ብርቅዬው መፅሃፍ
ይህ ቁርአን ለየትኛውም መፅሃፍ ተስጥቶ ያልታየና ያልተሰማ ክብርና ተአምራትን የያዘ ብቸኛውና ብርቅዬው መፅሃፍ ነው። የሰው ልጆች ከጨለማ ወደ ብርሃን ሊወጡበትና የህይወታቸው መመሪያ ያደርጉት ዘንድ ከአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የወረደ ፉጡር ሳይሆን የተከበረ የእርሱ ንግግር ነው። ስለዚህ ባጠቃላይ የሰው ልጆች። ለየት ባለ መልኩ ደግሞ ሙስሊሞች። ህይወታቸውን በእምነትም ይሁን በስነምግባር፤ በፓለቲካም ይሁን በኢኮኖሚ ባጠቃላይ በሁሉም የህይወት ዘርፋቸው አንድና ቀጥተኛ መንገድን ከፈለጉ ይህንን ታላቅ መፅሃፍ ማጥናትና መመርመር ግድ ይላቸዋል። የወረደበትም ብቸኛው አላማም ይህው ነው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ይህን ሲናገር እንዲህ ብሏል፦
" كتب أنزلناه إليك مبرك ليدبروا ءايته وليتذكر أولوا الأبب "
“ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መፅሃፍ ነው። አንቀፆቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮ ባለቤቶችም እንዲገሰፁበት (አወረድነው) “ ምእራፍ ሷድ 29
" كتب أنزلناه إليك مبرك ليدبروا ءايته وليتذكر أولوا الأبب "
“ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መፅሃፍ ነው። አንቀፆቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮ ባለቤቶችም እንዲገሰፁበት (አወረድነው) “ ምእራፍ ሷድ 29
0 Comments