Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መንሀጅን (የሰለፎችን መንገድ) ከትክክለኛ ባለቤቱ አለመያዝ እና እውቀትን እንዴትና ከማን መያዝ እንዳለብን አለማወቅ የፊትና ሰበብ ነው።

መንሀጅን (የሰለፎችን መንገድ) ከትክክለኛ ባለቤቱ አለመያዝ እና እውቀትን እንዴትና ከማን መያዝ እንዳለብን አለማወቅ የፊትና  ሰበብ ነው። እውቀት የሚያዘው በእውቀት ከተካኑ ዑለማዎች (ምሁሮች) ሲሆን እነሱም ቁርአንና ሀዲስን በተገቢው መልኩ የሚረዱ የሃይማኖትን መሰረቶች
የሸሪዓን አላማና ፅንሰ ሐሳብ የሚያውቁ ሊሆኑ ይገባል፡፡
ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺟَﺎﺀَﻫُﻢْ ﺃَﻣْﺮٌ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺄَﻣْﻦِ ﺃَﻭِ ﺍﻟْﺨَﻮْﻑِ ﺃَﺫَﺍﻋُﻮﺍ ﺑِﻪِ ﻭَﻟَﻮْ
ﺭَﺩُّﻭﻩُ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝِ ﻭَﺇِﻟَﻰ ﺃُﻭﻟِﻲ ﺍﻟْﺄَﻣْﺮِ ﻣِﻨْﻬُﻢْ ﻟَﻌَﻠِﻤَﻪُ
َﻦﻳِﺬَّﻟﺍ ﻳَﺴْﺘَﻨْﺒِﻄُﻮﻧَﻪُ ﻣِﻨْﻬُﻢْ
‹‹ከጸጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላቸውም ጊዜ እርሱን ያጋንናሉ፡፡ ወደ መልክተኛውና ከእነርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ ዐዋቂዎቹ) በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር፡፡›› አል ኒሳእ 83
ﻓَﺎﺳْﺄَﻟُﻮﺍ ﺃَﻫْﻞَ ﺍﻟﺬِّﻛْﺮِ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﻟَﺎ ﺗَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ
‹‹የማታውቁም ብትሆኑ የእውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ›› አል ነህል 43 እውቀትን ዐሊም ካልሆነ ሰው መውሰድና መያዝ ከጥመት ምክንያቶች ውስጥ አንዳ መሆኑን ነብያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
ሲያስተምሩ እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ እውቀትን ከሰጣችሁ በኃላ መንጠቆን አይነጥቃችሁም ነገር
ግን የእውቀት ባለቤቶችን ከነእውቀታቸው በመግደል ይነጥቃችኋል ከዚያም መሀይም ሰዎች ይቀራሉ ሰው ስለዲን ይጠይቃቸዋል በሐሳባቸው (በግምት) ይመልሳሉ ራሳቸው ጠመው ሰው
ያጠማሉ፡፡” ይህ የቡኻሪ ዘገባ ሲሆን በሙስሊም ዘገባ ደግሞ “አላህ እውቀትን ከሰዎች ልብ መንጠቅን አይነጥቀውም ነገር ግንዑለማዎችን በመያዝ (በመግደል) እውቀቱን ያነሳዋል ምንም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ ሰዎች ጃሂሎችን መሪ አድርገው ያዙ ስለዲን ተጠየቁ ያለ እውቀት በመመለስ ጠመው አጠመሙ፡፡” እንደዚሁ እውቀትን ከቢድዓና ከስሜት ባለቤቶች መውሰድ
ከሙብተዲዕ ቡድኖች እውቀት መያዝ በሚያሳዩት ብልጭልጭ ነገር መታለል በማስታወቂያቸው መሸወድ መሸንገል አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ግልፅ የሆነው ሸይጣንም ብልጭልጭ ነገሮችን በማሳየትና በውሸት በመማል ነው ሰውን የሚያታልለው፡፡
ﻓَﻮَﺳْﻮَﺱَ ﻟَﻬُﻤَﺎ ﺍﻟﺸَّﻴْﻄَﺎﻥُ ﻟِﻴُﺒْﺪِﻱَ ﻟَﻬُﻤَﺎ ﻣَﺎ ﻭُﻭﺭِﻱَ
ﻋَﻨْﻬُﻤَﺎ ﻣِﻦْ ﺳَﻮْﺁﺗِﻬِﻤَﺎ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﻣَﺎ ﻧَﻬَﺎﻛُﻤَﺎ ﺭَﺑُّﻜُﻤَﺎ ﻋَﻦْ ﻫَﺬِﻩِ
ﺍﻟﺸَّﺠَﺮَﺓِ ﺇِﻟَّﺎ ﺃَﻥْ ﺗَﻜُﻮﻧَﺎ ﻣَﻠَﻜَﻴْﻦِ ﺃَﻭْ ﺗَﻜُﻮﻧَﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺨَﺎﻟِﺪِﻳﻦَ
ﻭَﻗَﺎﺳَﻤَﻬُﻤَﺎ ﺇِﻧِّﻲ ﻟَﻜُﻤَﺎ ﻟَﻤِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺻِﺤِﻴﻦَ
‹‹ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡ «ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ
አልከለከላችሁም» አላቸው፡፡ እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው፡፡›› አል አዕራፍ 2ዐ-21

Post a Comment

0 Comments