Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንድ ነው መንገዴ ግጥም


አንድ ነው መንገዴ

ዙርባውን ጀባ በል ሓጃህ እንዲወጣ
ሃሳቡ እንዲለቅህ ቀንዳም ሙክት አምጣ
በል ጎምበስበስ በል እኛ እንመርቅህ
የያዘህ አባዜ ጨርሶ እንዲለቅህ
አንችም “ዱስቱር” በይ ሸሁ ላሉት ነገር
ያሰብሽው ያለምሽው እንዲሆን ገር በገር
በማለት የሰው ሓቅ እየሰለቀጡ
የነቀፋቸውን እየገላመጡ 
     ስንት ጉድ አመጡ!
ዝም እንዴት ልበለው ይሄን አጭበርባሪ
በቀብር አምልኮ  ዓቂዳን ቀባሪ
ሱፊም ይሁን አሕባሽ ጠላት ነው ለሱና
ሁሉን አወግዛለሁ አላህ ያጽናኝና
የውስጤ መሰረት ተውሒዱ ነውና
         ተውሒዱን ሳይማር ዓቂዳን ሳያውቀው
          በ “ሰቢለላህ” ስም ከሱና  የራቀው 
         በቢድዓ ነቀርሳ  ውስጡ የማቀቀው
        ከተብለጉ ጋራ ከቶ እንዴት ልስማማ 
          በልቤ ተተክሎ  የዓቂዳ  ማማ
        ስጋ ደሜን ማርኮት የተውሒዱ ግርማ
የሴት የልጆችን ደም እያፈሰሰ 
ባልዋሉበት ፈርዶ ቀዬ እያስለቀሰ
ጂሃድ ነው ይለኛል በኢስላም ሲነግድ
የቀረውን አማኝ ለቅጣት ሲማግድ
ታድያ እንዴት ልላመድ ከተክፊሩ መስመር
መች ልብን ይስባል የኸዋሪጅ ቀመር
        ዘመናዊው ልማድ ውስጡን ካሰከረው
          የምእራቡ ባህል ልቡን ካሳወረው 
          ከክፉ ከቢድዓው ተደበላለቀው 
         ብሎ ከሚመክረኝ ሸሩ ከረቀቀው 
         እንዴት ልቀላቀል ከኢኽዋኑ ጎራ
         የሱናን ዓቂዳ ከማ ይሰብከው ጋራ
    አንድ ነው መንገዴ የልቤ ጎዳና
     በሰለፍ አረዳድ ቁርአንና ሱና 
     እለምናለሁኝ ራሕማንን  በጸና 
  በዚህ በውብ መንገድ ሁሌም እንድጸና።
አንድ ነው መንገዴ
ዙርባውን ጀባ በል ሓጃህ እንዲወጣ
ሃሳቡ እንዲለቅህ ቀንዳም ሙክት አምጣ
በል ጎምበስበስ በል እኛ እንመርቅህ
የያዘህ አባዜ ጨርሶ እንዲለቅህ
አንችም “ዱስቱር” በይ ሸሁ ላሉት ነገር
ያሰብሽው ያለምሽው እንዲሆን ገር በገር
በማለት የሰው ሓቅ እየሰለቀጡ
የነቀፋቸውን እየገላመጡ
ስንት ጉድ አመጡ!
ዝም እንዴት ልበለው ይሄን አጭበርባሪ
በቀብር አምልኮ ዓቂዳን ቀባሪ
ሱፊም ይሁን አሕባሽ ጠላት ነው ለሱና
ሁሉን አወግዛለሁ አላህ ያጽናኝና
የውስጤ መሰረት ተውሒዱ ነውና
ተውሒዱን ሳይማር ዓቂዳን ሳያውቀው
በ “ሰቢለላህ” ስም ከሱና የራቀው
በቢድዓ ነቀርሳ ውስጡ የማቀቀው
ከተብለጉ ጋራ ከቶ እንዴት ልስማማ
በልቤ ተተክሎ የዓቂዳ ማማ
ስጋ ደሜን ማርኮት የተውሒዱ ግርማ
የሴት የልጆችን ደም እያፈሰሰ
ባልዋሉበት ፈርዶ ቀዬ እያስለቀሰ
ጂሃድ ነው ይለኛል በኢስላም ሲነግድ
የቀረውን አማኝ ለቅጣት ሲማግድ
ታድያ እንዴት ልላመድ ከተክፊሩ መስመር
መች ልብን ይስባል የኸዋሪጅ ቀመር
ዘመናዊው ልማድ ውስጡን ካሰከረው
የምእራቡ ባህል ልቡን ካሳወረው
ከክፉ ከቢድዓው ተደበላለቀው
ብሎ ከሚመክረኝ ሸሩ ከረቀቀው
እንዴት ልቀላቀል ከኢኽዋኑ ጎራ
የሱናን ዓቂዳ ከማ ይሰብከው ጋራ
አንድ ነው መንገዴ የልቤ ጎዳና
በሰለፍ አረዳድ ቁርአንና ሱና
እለምናለሁኝ ራሕማንን በጸና
በዚህ በውብ መንገድ ሁሌም እንድጸና።