁርአን ፍቺ ካላቸው መፅሀፎችን በመጠቀም መቅራት ትችላለች።
ባሁኑ ጊዜም የተለያዩ ተች የማያስፈልጋቸው ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አሉ፤ እነዚህን መጠቀም ችግር እንደሌለው አያጠራጥርም። ነገር ግን የተለያዩ ተች ሰወክሪን ሞባይሎችና መሳሪያዎች ላይ መቅራትን በተመለከተ ታላቁ አሊም ሸይኽ አብዱልከሪም አልኹደይር ተች ማድረግ ወይም በእጅ መንካት እንደማይፈቅ ተናግረዋል። በድምፀወ የሚታዘዝ ወይም የሞባይሉን በተኖች በመጠቀም ከገፅ ወደገፅ መሄድ የምንችልበት ከሆነ ግን ችግር የለውም።
② ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን ሳትነካ መቅራት የምትችልባቸው ሁኔታን በተመለከተ የሸይኽ ሷሊህ አል ዑሰይሚን ረሂመሁላህ ማብራርያ
`````` ````` ``````
« ሀይድ ላይ ያለች ሴት ለአስገዳጅና አስፈላጊ ጉዳይ ቁርኣንን ማንበብ ትችላለች።
ለምሳሌ
1~ መምህር ብትሆንና ተማሪዎቿን ለማስተማር ፣ እንዲሁም
2~ ተማሪ ሆና ቁርኣንን ለመማር ስትል ፣ ወይም
3~ ልጆቿን ለማስተማር ስትል
እነሱ የሚቀሩትን ታርማለችም ቀድማቸውም ታነብላቸዋለች።
ባጠቃላይ አስፈላጊ ሁኔታ ከገጠማት ማንበብ ይፈቀድላታል ፤ ችግርም የለበትም።
በተጨማሪም የቀራችው ቁርኣን እንዳይረሳት ለማስታወስ ስትል ማንበብ ትችላለች። በዚህም ሀይድ ላይ መሆኗ ችግር አይፈጥርባትም።
ሀይድ ላይ ያለች እንስት ቁርኣንን ሳትነካ ማንበብን በተመለከተ በምሁራን መካከል ሶስት አይነት አስተያየቶች ይገኛሉ።
1# አንዳንድ ምሁራን ሀይድ ላይ ያለች ሴት ያለ ምንም አስፈላጊ ጉዳይ ቁርኣንን ማንበብ ትችላለች ሲሉ
2# ሌሎች ደግሞ አስፈላጊ ጉዳይ እንኳ ቢገጥማት ቁርኣንን ማንበብ ሀራም ይሆንባታል ይላሉ
3# ሶስተኛው አቋም ደግሞ እንደ ማስተማር፣ መማርና እንዳተረሳው በመስጋት ቁርኣንን ማንበብ የሚያስፈልጋት ጉዳይ ሲገጥማት ብታነብ ችግር የለባትም። የሚል ነው።
ይህ ሶስተኛው አስተያየት ተቀባይነት ያለውና ሚዛን ደፊ አቋም ሊባል የሚገባው ነው።
مجموع فتاوى ورسائل الشيخ محمد صالح العثيمين - المجلد الحادي عشر - باب الحيض.

☞ ለማጠቃለል፤
― በሀይድ ጊዜ ቁርኣንን መንካትን በተመለከተ ቀጥታ በእጅ ወይም በሌላ አካሏ መንካት አይፈቀድም። በጓንትና መሰል ጨርቅ በመጠቀም መቅራት ለችግር ግዜ ተፈቅዷል።
― ጀናባ ላይ የሆነ ወንድም በተመሳሳይ መንካት አይፈቀድለትም።
― ከሚቀራ ሰው ጋርም ይሁን ለብቻ ቁርአኑን ሳትነካው መቅራትን በተመለከተ አስፈላጊ የሚሆንባቸውን ሁኔታዎች ገልፀን በሌላ ጊዜያት አለመቅራቷ የተሻለ መሆኑን የሊቃውንት ማብራርያን አስፍረናል።
― ከሞባይል ላይ የቁርአንን ፅሁፍ ተች በማድረግ መንካት አይፈቀድም። በሌላ መንገድ ስክሪኑን ሳይነካ ቁርአኑን መግለፅና ሶፍርዌሩን መጠቀም ከተቻለ ችግር የለውም።
ስለሆነም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ያላችሁ ቁጥር 6 እና 7 የሀይድ ማብራርያን ደጋግመው ቢያነቡ ምላሹን እዚያው ያገኛሉ።
ባረከላሁ ፊኩም
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን
______________
وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
‪#‎ተከታዩን‬-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ
www.facebook.com/tenbihat
إن شاء الله ይቀጥላል
_________
Abufewzan احمد سيرة
19 ረቢዕ አልሳኒ 1436 8 Feb15