Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አርቴፊሻል ጥፍር ማስተከል እንዴት ይታያል?

‎አርቴፊሻል ጥፍር ማስተከል እንዴት ይታያል?

ሰው ሰራሽ ጥፍር ለማስተከል ምክኒያት ሊሆን የሚችለው ከሁለት አንዱ ነው! 

1) የተነቀለ ጥፍርን ለመተካት ሊሆን ይችላል፤ ይህ እንደ ህክምና ይታያል። ክልክልም አይሆንም። ለዚህም መረጃ የሚሆነን ቲርሚዚይ የዘገቡትና አልባኒም ሰሂህ ያሉት የዓርፈጃህ ኢብኑል አስዓድ ሀዲስ ነው። በጃሂሊያ ዘመን የተቆረጠ አፍንጫውን የተካበት ብር (silver) ስለበሰበሰ በወርቅ እንዲተካው መልእክተኛው እንደፈቀዱለት ተናግሯል። ይህ የሚያሳየው በዚህ መልክ ጉዳት የደረሰበትን አካል መተካት ችግር እንደሌለው ነው። 

እዚህ ላይ ልናጤነው የሚገባው፤
ሀ) ጥፍሩ ረጅም መሆን የለበትም
ለ) ውሀ ከስር ወዳለው የሰውነት ክፍል ይደርስ ዘንድ ለውዱእና ለትጥበት በቀላሉ የሚነሳ አይነት መምረጥ ያስፈልጋል። በጣም የሚያስቸግር ከሆነ ግን ችግር አይኖረውም። 

2) ለውበት ጥፍርን መተካት፤ 
ይህ አይፈቀድም! የዚህም ዋነኛ ምክኒያቱ የአላህን አፈጣጠር መቀየር መሆኑ ነው። እንደዚሁ ሌላ ሰዎች ተፈጥሯዊ ጥፍር እንዲመስላቸው ስለሚያደርግ መሸንገል ነው። 

አርቲፊሻል ጥፍር ስለማስረከል በሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ተጠይቆ እንደመለሰው፤

" لا يجوز استخدام الأظافر قال علماء اللجنة الدائمة : " لا يجوز استخدام الأظافر الصناعية...؛ لما فيها من الضرر على محالها من الجسم ، ولما فيها -أيضا- من الغش والخداع وتغيير خلق الله ، وبالله التوفيق " انتهى من " فتاوى اللجنة الدائمة  ( 17/ 133 ) . 

«አርቲፊሻል ጥፍር መጠቀም አይቻልም! ምክኒያቱም፤የሚተከልበት የሰውነት አካል ላይ ጉዳት ያደርሳል! ከዚህም ባሻገር ሰዎችን መሸንገልና ማታለል ነው፤ እንደዚሁ የአላህንም ፍጥረት መቀየር ነው።»   በሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ 17/133

www.facebook.com/tenbihat‎

www.facebook.com/tenbihat