Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ሀይድ ህግጋት ክፍል-6

‎󾔺   ስለ ሀይድ ህግጋት   󾔁
               ክፍል-6 

የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•9

     የወር አበባ (ሀይድ) ከምን 
         󾀿 ያግድሻል ? 󾀿 
            """"""""""""""""""""
* ባለፈው መልእክት የወር አበባ ላይ ያለች እንስት ሰላትን ከመስገድ እንደምትቆጠብ እንዲሁም በሰላት ወቅት መግቢያና ማብቂያ ላይ ያለውን  ድንጋጌ ተመልክተናል።

* እነሆ ለዛሬ ሀይድ ከዚክር እንዲሁም ቁርኣን ከመቅራት ጋር ያለውን ድንጋጌ በአላህ ፈቃድ እንመለከታለን ።

    ዚክር እና ቁርኣንን መቅራት
    ```````````````````````````````
   የወር አበባ ላይ ያለች እንስት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን የምታወሳበትን ቃላቶች እንደ ተስቢህ፣ ታህሚድ፣ ተክቢርና ስትመገብ ቢስሚላህ ማለትን የመሳሰሉ እንዲሁም ሃዲስን ማንበብ፣ የፊቅህ ኪታቦችን ማንበብ፣ ዱዓእ ማድረግ፣ ዱዓእ ሲደረግ ኣሚን ማለት እና ቁርኣንን ማድመጥ በሙሉ ያለ ምንም ተቃውሞ ይፈቀድላታል። ክልከላ የለባትም።

   ቁርኣንነ ሲቀራ ማድመጥን በተመለከተም ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት መሰረት ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ሀይድ ላይ እያለች የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በደረቷ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር እሷም ታደምጥ ነበር።

   በሌላ የኢማም ቡኻሪና ሙስሊም ዘገባም ኡሙ ዐጢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ ከነቢዩ ﷺ የሰማችውን እንደሚቀጥለው ገልፃለች:
󾔁 وفي الصحيحين أيضاً عن أم عطية رضي الله عنها أنها سمعت النبي صلى الله عليه وسلم يقول : ( يخرج العواتق وذوات الخدور والحيض ـ يعني إلى صلاة العيدين ـ وليشهدن الخير ودعوة المؤمنين ويعتزل الحيض المصلى ) .

« ለጋብቻ የደረሱም ልጃገረዶችም እንዲሁም ሀይድ ላይ ያሉ ሴቶችም ለሁለቱ ዒዶች ይወጣሉ። በዚህም መልካም ነገር ላይ ይሳተፋሉ፣ የምዕመናንን ዱዓእ ይቀበላሉ፤ ነገር ግን ሀይድ ላይ ያሉት ከሰላት ይርቃሉ። »

*  ቁርኣን መቅራትን በተመለከተ ሀይድ ላይ ያለች እንስት:
 
~ በአንደበቷ ሳታነበንብ ፅሁፉን በዐይኗ መከታተሏና በልቧ ማስተዋሏ ምንም ችግር የለበትም።

~ ኢማሙ ነወዊ ረሂመሁላህ 
" ሸርሁል ሙሀዘብ شرح المهزب " በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ ባሰፈሩት መሰረት :

󾮜 ሀይድ ላይ ያለች እንስት በራሷ ቁርኣን ለመቅራት ከፈለገችና ፊትለፊቷ ተደርጎ ወይም ሰሌዳ ላይ ተፅፎ እያየች ከአንደበቷ ሳይወጣ በልቧ ብታነብ ያለ ምንም የምሁራን ኺላፍ የተፈቀደ ነው።

 በማለት ገልፀዋል።

~• ቁርኣንን በአንደበቷ ማንበብን በተመለከተ አብዛኞቹ ሊቃውንት (ዑለማእ) ክልክል ነው አይፈቀድም ይላሉ።

ሀይድ ላይ ላለች ሴት ቁርኣንን ማንበቧ አይከለከልም የሚሉ
      󾓿 መረጃዎች
        ``````````````
¹# ነገር ግን ኢማሙ ቡኻሪ፣ ኢብኑ ጀሪር አልጠበሪና ኢብኑ ሙንዚር ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን በአንደበቷ ማንበቧ የተፈቀደ ነው ክልከላ የለበትም ብለዋል።

 ²#  ከኢማሙ ማሊክና ሻፊዒይ ቀደም ካለው ንግግራቸው በተወራው መሰረትና ኢማሙ ቡኻሪይ " ፈትሁ ባሪ " ላይ  በኢብራሂም አልነኸዒ ንግግር ላይ አስተያየት ሰጥተው ባሰፈሩት መሰረትም  " ቁርኣን ማንበቡ ችግር የለውም " ብለዋል።

³# ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ በ " ፈታዋ " ድርሳናቸው ላይ እንደገለፁት:

وقال شيخ الإسلام ابن تيمية في "الفتاوى" : " ليس في منعها من القرآن سنة أصلاً ، فإن قوله : ( لا تقرأ الحائض ولا الجنب شيئاً من القرآن ) حديث ضعيف باتفاق أهل المعرفة بالحديث . وقد كان النساء يحضن في عهد النبي صلى الله عليه وسلم ، فلو كانت القراءة محرمة عليهن كالصلاة ، لكان هذا مما بينه النبي صلى الله عليه وسلم لأمته وتعلمه أمهات المؤمنين وكان ذلك مما ينقلونه في الناس ، فلما لم ينقل أحد عن النبي صلى الله عليه وسلم في ذلك نهياً لم يجز أن تجعل حراماً ، مع العلم أنه لم ينه عن ذلك ، وإذا لم ينه عنه مع كثرة الحيض في زمنه علم أنه ليس بمحرم " انتهى .

( በመሰረቱ ከቁርኣንም ይሁን ከሱና (ሀይድ ላይ ያለች እንስት እንዳትቀራ) የሚከለክላት መረጃ የለም ብለዋል።

" ሀይድ ላይ ያለች ሴትም ትሁን ጀናባ የሆነ ሰው ቁርኣን ምንም አያነብም። " የተባለው ሀዲስ የዘርፉ ማለትም የሀዲስ ሊቃውንት በሆኑት ስምምነት መሰረት ደዒፍ ነው።

   በነቢዩ    ዘመን ሴቶች ሀይድ ይፈሳቸው ነበር፤ ቁርኣንን መቅራቷ እነደ ሰላት ሁሉ ክልክል ቢሆንባት ኖሮ ነቢዩ  ለህዝባቸው ከሚያስጠነቅቁት ጉዳይ ኣንዱ ይሆን ነበር። የምእመናን እናቶችንም ያስተምሩ ነበር። ይህንንም ጉዳይ እነሱ ለተቀሪው ሰው ከሚያስተላልፉት መረጃ ይካተት ነበር።

   በመሆኑም ከመልእክተኛው  ኣንድም ሰው ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን እንዳታነብ የሚል መረጃ ካላስተላለፈ ይህ ነገር ክልክል ማለት አይፈቀድም።

   እንደሚታወቀው እሳቸው ያንን ጉዳይ አልከለከሉምና።

   በዘመናቸው በርካታ እንስቶች ሀይድ አየመጣቸው እየታወቀም ቁርኣንን አታንብቡ ብለው አልከለከሉም።

 ስለዚህም ሃራም ኣለመሆኑ ታወቀ ማለት ነው። )

"   የሸይኩል ኢስላም ንግግር አብቅቷል። "
         ~~~~~~~

* የምሁራንን አስተያየትና ልዩነት ከተረዳን ፤ ከኛ የሚጠበቀው 

󾮜 የኢስላም ሊቃውንት እንዳስረዱት አስፈላጊ ጉዳይ ካልገጠማት በስተቀር ሀይድ ላይ ያለች እንስት ቁርኣንን በአንደበቷ ባታነብ የተሻለ ነው።

ለምሳሌ:
``````````
•~  የቁርኣን አስተማሪ ከሆነችና ተማሪዎቿን ማረም ካስፈለጋት ብታነብ ወቀሳ የለባትም።

•~  እንዲሁም የቁርኣን ተማሪ ከሆነችና ሀይዷ የመጣባትም በዚሁ በፈተና ወቅቷ ከሆነ ለፈተናው ስትልና ለመሳሰሉት አስፈላጊ ጉዳዮች ብታነብ አግባቢ እንደሆነ ሊቃውንት ያስረዳሉ  ።
_____________

በቀጣዩ ርዕሳችን ኢን ሻአ አላህ ፤ የወር አበባ ላይ ያለች እንስት ፆምን መፆም በተመለከተ ያለውን ድንጋጌ እንመለከታለን።

وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
#ተከታዩን-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ

www.facebook.com/tenbihat
_________
󾔧Abufewzan
18 ረቢዕ አልሳኒ 1436    
7 Feb15‎

📎 ስለ ሀይድ ህግጋት 📙
ክፍል-6
የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•9
የወር አበባ (ሀይድ) ከምን
ያግድሻል ?
""""""""""""""""""""
* ባለፈው መልእክት የወር አበባ ላይ ያለች እንስት ሰላትን ከመስገድ እንደምትቆጠብ እንዲሁም በሰላት ወቅት መግቢያና ማብቂያ ላይ ያለውን ድንጋጌ ተመልክተናል።
* እነሆ ለዛሬ ሀይድ ከዚክር እንዲሁም ቁርኣን ከመቅራት ጋር ያለውን ድንጋጌ በአላህ ፈቃድ እንመለከታለን ።
ዚክር እና ቁርኣንን መቅራት
```````````````````````````````
የወር አበባ ላይ ያለች እንስት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን የምታወሳበትን ቃላቶች እንደ ተስቢህ፣ ታህሚድ፣ ተክቢርና ስትመገብ ቢስሚላህ ማለትን የመሳሰሉ እንዲሁም ሃዲስን ማንበብ፣ የፊቅህ ኪታቦችን ማንበብ፣ ዱዓእ ማድረግ፣ ዱዓእ ሲደረግ ኣሚን ማለት እና ቁርኣንን ማድመጥ በሙሉ ያለ ምንም ተቃውሞ ይፈቀድላታል። ክልከላ የለባትም።
ቁርኣንነ ሲቀራ ማድመጥን በተመለከተም ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት መሰረት ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ሀይድ ላይ እያለች የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በደረቷ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር እሷም ታደምጥ ነበር።
በሌላ የኢማም ቡኻሪና ሙስሊም ዘገባም ኡሙ ዐጢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ ከነቢዩ ﷺ የሰማችውን እንደሚቀጥለው ገልፃለች:
📙 وفي الصحيحين أيضاً عن أم عطية رضي الله عنها أنها سمعت النبي صلى الله عليه وسلم يقول : ( يخرج العواتق وذوات الخدور والحيض ـ يعني إلى صلاة العيدين ـ وليشهدن الخير ودعوة المؤمنين ويعتزل الحيض المصلى ) .
« ለጋብቻ የደረሱም ልጃገረዶችም እንዲሁም ሀይድ ላይ ያሉ ሴቶችም ለሁለቱ ዒዶች ይወጣሉ። በዚህም መልካም ነገር ላይ ይሳተፋሉ፣ የምዕመናንን ዱዓእ ይቀበላሉ፤ ነገር ግን ሀይድ ላይ ያሉት ከሰላት ይርቃሉ። »
* ቁርኣን መቅራትን በተመለከተ ሀይድ ላይ ያለች እንስት:
~ በአንደበቷ ሳታነበንብ ፅሁፉን በዐይኗ መከታተሏና በልቧ ማስተዋሏ ምንም ችግር የለበትም።
~ ኢማሙ ነወዊ ረሂመሁላህ
" ሸርሁል ሙሀዘብ شرح المهزب " በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ ባሰፈሩት መሰረት :
ሀይድ ላይ ያለች እንስት በራሷ ቁርኣን ለመቅራት ከፈለገችና ፊትለፊቷ ተደርጎ ወይም ሰሌዳ ላይ ተፅፎ እያየች ከአንደበቷ ሳይወጣ በልቧ ብታነብ ያለ ምንም የምሁራን ኺላፍ የተፈቀደ ነው።
በማለት ገልፀዋል።
~• ቁርኣንን በአንደበቷ ማንበብን በተመለከተ አብዛኞቹ ሊቃውንት (ዑለማእ) ክልክል ነው አይፈቀድም ይላሉ።
ሀይድ ላይ ላለች ሴት ቁርኣንን ማንበቧ አይከለከልም የሚሉ
📗 መረጃዎች
``````````````
¹# ነገር ግን ኢማሙ ቡኻሪ፣ ኢብኑ ጀሪር አልጠበሪና ኢብኑ ሙንዚር ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን በአንደበቷ ማንበቧ የተፈቀደ ነው ክልከላ የለበትም ብለዋል።
²# ከኢማሙ ማሊክና ሻፊዒይ ቀደም ካለው ንግግራቸው በተወራው መሰረትና ኢማሙ ቡኻሪይ " ፈትሁ ባሪ " ላይ በኢብራሂም አልነኸዒ ንግግር ላይ አስተያየት ሰጥተው ባሰፈሩት መሰረትም " ቁርኣን ማንበቡ ችግር የለውም " ብለዋል።
³# ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ በ " ፈታዋ " ድርሳናቸው ላይ እንደገለፁት:
وقال شيخ الإسلام ابن تيمية في "الفتاوى" : " ليس في منعها من القرآن سنة أصلاً ، فإن قوله : ( لا تقرأ الحائض ولا الجنب شيئاً من القرآن ) حديث ضعيف باتفاق أهل المعرفة بالحديث . وقد كان النساء يحضن في عهد النبي صلى الله عليه وسلم ، فلو كانت القراءة محرمة عليهن كالصلاة ، لكان هذا مما بينه النبي صلى الله عليه وسلم لأمته وتعلمه أمهات المؤمنين وكان ذلك مما ينقلونه في الناس ، فلما لم ينقل أحد عن النبي صلى الله عليه وسلم في ذلك نهياً لم يجز أن تجعل حراماً ، مع العلم أنه لم ينه عن ذلك ، وإذا لم ينه عنه مع كثرة الحيض في زمنه علم أنه ليس بمحرم " انتهى .
( በመሰረቱ ከቁርኣንም ይሁን ከሱና (ሀይድ ላይ ያለች እንስት እንዳትቀራ) የሚከለክላት መረጃ የለም ብለዋል።
" ሀይድ ላይ ያለች ሴትም ትሁን ጀናባ የሆነ ሰው ቁርኣን ምንም አያነብም። " የተባለው ሀዲስ የዘርፉ ማለትም የሀዲስ ሊቃውንት በሆኑት ስምምነት መሰረት ደዒፍ ነው።
በነቢዩ ዘመን ሴቶች ሀይድ ይፈሳቸው ነበር፤ ቁርኣንን መቅራቷ እነደ ሰላት ሁሉ ክልክል ቢሆንባት ኖሮ ነቢዩ ለህዝባቸው ከሚያስጠነቅቁት ጉዳይ ኣንዱ ይሆን ነበር። የምእመናን እናቶችንም ያስተምሩ ነበር። ይህንንም ጉዳይ እነሱ ለተቀሪው ሰው ከሚያስተላልፉት መረጃ ይካተት ነበር።
በመሆኑም ከመልእክተኛው ኣንድም ሰው ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርኣንን እንዳታነብ የሚል መረጃ ካላስተላለፈ ይህ ነገር ክልክል ማለት አይፈቀድም።
እንደሚታወቀው እሳቸው ያንን ጉዳይ አልከለከሉምና።
በዘመናቸው በርካታ እንስቶች ሀይድ አየመጣቸው እየታወቀም ቁርኣንን አታንብቡ ብለው አልከለከሉም።
ስለዚህም ሃራም ኣለመሆኑ ታወቀ ማለት ነው። )
" የሸይኩል ኢስላም ንግግር አብቅቷል። "
~~~~~~~
* የምሁራንን አስተያየትና ልዩነት ከተረዳን ፤ ከኛ የሚጠበቀው
የኢስላም ሊቃውንት እንዳስረዱት አስፈላጊ ጉዳይ ካልገጠማት በስተቀር ሀይድ ላይ ያለች እንስት ቁርኣንን በአንደበቷ ባታነብ የተሻለ ነው።
ለምሳሌ:
``````````
•~ የቁርኣን አስተማሪ ከሆነችና ተማሪዎቿን ማረም ካስፈለጋት ብታነብ ወቀሳ የለባትም።
•~ እንዲሁም የቁርኣን ተማሪ ከሆነችና ሀይዷ የመጣባትም በዚሁ በፈተና ወቅቷ ከሆነ ለፈተናው ስትልና ለመሳሰሉት አስፈላጊ ጉዳዮች ብታነብ አግባቢ እንደሆነ ሊቃውንት ያስረዳሉ ።
_____________
በቀጣዩ ርዕሳችን ኢን ሻአ አላህ ፤ የወር አበባ ላይ ያለች እንስት ፆምን መፆም በተመለከተ ያለውን ድንጋጌ እንመለከታለን።
وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
‪#‎ተከታዩን‬-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ
www.facebook.com/tenbihat
_________
Abufewzan
18 ረቢዕ አልሳኒ 1436
7 Feb15