Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ባለትዳሮችን ማማከርና በትዳር ጉዳይ ላይ ጣልቃ ገብነት እስከየት ?

‎.
ባለትዳሮችን ማማከርና በትዳር ጉዳይ ላይ ጣልቃ ገብነት
እስከየት   ?
 
   ትዳር 
በባልና ሚስት መካከል የሚደረግ የጋራ ስምምነትና መቻቻል ላይ የተመሰረተ ውልና ሂደት ነው ። እንዲሁም በውስጡ በርካታ ሚስጢሮችን ያቀፈ ህይወትም ነው።

~ በዚህም ሂደት ለየት ያለ የህይወት መስመር ይዘረጋል።

~ ወንዱም ሆነ ሴቷ በየትኛውም ፕሮጀክት ሊያስገኙት የማይችሉትን ጥቅሞች ያተርፉበታል።

በትዳር
~ ሰዋዊ  ወይም ስጋዊ ስሜታቸውን በሃላል ያረኩበታል። ገላ ሰውነታቸውን እንዲሁም አዕምሯቸውን ያነቃቁበታል ያሳርፉበታል።

ይህንን ታላቅ ልገሳም
አላህ አዝዘ ወጀልለ በአል-አዕራፍ ምዕራፍ ቁጥር 189 በሚቀጥለው መልኩ ይገልፅልናል 

« هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ مِنْ نَفْسٍ وَاحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا…… » 

الأعراف: 189

« እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከኣደም) የፈጠራችሁ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው። … »

ይላል

በሌላ በኩል ከትዳር
~ የሚወዱትን የሚናፍቁትን የአይን ማረፍያ፣ የልብ መርጊያ ፍቅረኛ ወዳጅ በፍቁድ መንገድ ያገኙበታል።

ብሎም በትዳር
~ ዝርያ ይቀጥሉበታል፣ አይናቸውን በአይናቸው በማየት የአብራካቸውን ክፋይ፣ ተተኪያቸውን በትክክለኛው የማፍሪያ መስመር ያፈሩበታል።

እንዲሁም በትዳር
~ ልክ ወላጆቻቸው ዘንድና ጓዶቻቸው ዘንድ አይተው ሲመኙት የነበረውን በቁጥርም በይዘትም መልካም የሆነን ቤተሰብ ያቋቁሙበታል።

~ ዘመድ አዝማድም ያስፋፉበታል።

ለትዳር ከታደሉ
~ የራስ ቤት የራስ ጎጆ በመፍጠር አዲስ ጎረቤት፣ አዳዲስ ወዳጆችን ይመሰርቱበታል።

በተለይ በትዳር
~ የኔ የሚሉትን ደጋፊና ተቆርቋሪ ታማኝ ወዳጅ ከጎን ያገኙበታል። እሱ ለሷ አሷ ደግሞ ለሱ ከማንም በላይ ጓጊና አዛኝ ይሆናሉና።

አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህንኑ እንድናስተውል በ ሩም ምዕራፍ አንቀፅ 21 ያመላክተናል 

« وَمِنْ آَيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِتَسْكُنُوا إِلَيْهَاوَجَعَلَ بَيْنَكُمْ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآَيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ » 

الروم: 21.

« ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህም ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ተዓምራቶች ኣልሉ። »

ይለናል

ሌላኛው ጥቅም
 በትዳር
~ ከተለያዩ የዘመኑ ፈተናዎችም ሆነ ከግልፁ ዝሙት ይጠበቁበታል። ብሎም የላጤነትን ቁጥር በማሳነስ ብልሹ ና ርካሽ ምግባርን ለመቀነስ ድርሻቸውን ይወጡበታል። የህብረተሰቡም ክብርና ዝርያ ይፀዳበታል።

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳስጠነቀቁን

« إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فأنكحوه إلا تفعلوا تكن فتنة في الأرض وفساد كبير …… »

« ዲኑን እና ስነምግባሩን የምትወዱለት ሰው {ዲኑን በመተግበር የሚታወቅ ብሎም መልካም ባህሪ ያለው}  (ለጋብቻ ፍለጋ) ሲመጣችሁ አጋቡት። ይህ ካልሆነ ማለትም ካላደረጋችሁት ግን በምድር ላይ ከባድ የሆነ ፈተናን ብልሽትን ታሰፍናላችሁ ። »

በተጨማሪም ለመልካም ትዳር የታደሉ

~ ክቡር መንደር፣ ሃገርና ማህበረሰብ ይገነቡበታል ።

እንዲሁም… ………
~ አሱ በሷ እሷ በሱ ብሎም በሚያፈሩት ልጆችም ሰበብ የዱንያ ላይ ሪዝቃቸውን ያሰፉበታል። በመልካምነታቸው ልክም የዱንያንና የኣኺራን ስኬት  ይጎናፀፉበታል።

ሱረቱል ኑር አንቀፅ 32 ትን ልብ ይበሉ 

« وَأَنْكِحُوا الْأَيَامَى مِنْكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ إِنْ يَكُونُوا فُقَرَاءيُغْنِهِمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ »

 {النور:32} 

« ከእናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ። ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የሆኑትን አጋቡ ። ድሆች ቢሆኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል። አላህም ስጦታው ሰፊ አዋቂ ነውና ። »
 
 ስለሆነም ይህንን ታላቅ  የሆነ የህይወት ማዕከል በቀላሉ ማፍረስና መበተን ጉዳቱ የከፋ በመሆኑ ሁሉም የየራሱን መልካም አስተዋፅዖ ማድረግ ይገባዋል። 

   በተለይ ወደ ባለትዳሮቹ መቅረብ የሚችሉ ግለሰቦች ለነርሱ መራራቅና ለአንዳቸው ባንዳቸው ላይ ማመፅ ሰበብ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል።
    
   በመሆኑም በሁለቱ ግለሰቦች ዙርያ የሚገኙ ወዳጆች መልካምን በማሰብም ይሁን በሌላ አስተሳሰብ…… የወዳጆቻቸውን ትዳር ከሚያናጋ አካሄድ ሊርቁ ይገባል።

  ይህ ሲባል ግን እሷ ወይም እሱ ሲበደል በዝምታ ይለፉት ማለትም አይደለም። ይልቁንም ባላቸው ቅርበትና ወዳጅነት ልክ ለማግባባት መጣር አለባቸው።

   የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት: 
 
( مَنْ خَبَّبَ زَوْجَةَ امْرِئٍ أَوْ مَمْلُوكَهُ فَلَيْسَ مِنَّا )

« አንዲትን ሴት በባሏ ላይ ወይም ባርያውን(አገልጋዩን) በአለቃው ላይ ያበላሸ (ያሳመፀ) ከኛ አይደለም»
ብለዋል።
   
   አንዲትን ባለትዳር ሴት በባሏ ላይ እንድታምፅ ያደረጋት ማለትም ስነምግባሯ ፀባይዋ እንዲበላሽ ሰበብ የሆነ ሰውን በተመለከተ ጠንካራ የሆኑ ማስጠንቀቂያዎች ተላልፈዋል።

   ከነዚህም መሃከል መልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሌላ ሃዲሳቸው እንዳሉት:- 

" ملعون من خبَّب امرأة على زوجها "

« አንዲትን ሴት በባሏ ላይ ብልሹ እንድትሆን ያደረገ ዕርጉም ነው » 

ይህንን በተመለከተም  ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አልፈውዛን ሃፊዘሁላህ ሲያብራሩ 

وقال الشيخ صالح الفوزان- وفقه الله - :
وقد جاء الوعيد الشديد في حق من يفسد الزوجة على زوجها ، ويخببها عليه ؛ 

فقد جاء في الحديث :
 " ملعون من خبَّب امرأة على زوجها " 
ومعناه : أفسد أخلاقها عليه ، وتسبب في نشوزها عنه .

" المنتقى من فتاوى الشيخ الفوزان " 
( 3 / 248 ، 249 ) .

“ ይህም ለመጥፎ ፀባይዋ ሰበብ የሆነ፣ ወደ ክፋት የጎተጎታት ፣ የሳባትና በባለቤቷ ላይ እንድታምፅ ስርዓት እንድትጥስ ያደረጋት ከመልካም ሙስሊሞች አባል እንዳልሆነና ኣልፎም ከአላህ ራህመት የራቀ ዕርጉም መሆኑን ያሳያል። ”
……………………………………………

   በተለይ ባሁኑ ወቅት ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ሆኗል። የእያንዳንዱን ቤተሰብ የሚያንኳኳ ዜናም እየሆነ ነው።

   ይህ ባህሪ በሚስት ጓደኞች፣ ቤተሰቦች፣ ወላጆች፣ እንዲሁም ጎረቤቶችና ሌሎችም ጣልቃ ገብ ባህሪ ያላቸው ግለሰቦች የተፈተኑበት ሆኗል።

   " አዛኝ ቅቤ አንጓች " እንዲሉ

 ለትዳሮች መፈረካከስ ሰበብ እየሆኑ ለሷ ብዬ ነው ለሱ ብዬ ነው የሚሉ ወገኖችም ሊመከሩና ይህንን የመሳሰሉ ሃዲሶችን ልብ ሊሉት ይገባቸዋል።
---------------------------------------

   ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አልፈውዛን አክለው  እንደሚያስረግጡት 

… والواجب على أهل الزوجة أن يحرصوا على صلاح ما بينها وبين الزوجها؛ لأن ذالك من مصلحتها ومصلحتهم. 

“ በተለይ የሚስት ወገኖች (ቤተሰቦች) በባሏና በርሷ መካከል ቁርሾን ሊያስወግዱ እርቅ ሊፈጥሩ በዚህ ላይ ሊተጉ ግዴታ ይሆንባቸዋል ። ዞሮ ዞሮ ይህ ጉዳይ ለራሳቸውም ለሚስቲቱም ጥቅም መሆኑን ሊያስተውሉ ይገባልና። ”

" المنتقى من فتاوى الشيخ الفوزان "
 ( 3 / 248 ، 249 ) .
   
  አላህ ከእንደዚህ አይነቱ ፊትና ይጠብቀን
ኣሚን
Abufewzan Last zulhijjah 
oct 25/2014‎

Abufewzan Last zulhijjah  oct 25/2014