Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዶክተር ፈውዛን አልፈውዛን ጥያቄ 2- ድራማና ዘፈኖች (የትምህርቱ አካል ሆነው) የሚሰጥባቸውን የክረምት ትምህርቶች (courses) እንዴት ይመለከቷቸዋል?

አዳዲስ አካሄዶችን በተመለከተ ለተጠየቁ ጥያቄዎች የተሰጠ ጠቃሚ ምላሽ
ዶክተር ፈውዛን አልፈውዛን
ጥያቄ 2- ድራማና ዘፈኖች (የትምህርቱ አካል ሆነው) የሚሰጥባቸውን የክረምት ትምህርቶች (courses) እንዴት ይመለከቷቸዋል?
መልስ/ ጥቅም የማይሰጡ ጎጅ የሆኑ ነገሮችን የመርከዙ ሀላፊዎች መከልከል አለባቸው፡፡ ቁርዓንን ሀዲስንና ፊቅህን የአረብኛ ቋንቋዎችን ሊያስተምራቸው ይገባል፡፡ በሌሎች ጉዳዬች (ተማሪዎችን) ከመጥመድ በነዚህ (ጠቃሚ በሆኑ) ጉዳዬች (ተማሪዎችን) መጥመዱ በቂ ነው፡፡ እንዲሁም (በተጨማሪ) ለዚህ አለም ሂዎታቸው የሚያስፈልጋቸውን አለማዊ ትምህርቶች (academic courses) ማስተማር፡፡ ለምሳሌ:- የአጻጻፍ ስልቶች፣ ሂሳብና ጠቃሚ የሆኑ የክህሎት (Technical Education) ትምህርቶችን ፡፡
በፕሮግራሞች (1) ውስጥ ተማሪዎችን ለማዝናናት በሚል (ሽፋን) አዝናኝ ነገሮችን (ሙዚቃ፣ ድራማና የመሳሰሉትን) ማስገባት ተገቢ አይደለም፡፡ ጥቅም የሚያገኙበትን ዋናውን የትምህርት ጊዜያቸውን ይጋፋል፡፡እንዴውም አንዳንዴ (ተማሪዎች) የመጡበትን ዓላማ ረስተው በማይጠቅም ነገር ተጠምደው የሚውሉበት አጋጣሚ አለ፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡ በድራማዎችና በዘፈኖች፡፡ (እነዚህ ነገሮች ደግሞ) ቀልድና ጨዋታ ብቻ ያዘሉ ናቸው፡፡ (ተማሪዎቻችንን በነዚህ ነገሮች ጠምዶ ማዋል) በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እየተላለፉ ያሉትን ቲያትሮችን እና ዘፈኖችን እንዲከታተሉ እያሰለጠናቸው መሆኑ ግልጽና ግልጽ ነው፡፡

1) ሸይኽ ፈውዛን "ኹጦቡል ሚንበርያ" በሚባለው ኪታባቸው (ሙጀለድ 3/ ገጽ 183-184) (ኢስላማዊ ዘፈንን በሚመለከት) የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
ከኪታባቸው የተወሰደው ንግግር በቀጥታ እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
“በእርሱ ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው፡ በሙስሊም ወጣቶች መካከል ተሰራጭቶ የሚገኘው በውስጡ የህብረት ዜማ ያቀፈ ካሴት ነው፡፡ (በተለምዶ) "አናሽደል ኢስላሚያ" ብለው ይጠሩታል፡፡ (ነገር ግን) ከዘፈን አይነቶች አንዱ ነው፡፡ አንዳንዴ ፈታኝ በሆነ ድምጽ (ተቀርጾ) እናገኘዋለን፡፡ ካሴት መሸጫ (ሱቆች) ከቁርዓን ካሴቶችና ዲናዊ ሙሀዶራዎች (ተርታ አሰልፈው) ሲሸጧቸው (ይስተዋላል)፡፡