Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አስፈሪ ነብያዊ ትንቢት!




አስፈሪ ነብያዊ ትንቢት!
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሺርክ የጎን ውጋት ሆኖ እረፍት
ይነሳቸው ነበር፡፡ ተመልከቱ እስኪ ሶሐባቸውን ጀሪር ኢብኑ
ዐብዱላህን “ምነው ከዚህ ከዙል ኸለሷ አታሳርፈኝም” ብለው
ሲጠይቁት፡፡ እኛስ? እኛማ ሽርክ አይጎረብጠን፡፡ ምቾታችንን
አይነሳን፡፡ ለነገሩ ከነመኖሩስ መቼ አመንና፡፡ ይሄ ሁሉ
የጃሂሊያን አስከፊ ገፅታ አለማወቅ የሚያመጣው ጣጣ ነው፡፡
እንደሚባለው “ጃሂሊያን የማያውቅ ትውልድ ሲመጣ የኢስላም
ቋጠሮዎች በየተራ ይፈርሳሉ፡፡” ይሄው ዛሬ የኛው ለኢስላም
ተቆርቋሪ ትውልድ የነ አቡ ጀህልን ሺርክ እየሰራ፣ የነ አቡ
ጀህልን ምክኒያት እየደረደረ እነ አቡ ጀህልን ይራገማል፡፡
ከሺርክ ላይ ጎዝጉዞ እየኖረ ከተውሒድ ጣራ ላይ ያለ
ይመስለዋል፡፡ ከተውሒድ እጅግ ባነሱ ጉዳዮች አስገራሚና
ጠንካራ ውሳኔ እያሳለፈ የኢስላሙ ህልውና ዋና ምሰሶ የሆነውን
ተውሒዱን ስለሚንደው ሺርክ ሲወራ ግን ውስጡ ይደፈርሳል፡፡
{አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ የነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም
የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይሸማቀቃሉ (ይደነብራሉ)፡፡
እነዚያም ከርሱ ሌላ የሆኑት (ጣዖታት) በተወሱ ጊዜ እነርሱ
ወዲያውኑ ይደሰታሉ፡፡} (አዙመር፡ 45) {በቁርኣኑም ጌታህን
ብቻ በጠቀስክ ጊዜ ጀርባቸውን ሰጥተው ይደነብራሉ} (አል
ኢስራእ፡ 46) እነኚህ አንቀፆች ኢስላምን በ“እንጭጩ”
ለመቅጨት ሲራወጡ ስለነበሩ ሙሽሪኮች አልነበረም እንዴ
የሚያትቱት? ዛሬስ የተውሒድ ደዕዋ የሚያስደነብረው እነማንን
ነው? የሚከፉት እውን እነማን ናቸው? ተራ ጃሂሉማ ይቅር
ባያውቅ ነው ይባላል፡፡ በሒክማ እያስታከኩ “በሒክማ”
ተውሒድን የሚዋጉትን እስኪ አስቧቸው፡፡ አዎ ሒክማ
ያስፈልገናል፡፡ ግን ሒክማ ማለት አግባብ ባለው መልኩ
ለቀዳሚ ነገር ቅድሚያ እየሰጡ ማስተማር እንጂ በሽርክ
ለተዘፈቀ ማህበረሰብ “ፍቅር በኢስላም” ዓይነት ርእስ
እየለቀቁ ማስተኛት አይደለም፡፡ ከማንም በላይ ስለኢስላም
እየጮኸ ግን ተውሒድ የሚያስደነብረው ስንት ነው?
በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ለተውሒድ ዳዕዋ ትልቅ ደንቃራ የሆኑት
በሐቅ ሒሳብ እውቅናን የሚሸምቱ ቁሳውያን ሰባኪዎች
ናቸው፡፡ “በአሁኑ ሰዐት 13 ዓመት ወደ ተውሒድ መጣራት
አያስፈልግም”፣ “ሁሉም ሙስሊም ላኢላሀኢለላህ እያለ ነው”፣
“ከነአቡጀህል መሀል ያላችሁ ይመስል ሺርክ ሺርክ አትበሉ”
እያሉ ሐቂቃውን ክደው ሰውን ያስተኛሉ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ
ወሰለም ግን ይሄውና አስፈሪ ትንቢት ይሰጣሉ “… ከህዝቦቼ
የተወሰኑ ጎሳዎች ወደ ሙሽሪኮች ሳይጠጉ፣ የተወሰኑትም
ጣኦቶችን ሳይመልኩ ቂያማ አትቆምም!!!” አቡ ዳውድ
የዘገቡት፡፡ ሌላም አለ “የደውስ ጎሳ አሮጊቶች በዘል ኸለሷ
ጣኦት ዙሪያ ለጦዋፍ መቀመጫቸውን ሳያረጠርጡ/ሳያደገድጉ
ቂያማ አይቆምም” ይላሉ፡፡ ሙስሊም የዘገቡት፡፡ በርግጥም
የተነበዩት በተጨባጭ ታይቷል፡፡ ዘል ኸለሷን እንውሰድ፡፡
ዙል ኸለሷ የደውስ ጎሳዎች ያመልኳት የነበረች ጣዖት ነበረች፡፡
በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትዕዛዝ እንድትፈርስ ተደርጋ
ነበር፡፡ ግን በሷላይ ያለው የሺርክ እምነት አብሮ ለዘላለሙ ከሷ
ጋር ፈርሷል ወይስ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
እንደተነበዩት ከጊዜ በኋላ ተመልሷል? ሸይኹል አልባኒ እንዲህ
ይተርኩልናል፡፡ “ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተናገሩት
በርግጥም ተከሰተ፡፡ ደውስና በዙሪያው ያሉ የዐረብ ጎሳዎች
እንደገና መሀይምነት እነዚያን አካባቢዎች ከተቆጣጠረ በኋላ
በዘል ኸለሷ ተፈተኑ፡፡ ከአላህ ሌላ እንደገና አመለከቷት፡፡
ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሃብ ተነስቶ ወደ ተውሒድ
እስከሚጣራ፣ ከዲንም የከሰመውን እንደገና እስከሚያድስ፣
ኢስላምን ወደ ዐረቢያ ልሳነ ምድር ዳግም እስከሚመልስ
ድረስ፡፡ በጊዜው የነበረው ንጉስ አልኢማም ዐብዱል ዐዚዝ
ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ ረሒመሁላህ ተነስቶ የተወሰኑ
ዳዒዎችን ወደ ዘልኸለሷ በመላክ እንዲያፈርሷት አደረገ፡፡
የመጀመሪያው የሰዑድ ቤተሰቦች አገዛዝ በቱርኮች ሲወድቅ
መሀይማን ዳግም ዘል ኸለሷን ማምለካቸውን ተያያዙት፡፡
እንደገና ንጉስ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ዐብዱረሕማን ኣለ ሰዑድ
ሒጃዝን ሲቆጣጠር በዚያ አካባቢ ያለውን ሹም ያዘዋል፡፡
ከሰራዊቱም የተወሰነው ወደዚያው አቅንቶ አፈረሷት፡፡
ቅሪቷንም አስወገዱት፡፡ (ፈዋኢዱን ሚን መዓኒ ሚን ኩቱብ
አልአልባኒ፡ 1/14)
ዛሬ ግን “አንዳንድ” “ምሁሮች” ተውሒድ ማለት ልክ እንደ
ስሙ “ተው” + “ሂድ” ማለት ነው፡፡ ሰዎችን የሚያባርር
የሚበትን ነው ይሉናል፡፡ ምሳሌ አይደለም የተባለ ነው
እያወራሁ ያለሁት፡፡ ግን ተውሒድ የሚያስበረግገው ሰው
ከኢስላም ምን ይፈልጋል?