Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

~`~ ማንን ነው የወደድነው ? ~`~ ሙሐመድ ﷺ የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት ከመነሻ እስከ መድረሻ

‎~`~  ማንን ነው የወደድነው  ? ~`~  

         ሙሐመድ ﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
   ከመነሻ እስከ መድረሻ
                󾁇
   በፋራን ተራሮች መሃል በነዚያ ሰላማዊ በሆኑት ሸለቆዎች፣ በተባረከቿ ምድር  በመካ … ያ የሰው ልጆችን ልብ የገዛውና ያንጠለጠለው፤ የክብርና የታላቅነት መገለጫ የሆነው፤ የመጀመርያው የአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ መመለኪያ  ቦታ የሆነው ቤት ተገነባ።

   የሰው ልጆች በሙሉ መካን ይናፍቋታል። ከመካ ጋር የተያያዙ ከሰው ልጆች ህይወት ጋር የተቆራኙ ጥንታዊም፣ አሁንም ያለ፣ የወደፊትም ታሪክ አላቸውና።

   የድንቅ ታሪክ ባለቤት በመሆኗ ጠላት የሆናት እንኳን ሊረሳትም ችላ ሊላትም አይቻለውም።

   ወዳጆቿ  በናፍቆት እንደ ሚጓጉላት ሁሉ፤ ተፃራሪዎቿ ደግሞ በቅናትና ምቀኝነት ሌት ተቀን በቁጭት ያርሩላታል።

እንዴትስ አትታወስ    !
እንዴትስ አትናፈቅ     !
እንዴትስ ችላ ትባል  !

✔ የቀድሞዎቹን መፅሃፍት ያረጋገጠና የሻረ ወህይ የወረደባት፤

✔ የሰው ልጆችና የጋኔኖችም የበላይ የሆነ ምርጥ ፍጡር አለቃችን ተወልዶ ያደገባት፤

✔የመጨረሻው ክፍለ ዘመን ነቢይ የተላከባት ምድር ናት።

ሙሀመድ ﷺ
~ በብርሃን የተወለዱ
~ በብርሃን የኖሩ
~ ወደ ብርሃን የተጣሩ
~ የግልፅ ኣኩሪ ታሪክ ባለቤት

~ ከሺሆች አመታት በስተፊት ከተደገሰላትና ደረጃ በደረጃ አስደናቂ ታሪክ እየተደረገላት ከተዘጋጀችው መካ ምድር የተገኙ ታላቅ መሪ።
               
  ከዚህች የመለኮታዊ ራእይ መፍለቂያ ከሆነችውና የኢማን አየር ከሚሰራጭባት ሰላማዊዋ መንደር ተጠባቂው የምርጦች ምርጥ ሙሀመድ ﷺ ተወለዱ። 

   󾁇   󾁀󾁀  󾁀󾁀   󾁇

   የዛሬው ርእሳችን ታላቁ የሰው ልጆች አለቃ ከየት ተገኙ ፤ ወደዚህች ዓለም ብቅ ከማለታቸው በፊትስ ፈጣሪ ጌታችን አምላካችን አላህ ለእኚህ ወደፊት ተወልደው ኣድገውና ነቢይ የሚሆኑባትን ሀገርንም ሆነ እሳቸውን  በምን ዓይነት ቅድመ ዝግጅቶች እንዳመቻቸ እንመለከታለን።

       ክስተት 1
  የክቡሩ ነቢይ መነሻ ግንድ
  °````````````````````````````°
   የአመፀኞችና የክህደት መንደር ከነበረችው፤ ባእድ አምልኮና በሰው ልጆች ላይ በደሎች በሰፊው ከሚፈፀሙባት ክልል ከኢራቅ ምድር  ነቢዩ ኢብራሂም صلى الله عليه وسلم ከወንድማቸው ከሃራን ልጅ ከነቢዩ ሉጥ ጋር እና ውዷ ባለቤታቸውን እመቤት ሳራን አስከትለው ቀዬውን ለቅቀው ተሰደዱ። የአላህ ሰላትና ሰላም ይስፈንባቸው።

   በዚህም ጉዞ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ክቡር ወዳደረጋት የሻም ምድር (ወደ የዛሬዎቹ ሱሪያ፣ ኦርዶን፣ ሉብናን እና ፍልስጢን) ክልል ተጓዙ። 

   ኢብራሂም የተውሂድን ዓርማ እንዳነገቡ፣ ባእድ አምልኮትን የሚያወግዝና አንድ ብቸኛ ፈጣሪ ጌታን አላህን ብቻ አምልኩ የሚለውን መልእክት እንዳንፀባረቁ ለተወሰኑ ቀናት በመስር (በግብፅ) ምድርም ቆይታ አድርገው ነበር።

 ክስተት 2
ቀጣዩ ቀደር
°````````````°
   እዚያም አስደናቂው ሁለተኛው ቀደር ይፋ ሆነ ። ግሩም የአክብሮት ስጦታ ያጎታቸው ልጅ ለሆነችው  ለውዷ ባለቤታቸው ለሳራ ተለገሰ።

   ያ የወደፊቱን ክስተት መጠቆሚያ የሆነው ፣ የፈተናዎች ማለፊያ ውጤት ሽልማት ኣድርጎ አላህ ያመቻቸላቸው ስጦታ የነቢዩ ኢስማዒል  صلى الله عليه وسلم 
ወላዲት እናት ሃጀር ነበረች።

   በመጀመርያው የአላህ ቀደር ኢብራሂም ተወልደው ያደጉበትን ሀገር ኢራቅን ለቀው ወደ ሻም ተሰደዱ። 

  በሁለተኛው ክስተት መስር ማለይም ግብፅ ሃገር በገቡበት ከሃገረ ገዢው በደረሰባቸው ፈተና ባሸናፊነት በማለፋቸው ለፈተናው ሰበብ ለሆነችው የመጀመርያዋ ባልተቤታቸው የቤተ መንግስቱ ምርጥ ደንገጡር እንድትጎዳኛት ተሰጣት።

  ክስተት 3 
ቀጣዩ ቀደር
 °```````````°
   በቀጣዩ የአላህ ቀደር እመቤት ሳራ ለውዱ ፍቅረኛዋ ፣ ለህይወቷ አጋር፣ የተውሂድን አርማ አንግቦ በገባበት ሁሉ ላስከበራትና ቦታ ላስሰጣት፣ በሄደበት ከጎኑ ለሚያደርጋት ባለቤቷ አስገራሚ ድንቅ ስጦታ አቀረበች።

   በጣም ትወደዋለች፣ ትጓጓለታለች፣ እሱን ለማስደሰት የቻለችውን ሳትታክት ትፈፅማለች።

   የረዥም ግዜ የትዳር አጋሮቹ ኢብራሂምና ሳራ ወልደው የመሳም እድሉ ባይደርሳቸውም ወዳጅነታቸው የሚያስቀና ነበረ። 
ሳራ ለባሏ ሃጀርን ሸለመች  ❗

ማንም አያገባውም  !
የደካሞችንም ደካማ አስተያየት የሚቀበል ጤናማ ሰው የለምና።

󾔐 ምንኛ ያማረ ውድ ስጦታ 󾔐
      የኔን ላንተ እውነተኛ ፍቅር 

   የወደዱትን ጉድለቱን መሙላት ይሉሃልም ይኸ ነው።

   የተከበረችበትን ስጦታ፣ የተለገሳትን አጫዋች ሽልማት ለቁም ነገር አዋለች።

   ግዜው የጨዋታና በአጫዋች የሚዝናኑበት አይደለም።

   ግዜው በአገልጋይ ጉልበት እመቤት የሚሆኑበት አይደለም።

   ጊዜው የቁም ነገር ነው። ባለችዋ እድሜ መልካምን በማብዛት ጀነትን ለመሸመት የሚሯሯጡባት ናትና ባሏን አስደሰተች፤ የሃጀርንም ነፃነት በማወጅ በእህትነት ተቀብላ አጋርዋ አድርጋ ባሏን አካፈለቻት ።

   ኢብራሂም ሁለተኛ ሚስት አገኙ። ግንኙነቱም ተፈፀመ። ቀጣዩ ክስተት ብቅ ኣለ… ……

  ክስተት 4
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°
  
   አላሁ አዝዘ ወጀለ ከአንዱ ቀደር ወደ ሌላኛው እየነዳን… … 

________

        ሙሐመድ ﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ  ባለቤት 
ይቀጥላል… …
_______
 󾔧 احمد سيرة abufewzan
26 rabi'e al-awal 1436
17Jan14‎
~`~ ማንን ነው የወደድነው ? ~`~

ሳራ ለባሏ ሃጀርን ሸለመች
ማንም አያገባውም !
የደካሞችንም ደካማ አስተያየት የሚቀበል ጤናማ ሰው የለምና።
ምንኛ ያማረ ውድ ስጦታ
የኔን ላንተ እውነተኛ ፍቅር
የወደዱትን ጉድለቱን መሙላት ይሉሃልም ይኸ ነው።
የተከበረችበትን ስጦታ፣ የተለገሳትን አጫዋች ሽልማት ለቁም ነገር አዋለች።
ግዜው የጨዋታና በአጫዋች የሚዝናኑበት አይደለም።
ግዜው በአገልጋይ ጉልበት እመቤት የሚሆኑበት አይደለም።
ጊዜው የቁም ነገር ነው። ባለችዋ እድሜ መልካምን በማብዛት ጀነትን ለመሸመት የሚሯሯጡባት ናትና ባሏን አስደሰተች፤ የሃጀርንም ነፃነት በማወጅ በእህትነት ተቀብላ አጋርዋ አድርጋ ባሏን አካፈለቻት ።
ኢብራሂም ሁለተኛ ሚስት አገኙ። ግንኙነቱም ተፈፀመ። ቀጣዩ ክስተት ብቅ ኣለ… ……
ክስተት 4
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°
አላሁ አዝዘ ወጀለ ከአንዱ ቀደር ወደ ሌላኛው እየነዳን… …
________
ሙሐመድ ﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
ይቀጥላል… …
_______
احمد سيرة abufewzan
26 rabi'e al-awal 1436
17Jan14