Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስጋት አያጣንም ገላጋያችን ግን አላህ ብቻ ነው

~`~ ~`~
ስጋት አያጣንም
ገላጋያችን ግን አላህ ብቻ ነው
________ √ _________
« በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእመናን) አይነት መከራ ብጤ ሳይመጣችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን
መልእክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት " የአላህ እርዳታ መቸ ነው ? ! " እስሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው ፤ ተርበደበዱም።
ንቁ የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው። (ተባሉም)። »
አል በቀራህ: 214
” أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُم مَّثَلُ الَّذِينَ خَلَوْا مِن قَبْلِكُم ۖ مَّسَّتْهُمُ الْبَأْسَاءُ وَالضَّرَّاءُ وَزُلْزِلُوا حَتَّىٰ يَقُولَ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ مَتَىٰ نَصْرُ اللَّهِ ۗ أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ“ .
البقرة: (214)
በእርግጥም ቅርብ ነው ። በተግባርም አዩት።
ሰለዋቱላሂ ወሰላሙሁ ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ ወአላ ኣሊሂ ወሳህቢሂ ወሰለም።
ተርበድብደውም ፀኑ። ግራ ቀኝ አላሉም።
እንኳንስ በሌላ ፍጡር ከመሃላቸው በነበሩት በሰው ልጆች አለቃ በመልእክተኛው ላይ እንኳ ተስፋ አልጣሉም አልተማመኑምም።
የአላህ እርዳታን ነበር የከጀሉት። እጅ ለእጅ ተያይዘውም ለታላቁ ስኬት በቁ።
ረዲየላሁ ዐንሁም አጅመዒን።

Post a Comment

0 Comments