Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙስሊሟ ሴት እና ትዳር ከጋብቻ ትስስር በኃላ

ሙስሊሟ_ሴት_እና_ትዳር
ከጋብቻ ትስስር በኃላ
1,መታዘዝ ፡- አማኟ ሴት አላህን በሚወነጅል ነገር እስካልሆነ ድርስ ለባሏ ታዛዥና ተንከባካቢ ነች:: በርግጥም ደግሞ ባል በሚስቱ ላይ ያለው መብት ከምንም በላይ ነው:: ከወላጆቿም ጭምር:: እናም አማኟ ሴት ይህን በወጉ ተገንዝባ የባሏን መብት አቅሟ በፈቀደው ሁሉ የምትፈጽም ነች:: ይህን ከሚናገሩ በርካታ መረጃዎች ውስጥ የሚከተለው አቡ ሁረይራ ያወራው የረሱል (ﷺ) ሀዲስ ይገኝበታል እንዲህ ብለዋል ፡-
«አንድ ሰው ለሌላ አካል እንዲሰግድ ባዝ ቦሮ ሴትን ልጅ ለባሏ እንድትሰግድ አዝ ነበር» (ቲርሚዚይ ዘግበውታል)
አዎ! አማኟ ሴት ባሏን ስትታዘዝ ለአላህና ለመልዕክተኛው ስትል እንደሆነ ጠንቅቃ ታውቃለች::እናም በዚህ ጉዞ ላይ መሰናክሎች ቢፈጠሩም እንኴን ሙሉ በሙሉ ግን ከታዛዥነት አታፈነግጥም:: እንዲያውም ትክክለኛ ታዛዥነቷ የሚረጋገጠው በዚህ ቀውጢ ወቅት ነው። ምክንያቱም ኖሮት ሲያደርግላት፣አግኝቶ ሲያቀማጥላት የሚኖር ለሆነውማ ምላሹ ለሁሉም ግልጽ ነው። ሌላው ቢቀር ይህ ውለታው ሪሱ ይገዛልና ፡፤ዳሩ ግን መብቷን ሲያጎድል ታግሳ፤ እጅ ሲያጥረው አይዞህ ብላ፤ ሲቸግረው ያልፋል ብላ የምታደርገው ታዛዥነት ትክክለኛ ለአላህለ ብላ አድራጊነቷን (ኢኽላስ) አመልካች ነው:: ለዚህ ምሳሌ ከሚሆኑት እጹብ ድንቅ እንስቶች ውስጥ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ (ﷺ) በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ለውድ ባለቤቷ አሊይ ቢን አቢጣሊብ (ረድየላሁ ዐንሁ) እህል በምትፈጭበት ሰአት በእጇ ላይ የሚደርሰውን ህመም አጫወተችው:: የባለቤቱን መብት ጠባቂ ተንከባካቢና አፍቃሪ የነበረው ውድ ባሏም አሊይ (ረድየላሁ ዐንሁ) ወደ አባቷ (ﷺ) ሄዳ የምታግዛት ሰራተኛ እንዲሰጧት እንድት ጠይቅ አመላከታት፡፤እርሷም ሄደች:: ነገር ግን ለመጠየቅ እፍረት ይዟት ተመለሰች::ከዚያም አሊ (ረድየላሁ ዐንሁ) እራሱ በመሄድ ጠየቃቸው። ነገር ግን የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ያሉትን አልሰጧቸውም። ግና ወደ እነርሱ በመምጣት እንዲህ አሏቸው ፡-
«ከጠየቃችሁት የበለጠ ነገር ላስተምራችሁን? በመኝታችሁ ላይ ስትሆኑ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሀነላህ፣አልሀምዱሊላህ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላሁ አክበር ሰላሳ አራት ጊዜ በሉ::ይህ ለእናንተ ከአገልጋይ የበለጠ ነው::»
አዎ! ልክ እንደዚሁ ነው አማኟ ሴት ደስታንም ሃዘንንም ከውድ ባሏ ጎን በመቆም የምታሳልፈው:: ታዛዥነት ሲባል ከላይ እንደተጠቀሰው ጠቅልል ባለ መልኩ ሲሆን የተወሰኑ ነጥቦችን ብቻ በዚህ ዙሪያ እንመልከት ፡-
==> እርሱ ያልፈለገውን ሰው ቤቱ አታስገባም
==> እርሱም ባለበት ግዴታ ያልሆኑ ጾሞችን አትጾምም::
ማስረጃ የሚከተለው አቡ ሁረይራ ያወሩት ሃዲስ ነው የአላህ መላክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ፡-
«ለአንዲት ሴት ባሏ ባለበት ልትጾም አይበቃላትም፡፡በቤቱ ውስጥም ያለ እርሱ ፍቃድ ማስገባት አትችልም” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
==> ለግንኙነት ሲጠይቃት እንቢ ማለት የለባትም::
አቡ ዓልይ ጠልቅ ኢብን ዐለይ ባወሩት ሃዲስ የአላህ መላክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ፡-
«ባል ሚስቱን ለፍላጎቱ ከጠራት ከምድጃ ላይ ቢሆን እራሱ ትምጣለት::» (ቲርሚዝይ እና ነሳኢ ዘግበውታል )