Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰዒድ ቁጥብ እና እኩይ ስራዎቹ Part 2

ሰዒድ ቁጥብ እና እኩይ ስራዎቹ
…ከባለፈው የቀጠለ
-ሰዒድ ቁጥብ ስለ ዑሥማን ቢን አፋን(ረ.ዐ) ምን ይላል?
በአል ዓዳለቱል ኢጅቲማዒያህ ፊል ኢስላም (ገጽ 186-5ኛ ዕትም) ውስጥ ሰዒድ ቁጥብ የሚከተለውን ብሏል፡-
هذا التصوّر لحقيقة الحكم قد تغيّر شيئـًا ما بدون شك على عهد عثمان ، ولقد كان من سوء الطالع : أن تدرك الخلافة عثمان وهو شيخٌ كبير ، ضعفت عزيمته عن عزائم الإسلام ، وضعفت إرادته عن الصمود لكيد مروان وكيد أمية من ورائه .
فهم عثمان ـ يرحمه الله ـ أنّ كونه إمامـًا يمنحه حريّة التصرّف في مال المسلمين بالهبة والعطية؛ فكان رده في كثير من الأحيان على منتقديه في
<<وإلاّ ففيم كنت إمامـًا ؟>> هذه السيايسة
: كما يمنحه حرية أن يحمل بني معيط وبني أمية ـ من قرابته ـ على رقاب الناس ، وفيهم الحكم طريد رسول الله لمجرّد أنّ من حقه أن يكرم أهله ويبرهم ويرعاهم
‹‹የእውነተኛ አመራር ፅንሰ-ሀሳብ ያለምንም ጥርጥር በተወሰነ መልኩ በዑሥማን ዘመን ተቀይሯል፡፡ ይህ ደግሞ የሆነው ካለመታደል ነው፡፡ ኺላፋነቱ ወደ ዑሥማን የሄደው፤ እሱ በዕድሜ የገፋ፣ቁርጠኝነቱ ከእስልምና ውሳኔዎች አንጻር የደከሙ ሆነው፣ከኺላፋው በስተጀርባ የተፈጠሩትን የመርዋን እና የበኒ ዑመያህ ሴራን የማዘግየት ፍላጎት እያለው ሳለ ነበር፡፡ ዑሥማን(አላህ ይዘንለትና) ኢማምነቱን እንደሽልማት በመቁጠር የሙስለሞችን ገንዘብ በስጦታ መልክ በነጻነት አባክኗል፡፡በዚህ ፖለቲካዊ አካሄዱ በተለያዩ ቦታዎች ተተችቶ ‹‹ኢማምነቴ ለዚህ ካልሆነ ለመቼ ይሆናል›› የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በዚህ አመለካከቱ(ኢማምነቴ ስጦታ ነው) በመቀጠል ከቅርብ ዘመዶቹ በኒ ሙዓይጥንና በኒ ዑመያህ በመሾም በህዝብ ትካሻ ላይ ጭኗል፡፡ ከነርሱ ውስጥም በነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ) የተጠላው አል-ሀኪም(አምር ቢን አል-አስ) ይገኛል፡፡ ይህን ሁሉ የሰራበት ብቸኛ ምክንያት ለቤተሰቦቹ ቸር፣ደግ ለመሆንና እነርሱን ለመንከባከብ ነው፡፡››
በአል ዓዳለቱል ኢጅቲማዒያህ ፊል ኢስላም (ገጽ 189-5ኛ ዕትም፣ ገጽ 160-161 6ኛ ዕትም) ውስጥ ሰዒድ ቁጥብ በዑሥማን ላይ ቀጥፏል፡-
{وأخيرا ثارت الثائرة على عثمان واختلط فيها الحق بالباطل والخير بالشر ولكن لا بد لمن ينظر إلى الأمور بعين الإسلام ويستشعر الأمور بروح الإسلام أن يقرر أن تلك الثورة في عمومها كانت أقرب إلى روح الإسلام واتجاهه من موقف عثمان,أو بالأدق من موقف مروان ومن ورائه بنو أمية}
‹‹በመጨረሻም በውስጧ ሀቅና ባጢል፣ኸይርና ሸር የተደባለቀባት የሆነች የአመጽ አብዮት በዑሥማን ላይ ተነሳች፡፡ ነግር ግን ጉዳዩን(አብዮቱን) በኢስላማዊ ዕይታ የሚመለከትና በኢስላማዊ መንፈስ የሚረዳ ሰው ይህች አብዮት በጥቅሏ ከዑሥማን አቋም ይልቅ ለኢስላም መንፈስና አስተምህሮ የቀረበች ነበረች ወደሚለው ድምዳሜ ይደርሳል፡፡››
-አሁን ደግሞ ሰዒድ ቁጥብ የገለጸውን ዑሥማን ትተን፤ትክክለኛ ኢስላማዊ መዛግብት ስለኸሊፋው ዑሥማን(ረ.ዐ) የፃፉትን በጣም በጥቂቱ እናውራ፡-
1. በጀነት ከተመሰከረላቸው አስር ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ (ቲርሚዚ፣ኢማም አህመድና ሌሎችም)
2. ዑሥማን የነቢዩን(ሶ.ዐ.ወ) ሁለት ልጆች በማግባት አማችነትን ያገኘ ነው፡፡ ነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ) ሶስተኛ በነበራቸው ይድሩት እንደነበር የተናገሩለትም ሰው ነው፡፡
3. ረሱል(ሶ.ዐ.ወ) አሉ፣‹‹ዑሥማን ከነሚስቱ ከሉጥ(ዐ.ሰ) ቀጥሎ ለአላህ ሲል የቤቱን ምቾት የተወ ሰው ነው፡፡››
4. ዑሥማን መላኢኮች ያፍሩታል(ሃያ ያደርጉት ነበር)፡፡
5. ቢእር ሩማ የተባለች መጠጥ ምንጭ በመዲና ነበረች፡፡ ሙሃጅሮች የመዲና ውሃ አልተመቻቸውም፡፡ መዲና ውስጥ የሚገኝ ውሃ ጣፋጭ(ለመጠጥ የሚሆን) አልነበረም፡፡ ቢእር ሩማን ገዝቶ ለሙስሊሞች በማድረግ ጀነትን የሚከጅል ማን ነው ሲሉ ነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ) ጠየቁ፡፡(ሶህሂ አነሳዒ ሊልአልባኒ/766/) በቡኻሪ /2778/ የቢእር ሩማን ምንጭ ቆፍሮ ያዘጋጀ ጀነት አለው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ ሩማ የተባለችው ይህቺ ምንጭ ከበኒ ጊፋር ለሆነ ሰው ሀብት ነበረች፡፡ እሱም በእፍኝ ምግብ ውሃውን እየሸጠ ይተዳደር ነበር፡፡ በጀነት ምንጭ ትሸጣታለህን(ትለውጣታለህን)ብለው ነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ) ጠየቁት፡፡ እሱም ለኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ ሌላ ሀብት(መተዳደሪያ)የለንም ብሎ መለሰ፡፡ ይህ ጉዳይ ለዑሥማን እንደደረሰው፣35 ሺህ ዲርሃም ገዛትና ወደ ነቢዩ መጥቶ ለሰውየው ያደረከውን ለኔ ታደርግልኛልህን ብሎ ጠየቀ፡፡እሷቸው አዎ አደርግልሃለሁ፡፡ ዑሥማንም በርግጥ ምንጯን ለሙስሊሞች በሰደቃ መልክ ሰጥታቻለሁ አለ፡፡ ዑሥማን(ረ.ዐ) ምንጯን ለሀብታሙም፣ ለድሃውም፣ ለመንገደኛውም ሰደቃ አደረጋት፡፡ (ፈትሁል ባሪ 5/408)
6. የተቡክ ዘመቻ ጊዜ ለጀይሹል ዑስራ(ለሰራዊቶቹ) ሙሉ ስንቅና ትጥቅ ያዘጋጀ ሰው የጀነት መሆኑን ነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ) ሲገልጹ ዑሥማን የተሟላ ትጥቅና ስንቅ አቀረበ፡፡ (ሱነን ቲርሚዚ /3700-3702/ ኢብኑ ሻሀብ አዙህሪ/ታቢዒ)፡፡ ዑሥማን 940 ግመል፣60 ፈረስ ለግሷል፡፡ ወደነቢዩ በመምጣት ከፊት ለፊታቸው 10000 ዲናር አፈሰሰ(አቀረበ)፡፡ ነቢዩ በደስታ ዲናሩን እያገላበጡ ‹ዑሥማን ከአሁን በኋላ የሚሰራው ስራ ምንም አይጎዳውም› በማለት ደጋግመው ተናገሩ፡፡
7. ኢብን አባስ ስለዑሥማን ቸርነትና አዛኝነት እንዲህ አለ፡-‹‹በኸሊፋው አቡበከር ዘመን ሃይለኛ ድርቅ ተከሰተ፡፡ የተቸገሩ ሰዎች ወደ አቡበከር በመምጣት ሰማይ ዝናቧን ያዘች፣ምድርም አላበቀለችም፣ ሰዎችም በብርቱ መካር ውስጥ ናቸው ብለው ስሞታ አቀረቡ፡፡ ኸሊፋው አቡበክርም ታገሱ፣ኢንሻአለህ ይህን ምሽት ሳታመሹ ቸሩ አላህ ይህን ችግር ያስወግድላችኋል፡፡›› ኢብን አባስም በመቀጠል እንዲህ አለ፡ ‹ብዙ ሳንቆይ የዑሥማን ሰራተኞች ከሻም በ100 ግመል ስንዴ(ምግብ) ጭነው መጡ፡፡ ሰዎችም(ነጋዴዎች) ወዲያው ዑሥማን በር ተሰበሰቡና በሩን ቆረቆሩ፡፡ ዑሥማንም ከተወሰኑ ሰዎች ጋር ከቤቱ ወጥቶ ምን እንደፈለጉ ጠየቃቸው፡፡ እንደምታውቀው
ሰዎች በክፉ የድርቅ መከራ ላይ ናቸው፡፡ አንተ ዘንድ ምግብ የመጣ መሆኑን አውቀናል፡፡ ስለዚህ ለሙስሊም ችግረኞች በቅናሽ እንቸረችርላቸው ዘንድ ብትሸጥልን ብለው ጠየቁት፡፡ ግቡና ግዙ አለ፡፡ ከገቡ በኋላ ዑሥማን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡-እናንተ ነጋዴዎች ሆይ ምን ያህል ታተርፉኛላችሁ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ አስር ዲርሃም ያወጣህበትን አሥራ ሁለት አድርገን እንገዛሃለን አሉት፡፡ በርግጥ ከናንተ የበለጠ የጨመረልኝ አለ አለ፡፡ መዲና ውስጥ ከኛ ውጭ የቀረ አንድም ነጋዴ የለም፡፡ ማን ጨመረልህ አሉት፡፡ የላቀ የሆነው አላህ አንዱን ዲርሃም በአስር ሊገዛኝ ቃል ገብቶልኛል፣እናንተ ከዚህ በላይ ልትጨምሩልኝ ትችላላችሁን? ይህንን እንኳ እኛ አንችልም አሉት፡፡ *ዑሥማንም ይህን ምግብ ለተቸገሩ ሙስሊሞች ሰደቃ ማድረጌን አላህን ምስክሬ ነው፡፡›› (ተይሲር አል ከሪም አል መናን ፊ ሲረቲ ዑሥማን ቢን አፋን(ረ.ዐ)፣ ዶክተር ዓሊ መሐመድ አሱላቢ)
አንተ ወንድሜ ሆይ! እኔ ዑሥማንን ሳነውር ብትሰማኝ ዝም ትለኝ ይሆን? እረ በፍፁም፡፡ ታዲያ ሰዒድ ቁጥብ፡- ዑሥማን ቁርጠኝነት የሌለው፣ አቅሙ የደከመ፣ ያረጀ ስለነበር ለኺላፋነት አይገባውም ነበር ሲል ምን ተሰማህ? ሰዒድ ቁጥብ አሁንም፡- ዑሥማን ኢማምነቱን እንደስጦታ በመቁጠር የበይተል ማልን ንብረት አባክኗል ሲል ምን ትላለህ? ከላይ እናደነበብከው ዑሥማን ያለው ሀብት ተዝቆ የማያልቅ እንደነበር ነው፣አይደለም የሰው ሊነካ፡፡ ሰዒድ ቁጥብ ደገመ ዑሥማን፡- የቅርብ ዘመዶቹን ያለህዝብ ፍላጎት በህዝብ ትካሻ ላይ ጭኗል ማለቱን እንዴት ታየዋለህ? ሰዒድ ቁጥብ አልጨረሰም፡- በዑሥማን ላይ የተደረገው አብዮት(አመጽ) ኢስላማዊ መንፈስ ነበረው እያለ የዑሥማንን ገዳዮች ሲያወድስ አልተናደድክም? ሰዒድ ቁጥብ፡- አብዮቱን በኢስላማዊ መንፈስ እንድትመለከተው ጋብዟሃል፡፡ እስኪ አንተ በኢስላማዊ ዕይታና መንፈስ ተመልከትለትና በዑሥማን ላይ የተናገርከው እውነት ወይም ሀሰት ነው ብለህ መልስለት፡፡ እኔ በበኩሌ ስለዑሥማን የጻፈው ሀሰት እንደሆነ አምኜበት መልሴን በጽሁፍ እንደምታዩት ጽፌያለሁ፡፡
በባለፈው ጽሁፌ ብዙዎች ደስ እንደተሰኙ በአስተያየታቸው ገልጸዋል፡፡ ባለማወቅ ይህን ሰው ሲከተሉና ሲያስከትሉ እንደነበር፤አሁን ግን ማንነቱን አውቀው ከርሱ እኩይ ሥራዎችና ተግባሮች እንደሚርቁ አያይዘው ተናግረዋል፡፡ ከነርሱ መካከል ጥቂቶቹ ደግሞ በዑሥማንም ሆነ በሌሎች ላይ በስህተት ድንበር ማለፉን አምነው፤ ጥሩ ሥራዎችን ግን ልንከተል ይገባል የሚል አስተያየት አቅርበዋል፡፡ የዚህ አስተያየት ባለቤት የሆኑ ሰዎችን የምንጠይቀው ‹‹ቁርአንና ሐዲሥ(በታላላቅ የሱና ዓሊሞች የተጻፉ መጽሀፍት) አለቀባችሁ እንዴ ብለን ነው?›› አዎን እንደማይሉ እርግጠኛ ሆነን ‹‹ታድያ ሰዒድ ቁጥብ ላይ መንጠልጠል ምን የሚሉት ነው?›› ፍሬን የለለው መኪና ላይ መውጣት የሚፈልግ የለም፡፡ ሰዒድ ቁጥብ ፍሬን እንደለለው መኪና ነው፡፡ ሰዒድ ቁጥብም መልካም ሥራ ይኖረዋል፡፡ ግን ጥሩውን ከመጥፎ የምትለየው በየትኛው ዕውቀትህ ነው? ከስሜት ሰዎች(ሙብተዲዎች) መማር እንደማይቻል ብዙ መረጃዎች አሉ፡፡ ለዛሬ ሁለቱን ብቻ ጀባ ብያለሁ፡፡ ---//ጃቢር ኢብኑ አብዲላህ እንደዘገው ‹‹ ዑመር ኢብኑል ከጧብ አንድ ጊዜ ከመፅህፍ ባለቤቶች ያገኘውን መፅሀፍ ወደ ነብዩ ይዞ መጣ፡፡ ነብዩ(ሶ.ዐ.ወ) አነበቡትና በጣም ተቆጡ፡፡‹‹አንተ የኸጧብ ልጅ ሆይ ‹በዕምነታችሁ› የዋለላችሁ ናችሁን?! ነፍሴ በእጅ በሆነው ይሁንብኝ ንፅሁና አብሪ በሆነች መንገድ ነው የመጣኋችሁ፡፡ አህለል ኪታቦችን አትጠይቋቸው፡፡ ምክንያቱም እውነት ነግረዋችሁ ልታስተባብሉት ትችላላችሁ ወይም ውሸት ነግረዋችሁ እውነት ነው ብላችሁ ልትቀበሉት ትችላላችሁ፡፡ ሙሳ በህይወት በነበር ኖሮ እኔን ከመከተል ውጭ ሌላ አማራጭ አይኖረውም ነበር፡፡›› (ኢማሙ አህመድ /14736/ እና ሌሎችም ዘግበውታል፣ ኢማሙል አልባኒም ሐዲሡን አል ኢርዋእ/1589/ የተባለው ኪታባቸው ላይ ሀሰን ብለውታል) //
ተጨማሪ መረጃ በኢማሙ አህመድ ኢብን ሐንበል(ሲየር አዕላሙኑበላእ፣11/231) እንዲህ ይላሉ፡-‹‹ከስሜት ባለቤቶች(ከሙብተዲዎች) ጥቂትም ይሁን ብዙ መመዝገባችሁን(መቅሰማችሁን) ተጠንቀቁ፡፡ የፋና እና የሱና ባለቤቶችን ግን አጥብቃችሁ ያዙ(ከነርሱ ቅሰሙ)፡፡››
ተውራትና ኢንጅል(ከአላህ የተወረዱ) በውስጣቸው ብዙ ሐቅ እንዳለ እያወቁ ረሱል(ሶ.ዐ.ወ) እነርሱን ማንበብ ከልከለዋል፡፡ *የሰዒድ ቁጥብ ኪታቦች ይቅርና፡፡
አንድ ሹብሃ ሲወድቅ ሌላ ሹብሃ ማምጣት የሰው ልጅ ባህሪው ነው፡፡ እዚህ ላይ የተጠቀሱት መረጃዎች በኔ እምነት ለሐቅ ፈላጊ ከበቂ በላይ ናቸው፡፡ እንግዲህ መጥፎውን ጥለን ጥሩውን ብንማር የሚባል ነገር እንደሌለ ከመረጃዎች አይተናል፡፡ እዚህ ላይ የሚቀርብ ሹብሃ አለ፡፡ አቡ ሁረይራ እንኳ ከሸይጣን ተምሮ የለም እንዴ ይሉሃል፡፡ አቡ ሁረይራ ወደ ረሱል ሄዶ እንደዚህ ዓይነት ሰው ይህን ትምህርት አስተማረኝ ሲላቸው፣ ትምህርቱ ትክክል ነው እሱ ግን ውሸተም ነው አሉት፡፡ አንተ መጥፎውንና ጥሩውን ለመለየት በቂ ዕውቀት ያለህ ይመስልሃል? አላህ ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይምራን፡፡
ሌሎቹ ደግሞ ምን አሉ መሰላችሁ ‹‹ የዚህ ዓይነት ከፋፋይ ጉዳይ እያነሳችሁ አትከፋፍሉ››፡፡ ሐቁም እየወጣ ወደኋላ ማፈግፈግ ምን የሚሉት ነው? ከሰዒድ ቁጥብ ጋር ላንከዳህ ላትከዳን ተባብለን ቃል የገባን ይመስላል፡፡ ተጋብተናል እንዴ? እኔ ምን አውቃለሁ አልሰማሁም፡፡ በመስጅድ ውስጥ ስለትራፊክ(ስለኤች አይ ቪ) አደጋ የሚነገረው ህብረተሰቡን ከሞት ለመታደግ አይደል? ያውም መኪና አንድ ጊዜ ይገላል እንጂ የቀብር ጥያቄ ሆነ አይመጣ፡፡ ስለአኺራ አደጋ ሲነገርን ለምን እንሸሻለን? እኛ የምንፈልገው ምንድን ነው? ሳናውቅ ተከትለን አስከተልን፡፡ አሁን አወቅን፡፡ በቃ ከርሱ ጋር እንፋታ፡፡ ሰው ከሚወደው ሰው ጋር ነው የሚቀሰቀሰው ተብሏል፡፡ እኔ ከርሱ ጋር ነው መቀስቀስ የምፈልገው የሚል ሰው ካለ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት፡፡ ምን ይደረጋል በጉልበት አይሆን፡፡ አንዱ ምን አለኝ መሰላችሁ ‹‹በምድር ላይ እንደ ቀርዳዊ የምወደው ሰው የለም››፡፡ ምን ዓይነት ዕብደት(አቅልን መሳት)ነው? ‹‹እኔን ከራሱ አስበልጦ ያለወደደኝ ሰው አላመነም›› አሉ ነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ)፡፡ ይህ ወንድሜ ደግሞ ለነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ) የሚገባውን ውዴታ ለቀርዳዊ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡
ተጨማሪ ረድ የተደረጉ ስራዎቹ፡-
-ኢስላማዊ ማህበረሰብን ያከፍራል(ከእስልምና ሐይማኖት ውጭ ያደርጋል) (ዚላሉል ቁርአን፣4/2122፣3/1634፣2/1057፣4/2009)
-ሐዲሥ አል አሃድ በአቂዳዊ ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት የላቸውም ይላል (ዚላሉል ቁርአን 6/4008)
-በነቢያቶችና በህዝባቸው መካከል የነበረው ልዩነት በተውሂደል አል ኡሉሂያ ሳይሆን በተውሂደል ሩቡቢያ ነበር ይላል(ዚላሉል ቁርአን 4/1846)
-እስልምና ከክርስትናና ከኮሚኒዝም ጋር ተዋህዶ የተገኘ ነው(አል ማዕረካ አል ኢስላሚያ-ገጽ 61)
-ቁርአንን በሙዚቃ፣በዜማ በነሺዳ ይፈስራል(አዚላል 6/3404፣6/3811፣6/3956፣5/3018)
-ወጣቶችን በሙስሊም መንግስት ላይ አብዮትና መፈንቅለ መንግስት እንዲያካሂዱ ያንጻል(አል ዓዳላ አል ኢጅቲማዒያህ 160 እና 210፣አዚላል 3/1451)
-ዩሱፍ አል ቀርዳዊ (አውለውያት አል ሀረከቱል ኢስላሚያ 110) የሰዒድ ቁጥብ ኪታቦች ህብረተሰቡን በሰፊው እንደሚያከፍሩ ይናገራል፡፡
አላህ ሆይ! ንግግሩህን ሰምተው ቅኑን ከተከተሉት ሰዎች ጋር አድርገን፡፡ ኣሚን፡፡

Post a Comment

0 Comments