Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰዒድ ቁጥብ እና እኩይ ስራዎቹ Part 1

ሰዒድ ቁጥብ እና እኩይ ስራዎቹ
ሰዒድ ቁጥብ ከፈፀማቸው ስህተቶች መካከል የተወሰኑትን ከዚህ በታች አንብብ፡፡ ታድያ ልብ አድርግ፡፡ እኔና አንተ ረድ የማድረግ አቅሙ ኖሮን አይደለም ስለርሱ የምንጽፈው፡፡ እኛ ታላላቅ የሱና ዓሊሞች(ሁሉም የሚስማማባቸውን) ያወሩትን ወይም የፃፉትን ሳንቀንስ ሳንጨምር እናቀርባለን እንጂ፡፡ የምናገኘው ፋይዳ ባለማወቅ የሚከተሉ እና ሥራውን ህያው አድርገው የሚንቀሳቀሱ ሙስሊም ወንድሞቻችንን ከዚህ ሰው ጥፋት እንታደጋለን፡፡ ሌላው ፋይዳ በሥራችን አጅር እናገኝበት ይሆናል፤በአላህ ፍቃድ፡፡ አንተ ማን ነህ እርሱን የምትተቸው የሚባል ነገር(ሐቅን ላለመቀበል የሚቀርብ ሹብሃ) ተቀባይነት የለውም፡፡ እኔ ማንም አይደለሁም፡፡ እኔ የሰማሁትንና ያነበብኩትን የመናገር ግዴታ ስላለብኝ ነው የምፅፈው፡፡ ባታነሳው ምን ይጎዳሃል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል-ኡማውን ከምትከፋፍል፡፡ የኡማው አንድነት በተውሂድ ላይ ሲሆን ብቻ ነው ስለአንድነቱ የምጨነቀው፡፡ አለበለዚያ ለውሸት አንድነት፣የአላህ እና የመልዕክተኛውን ትዕዛዝ ላልጠበቀ አንድነት ግድ የለኝም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አንድነት (በጭቃ ላይ እንደተሰራ ቤት) መቼም ቢሁን እውን አይሆንም(ወላሂ ብዬ እምላለሁ)፡፡ ኡማውን አትከፋፍሉ የሚሉ ሰዎች በጀርባ የራሳቸውን የግል ጥቅም ለማስጠበቅ እንጂ የዚህ ኡማ መለያየት እንቅልፍ አሳጥቷቸው አይደለም፡፡ በዚህ ዘመን ለየዋሆች ቦታ የለም፡፡ ንቃ! ንቃ! ንቃ! ሰውዬው አባትህ ወይም ወንድምህ ይመስል ሽንጥህን ገትረህ አትከራከርለት፡፡ ለአባትህ ከሆነ ተከራከርለት የሚልም አልወጣኝም፡፡
………………………………
በዓሊሞች የተተቹ(ኢብን ባዝ፣ዑሠይሚን፣አልባኒ፣አሉ ሸይኽ እና ሌሎችም)የሰዒድ ቁጥብ ስህተቶች ፡-

1. የሳዑዲ አረቢያ ሙፍቲ(አሉ ሸይኽ) ተጠየቁ ‹‹ አንድ ሰው ሙዓዊያህንና የርሱ ጓደኛ አምር ቢን አል-አስን ወደ ውሸት፣ማታለል፣ትዕቢትና ጉቦ የተዘነበሉ፤ዓሊ ግን ለዚህ ተግባር እጅ አልሰጠም ነበር፤በዚህ ምክንያት የእነርሱ(የእነዓሊ) መተካት እና የርሱ(የእነሙዓዊያህ)መውደቅ አያስደንቅም ነበር ማለትን በተመለከተ የርሰዎ ዕይታ ምንድን ነው?›› ‹‹ይህ የወጣለት የባጢል ሰው ወይም የተረገመ አይሁድ ንግግር መሆን አለበት፡፡ የአላህ መልዕክተኛ(ሶ.ዐ.ወ) አምር ቢን አል-አስ የጀነት መሆኑን መስክረዋል፡፡ ሙዓዊያህ ደግሞ ከተከበሩ የነቢዩ ጓደኞች(ረ.ዐ) መካከል ነው፡፡ ሙስሊም እነዚህን ሰዎች ሊጠረጥር አይገባም፡፡ እነርሱ ሊተቹበት የሚያስችል ሥራ አልሰሩም፡፡ ስለዚህ ስለነሱ የሚባለው ነገር በሙሉ ግልጽ ፈጠራ ላይ የተመሰረተ እና በጉዳዩ ብዙዎችን ለማሳሳት የታሰበ ነው፡፡ ጥበቃ ከአላህ ነው፡፡ ይህን ንግግር ግልጽ ንፍቅና ካለበት ሰው እንጂ ከሌላ ሊሆን አይችልም፡፡››
………………………………
2. አላህ ሙሳን አናገረው የሚለውን የቁርአን አንቀጽ በተመለከተ ያለውን እንመልከት፡-
{وناديناه من جانب الطور الايمن}
በፊ ዚላሊል ቁርአን (4/2313) ፡-‹‹ ይህ ንግግር እንዴት እንደነበርና ሙሳ እንዴት እንደተረዳው እኛ አናውቅም፡፡ ጆሮዎች ሊሰሙት የሚችል ድምጽ ነበር…ወይም ፍጡሮች ሰምተውት ነበር የሚለውን እኛ አናውቅም፡፡ አላህ ንግግሩ ይሰማ ዘንድ ሙሳን እንዴት አድርጎ እንዳዘጋጀው አናውቅም፡፡ መከሰቱን እናምናለን፡፡ አላህ ካሉት ብዙ አማራጭ የመግባቢያ መንገዶቹ አንዱን በመጠቀም ፍጡራኑን ማናገር አይከብደውም፡፡›› ይላል ሰዒድ ቁጥብ፡፡ በሌላ ቦታ ላይ (4/2331)፡- ‹‹ስለዚህ የዚህን ጥሪ ምንጭ፣አቅጣጫ፣ቅርፅ፣ዓይነት እና ሙሳ ሰማው ወይም አገኘው የሚለውን አናውቅም፡፡››
እዚህ ላይ መግባባት ያለብን እነዚህ ንግግሮች ያለጭቅጭቅ ድንበር ያለፉ መሆናቸውን ነው፡፡ ‹እርሱ አላለም› እና ‹ቢልም ችግር የለውም› የሚሉት አገላለጾች የተለያዩ ናቸው፡፡ ‹እርሱ አላለም የሚሉ› ‹ቢልም ችግር የለውም› ከሚሉ ችግሩን ለመቀበል በጣም የቀረቡ ናቸው፡፡ ቢያንስ የችግሩን አስከፊነት ተረድተዋል፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት ማለቱን የሚያረጋግጡ ተጨባጭ መረጃዎችን ብቻ ነው፡፡ እነዚያኞቹ ግን ችግሩን አቅለው ስላዩት መረጃ ቢመጣም አይቀበሉም፡፡ እነርሱ በሰውዬው ፍቅር ድባቅ የተመቱ ናቸውና፡፡
………………………………
3. ‹አላህ ከአርሹ በላይ ነው፡፡› የሚለውን የቁርአን መልዕክት ነቢዩ(ሶ.ዐ.ወ) ከነጓደኞቻቸው ከተረዱት ውጭ የሆነ ሌላ መልዕክት ይዞ እናገኘዋለን-በሰዒድ ቁጥብ ሥራ ውስጥ፡፡ በፊ ዚላሊል ቁርአን(4/2328-6/3408-12ኛ ዕትም፣1406 ሂጅራ ፣ዳሩል ዒልም) ውስጥ ‹‹ ‹አላህ ከአርሹ በላይ ነው› የሚለውን አንቀጽ በተመለከተ፤እኛ ማለት እንችላለን /ይህ አንቀጽ አላህ ከፍጡራኑ የበለጠ(በክብር እና ደረጃ)መሆኑን የሚያመለክት እንጂ አላህ ቦታ ይይዛል ለማለት አይደለም/፡፡››
‹አላህ ከአርሽ በላይ ነው› የሚለው መልዕክት ሁሉም የተወረዱ መጽሀፍት እና የተላኩ መልዕክተኞች ‹አላህ በአካል ከዙፋኑ በላይ› እንደሆነ አስተምረዋል፡፡ የጀህሚያህ እና የሙዕተዚላህ መከሰት ድረስ በዚሁ ግንዘቤ ቀጥሏል፡፡ እነርሱ ከመጡ በኋላ ግን የአላህን ከአርሽ በላይ መሆን እና የቁርአንን የአላህ ቃል መሆን አስተባበሉ፡፡ ሰለፎችም ይህን ተከትሎ የዚህን አመለካከት መሪዎች እና ተከታዮች ካፊር(ካህዲያን) በማለት ፈረጁ፡፡
………………………………
እንደማጠቃለያ፡- ፉቅሃዎች ሰዒድ ቁጥብን በተመለከተ ይህን ይላሉ ‹‹ችግሩ ሰዒድ ቁጥብ ጋር አይደለም፡፡ እርሱ ስለሞተ የርሱ ጉዳይ በርሱና በአላህ መካከል ይቀራል፡፡ አላህ እንዲምረው እንክጅላለን፡፡ ችግሩ ያለው እሱን ‹የቅን መንገድ ኢማም› እያሉ ከሚጠሩት ተከታዮቹ ላይ ነው፡፡ እንዲሁም ከሌኒን ማርክዚም፣ከሮማን ካቶሊክ እና ከምዕራባዊያን የፍለስፍና አስተሳሰቦች በመውሰድ የሰራውን የሥራ ውጤቶቹን ለህብረተሰቡ እያስተላለፉ(እያዛመቱ) ካሉት ተከታዮቹ ላይ ነው፡፡ ችግሩን የባሰ የሚያደርገው ደግሞ ትክክል ያልሆኑ ሥራዎቹ ላይ ረድ(ትችት) ሲደረግ መከላከላቸው ነው፡፡ የሰውዬውን አብዮታዊ የሆኑ አመለካከቶቹን በህብረተሰቡ ላይ ለማስረጽ ቀንና ሌሊት የሚደክሙት ችግሮቹ ግልጽ እንዳይወጡ መንገዱን የዘጉ ናቸው፡፡››
ለሰውየው ወዳጆች ከላይ የተዘረዘሩት መረጃዎች በቂ እንዳልሆኑ በደንብ አውቃለሁ፡፡
………………………………
አላህ ለሐቅ የምንበረከክ ያድርግን!!

Post a Comment

0 Comments