Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙዚቃ ♬

በወንድም ጀማል ነጋሽ 
☞[ሙዚቃ] ♬
አቡ አሚርና አቡማለክ አሽዓሪ እንዳስተላለፋት ነብያችን (ሰለላሁ
አለይሒ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
<< ከኔ ኡማ (ሕዝብ) መካከል ከሴቶች ጋር ነፀነትን (መቀላቀል)
፣ሐርን፣አልክሆል መጠጥንና፣የሙዚቃ መሳሪያዎችን የሚፈቅዱ
ሰዎች ይኖራሉ>> ቡኻሪ ዘግበውታል
ኢብኑ መስዑድ በአላህ እየማሉ ይህች የቁርአን አንቀፅ ሙዚቃን
(ዘፈን) እንደምትመለከት ይገልፁ ነበር፦
<< ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና
ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት፤አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ ።>> (ሱራ
ሉቅማን 6)
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም) የተለያዩ የሙዚቃ
መሳሪያዎችን የከለከሉ ሲሆን ዑለማዎችም በየጊዜው
የሚፈበረኩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በነብዩ ሐዲስ የሚጠቃለሉ
በመሆናቸው ከልክለዋል ።
እንዲሁም እንደ ኢብነል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) ያሉ
አንዳንድ አሊሞች እንደጠቀሱት እነዚህ ዘመናዊ የሙዚቃ
መሳሪያዎች ከኸምር የበለጠ ሊያሰክሩ ወይም በሰዎች ላይ
ትልቅ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ። ስለዚህ ክልከላው ይበልጥ
ይጠነክራል፣ኋጢዐቱም ይበልጥ ይከብዳል ። ሙዚቃ ስለ ፍቅርና
መሰል ጉዳዮች ሲሆን ደግሞ ይበልጥ ይከፋል ።
አንዳንድ አሊሞች እንደሚናገሩት ሙዚቃ ለዝሙት በር ይከፍታል
መንገድ ይጠርጋል ። ልብ ውስጥ ኒፋቅ (አመፅ) እና ሽርክ
ያሳድጋል ። በአሁኑ ሰአት ሙዚቃ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘና
ከመዝናኛ ዘዴዎች አንዱ ሆኖ በመቆጠር ላይ ይገኛል ። ሆኖም
ይህ ተቀባይነት ማግኘቱና ተወዳጅነቱ የኢስላምን ህግጋት
አይቀይርም፣ጉዳቱም አይቀርም፣ወጀልነቱም አይለወጥም ።
ስለዚህ ማንኛውም ሙስሊም ራሱን ከሙዚቃ ንክኪ ማራቅና
ነፍሱን ከጀሀነም እሳት መከላከል ይገባዋል ። በአሁኑ ሰዓት
ሙዚቃ የተለያዩ ሞባይሎች የጥሪ ድምፅ ሲሆን ይታያል ። ይህ
ደግሞ በሶላት ላይ ሳይቀር ሙስሊሞችን እየበጠበጠ ይገኛል ።
ስለሆነም ሁላችንም ሞባይሎቻችንና መጣቀሚያዎቻችንን
ከሙዚቃ ለማፅዳት መታገል ይገባናል ። ሀያሉ አላህ ይርዳን ።
1
በወንድም ጀማል ነጋሽ
☞[ሙዚቃ] ♬
አቡ አሚርና አቡማለክ አሽዓሪ እንዳስተላለፋት ነብያችን (ሰለላሁ
አለይሒ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
<< ከኔ ኡማ (ሕዝብ) መካከል ከሴቶች ጋር ነፀነትን (መቀላቀል)
፣ሐርን፣አልክሆል መጠጥንና፣የሙዚቃ መሳሪያዎችን የሚፈቅዱ
ሰዎች ይኖራሉ>> ቡኻሪ ዘግበውታል
ኢብኑ መስዑድ በአላህ እየማሉ ይህች የቁርአን አንቀፅ ሙዚቃን
(ዘፈን) እንደምትመለከት ይገልፁ ነበር፦
<< ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና
ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት፤አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ ።>> (ሱራ
ሉቅማን 6)
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም) የተለያዩ የሙዚቃ
መሳሪያዎችን የከለከሉ ሲሆን ዑለማዎችም በየጊዜው
የሚፈበረኩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በነብዩ ሐዲስ የሚጠቃለሉ
በመሆናቸው ከልክለዋል ።
እንዲሁም እንደ ኢብነል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) ያሉ
አንዳንድ አሊሞች እንደጠቀሱት እነዚህ ዘመናዊ የሙዚቃ
መሳሪያዎች ከኸምር የበለጠ ሊያሰክሩ ወይም በሰዎች ላይ
ትልቅ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ። ስለዚህ ክልከላው ይበልጥ
ይጠነክራል፣ኋጢዐቱም ይበልጥ ይከብዳል ። ሙዚቃ ስለ ፍቅርና
መሰል ጉዳዮች ሲሆን ደግሞ ይበልጥ ይከፋል ።
አንዳንድ አሊሞች እንደሚናገሩት ሙዚቃ ለዝሙት በር ይከፍታል
መንገድ ይጠርጋል ። ልብ ውስጥ ኒፋቅ (አመፅ) እና ሽርክ
ያሳድጋል ። በአሁኑ ሰአት ሙዚቃ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘና
ከመዝናኛ ዘዴዎች አንዱ ሆኖ በመቆጠር ላይ ይገኛል ። ሆኖም
ይህ ተቀባይነት ማግኘቱና ተወዳጅነቱ የኢስላምን ህግጋት
አይቀይርም፣ጉዳቱም አይቀርም፣ወጀልነቱም አይለወጥም ።
ስለዚህ ማንኛውም ሙስሊም ራሱን ከሙዚቃ ንክኪ ማራቅና
ነፍሱን ከጀሀነም እሳት መከላከል ይገባዋል ። በአሁኑ ሰዓት
ሙዚቃ የተለያዩ ሞባይሎች የጥሪ ድምፅ ሲሆን ይታያል ። ይህ
ደግሞ በሶላት ላይ ሳይቀር ሙስሊሞችን እየበጠበጠ ይገኛል ።
ስለሆነም ሁላችንም ሞባይሎቻችንና መጣቀሚያዎቻችንን
ከሙዚቃ ለማፅዳት መታገል ይገባናል ። ሀያሉ አላህ ይርዳን ።


Post a Comment

0 Comments