Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከነዚህ በባጢል ከሚያከፍሩት ትይዩ ደግሞ የአህሉሱና ወልጀማዐን .....

በኡስታዙና ሱልጣን ኸድር (ሐፊዘሁላህ)
“ከነዚህ በባጢል ከሚያከፍሩት ትይዩ ደግሞ የአህሉሱና ወልጀማዐን
አቋም ባግባቡ የማይረዱ ወይም ደግሞ ከፊሉን ተረድተው ከከፊሉ
የሚዘነጉ አሉ፡፡ ከሚረዱት ውስጥ ለሰዎች በመግለፅ ፋንታ የሚደብቁት
አለ፡፡ ከቁርአንና ከሱና ተፃራሪ የሆኑትን ቢድዐዎች አያስጠነቅቁም፡፡
የቢድዐ ሰዎችን አያወግዙም አይቀጡም፡፡ ምናልባትም በሱናና በዲን
መሰረቶች ላይ የሚደረግን ንግግር ልቅ በሆነ መልኩ ሊያወግዙ ይችላሉ፡፡
በዚህ ርእስ ላይ ቁርኣን፣ ሱናና ኢጅማዕ የሚያመላክተውንና የቢድዐና
የልዩነት ሰዎች የሚያራግቡትን አይለዩም፡፡ ወይም ደግሞ ልክ ልዩነቶች
በሚታለፉባቸው የኢጅቲሃድ ርእሶች ላይ ዐሊሞች እንደሚተላለፉት
ለሁሉም የተለያዩ መንገዶች እውቅና ይሰጣሉ፡፡ ይህኛው አቋም በርካታ
ሙርጂአዎች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ ሙተፈቂሀ፣
ሱፍዮችና ተፈላሳፊዎች ላይ ይንፀባረቃል፡፡ ልክ የመጀመሪያው የስሜት
ተከታዮችና የከላም ባለቤቶች ላይ እንደሚንፀባረቀው፡፡ እንግዲህ ሁለቱም
መንገዶች ፈር የለቀቁ ከቁርኣንና ከሱና ያፈነገጡ ናቸው፡፡ መሆን ያለበት
አላህ መልእክተኞችን የላከበትንና መፃህፍት ያወረደበትን እውነት ግልፅ
ማድረግ ነው፡፡ (አልፈታዋ፡ 12/467፣468)
ሱብሐነላህ!!! “ታሪክ እራሱን ይደግማል” ይላሉ፡፡ ኢብኑ ተይሚያ
የሚገልፁዋቸው ሁለቱም አይነት አንጃዎች ዛሬ ግልፅ በሆነ መልኩ
ከሙስሊሙ መሀል ይገኛሉ፡፡ ሸይኹ ልክ ከኛው መሀል ሆነው፣ የኛን
ሁኔታ እያዩ ስለ እኛ የሚያወሩ ነው የሚመስለው፡፡ አሁንም ኢብኑ
ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- (ወደ ቢድዐው የሚጣራ ሰው
በሙስሊሞች የጋራ አቋም ቅጣት ይገባዋል፡፡ ቅጣቱ አንዳንዴ በሞት ሌላ
ጊዜ ደግሞ ከዚያ ባነሰ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሰለፎች ጀህም ኢብኑ
ሶፍዋንን፣ አልጀዕድ ኢብኑ ዲርሀምን፣ ገይላንንና ሌሎችንም ገድለዋል፡፡
ቅጣት የማይገባው ሆኖ ከተገኘ ወይም ደግሞ መቅታቱ የማይመች ሆኖ
ከተገኘ የግድ ቢድዐውን ማሳወቅና ሰዎችን ከቢድዐው ማስጠንቀቅ
ያስፈልጋል፡፡ ይህን ማድረጉ አላህና መልእክተኛው ያዘዙት ከሆነው
በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ውስጥ የሚካተት ነው))
(አልፈታዋ፡ 35/414)
አሁንም ኢብኑ ተይሚያ፡- (ከቁርኣንና ከሱና ጋር የሚፃረሩ ንግግሮች
(መቃላት) ወይም ዒባዳዎች ያላቸውን ሰዎች ሁኔታ ግልፅ ማድረግ፣
ከነሱም ህዝብን ማስጠንቀቅ በሙስሊሞች የጋራ አቋም ግዴታ ነው፡፡
እንዳውም ኢማሙ አሕመድ “(ግዴታ ያልሆኑ ፆሞችን) የሚፆም፣ (ግዴታ
ያልሆኑ ሶላቶችን) የሚሰግድና ኢዕቲካፍ የሚያደርግ ከሆነ ሰውና ከቢድዐ
ሰዎች የሚያስጠነቅቅ ከሆነ ሰው አንተ ዘንድ ማንኛው ይበልጣል”
ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው ነው የመለሱት፡- “የመጀመሪያው ቢፆም
(!) ቢሰግድ ኢዕቲካፍ ቢያደርግ ለራሱ ነው፡፡ በቢድዐ ሰዎች ላይ ሲናገር
ግን ለሙስሊሞች ነው እየሰራ ያለውና እሱ በላጭ ነው፡፡” ስለዚህ
ኢማሙ አሕመድ ግልፅ እንዳረጉት በቢድዐ ሰዎች ላይ መናገር ጥቅሙ
ልክ በአላህ መንገድ ላይ እንደመፋለም አጠቃላይ ለሙስሊሞች ዲናቸውን
የሚጠብቅ ጥቅም አለው፡፡ ምክኒያቱም ከቢድዐ ባለቤቶች የአላህን
መንገድና ሸሪዐውን ማፅዳት፣ በዲን ላይ መተላለፋቸውንም መከላከል
በሙስሊሞች የጋራ አቋም ግዴታ ነው፡፡ የነኝህን ተንኮል ለመከላከል
አላህ የሚመድበው ባይኖር ኖሮ ዲን ይጠፋ ነበር፡፡