Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መከራን በትዕግስት ማለፍ

መከራን በትዕግስት ማለፍ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የመካ ሙሽሪኮች በሙዕሚኖች ላይ የሚፈፅሙት ትንኮሳና ኢሰብዓዊ እርምጃ እጅጉን በከፋ ጊዜ ከፊል ሰሀቦች ወደ መልክኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመሄድ እንዲህ አሏቸው " ለምን ከአላህ ዘንድ እርዳታን (ነስርን ) አትጠይቅልንም? ለምን ጌታህን አትማፀንልንም? "
መልክተኛውም ( ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንዲህ በማለት አፅናኗቸው "ከናንተ በፊት በነበሩ ህዝቦች አንድ ሙዕሚን ተይዞ ይመጣል ፤ ጉድጓድ ይቆፈርለታል ፤ (በተቆፈረው) ጉድጓድ ውስጥም ይደረጋል ፤ (ከዚያም) መጋዝ ይመጣና በጭንቅላቱ ላይ ይደረጋል ሁለት ቦታ እስኪካፈል ድረስ ይገዘገዛል። ( እንዲሁም) ከብረት በተሰራ ማበጠርያ ስጋው ከአጥንቱ እስኪለይ ይበጠራል (ይሁንና ይህ ሁሉ መከራ) ከዲኑ አይመለሰውም ነበር ። " ባይምሉም ታማኝ የሆኑት ነብይ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁንና) ግን መሀላን በማከል እንዲህ አሉ " በአላህ ይሁንብኝ አላህ ይህን ዲን ይሞላዋል (ተቀባይነት እንዲያገኝ ያደርገዋል) አንድ ጋላቢ ከሰናዓእ እሰከ ሀድረመውት (በራሱ ላይ) አላህን እንዲሁም በበጎቹ ላይ ተኩላ ብቻ የፈራ ሲሆን ሆኖም ግን (እርዳታው ቶሎ ይመጣ ዘንድ ) እናንተ ትቸኩላላችሁ ። "
ሪያዱ አስሷሊህን ውስጥ በሰብር አርዕስት ስር ከተፃፉ ሀዲሶች ወይም ኪታቡ ላይ 41ኛው ሀዲስ
ከሀዲሱ ብዙ ቁም ነገሮች እንማራለን
፨ እምነታቸው አጠንክረው የያዙ ሙዕሚኖች አላህ የነርሱን ምንዳ ማብዛት ስለሚፈልግ ሁሌም ይፈትናቸዋል
(أَمْ حَسِبْتُمْ أَنْ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُمْ مَثَلُ الَّذِينَ خَلَوْا مِنْ قَبْلِكُمْ ۖ مَسَّتْهُمُ الْبَأْسَاءُ وَالضَّرَّاءُ وَزُلْزِلُوا حَتَّىٰ يَقُولَ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ مَتَىٰ نَصْرُ اللَّهِ ۗ أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ)
( የእነዚያ ከበፊቶቻችሁ ያለፉት (ምዕመናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ጀነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? (ለእነርሱ) መከራ (ድህነት) ፣ ጉዳት (ህመም) እና እንቅጥቃጤ ( የተለያዩ ፍራቻ በሚፈጥሩ ነገሮች ) ነካቻቸው
( እንደውም) መልክተኛውና እነዚያ ከሱ ጋር ያመኑት " የአላህ እርዳታ መቼ ነው? እስከሚሉ ድረስ አዋጅ( ንቁ )! የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው።)
[Surat Al-Baqara : 214]
፨ አላህ ሱብሀነሆ ወተዓላ መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተናገሩት እውን ማድረጉን ከሰነዓእ እስከ ሀድረም ት (የመን ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ናቸው) ሙዕሚኖች የበላይ ሆነዋል
፨ አንድ እውነተኛ አማኝ ቶሎ ድል ለምን አልመጣም ብሎ መጣደፍ እንደሌለበትና መጨረሻው የሙዕሚኖች መሆኑን
(قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ اسْتَعِينُوا بِاللَّهِ وَاصْبِرُوا ۖ إِنَّ الْأَرْضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَنْ يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ ۖ وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ)
(ሙሳም ለህዝቦቹ እንዲህ አላቸው " በአላህ ታገዙም ፣ ታገሱም ። ምድር የአላህ ናትና ከባርያዎቹ ለሚፈልገው ያወርሳታል ፍፃሜው ግን ለፈሪሀ አላሆች ነው።)
[Surat Al-Araf : 128]
ሁሌ የአላህ እርዳታ ዘገየ ፤ የአላህ ቻይነት ይገርማል እያልን ተስፋ አንቁረጥ ይልቅ አላህ እንደሚፈልገው እኛ ምን ያህል ትክክለኛ ሙዕሚኖች ነን ? ብለን እራሳችን መፈተሽ ይኖርብናል ። አላህ ሱብሀነሆ ወተዓላ ሰብረኞች እጅጉን ያወደሳቸዋል ፤ በዲን ውስጥ መሪነትም የሚያገኙት እነርሱ ብቻ እንደሆኑ ይናገራል
(وَجَعَلْنَا مِنْهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا لَمَّا صَبَرُوا ۖ وَكَانُوا بِآيَاتِنَا يُوقِنُونَ)
(በታገሱና በተዓምራቶቻችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ ከነርሱ ውስጥ በትዕዛዛችን የሚመሩ መሪዎችን አደረግን።)
[Surat As-Sajda : 24]
ሁሌም ቢሆን መፈተን ያለፉ ነብያቶች ሱና ነውና ከፈተና የማናመልጥ መሆናችንን ጠንቅቀን አውቀን የሚመጣውን ፈተና ይበልጥ የምናሸንፈው ዲናችንን በአግባቡ ስናውቅ ብቻና ብቻ እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል ። ከሚነሱ አንጃዎች ሁሉ አዲስ ከምንሆን ቀድመን መሠረታችን በተውሂድ ብናስተካክል አይደለም አህባሽ ሌላም ቢመጣ ጉዳያችን አይሆንም። ልብ በሉ ዛሬ አህባሽ በፊት ለፊት በር ሰተት ብሎ ስለገባ በአደባባይ ተቃውመን ብናሸንፍ እና ነገ ደግሞ ሌላኛው አንጃ በጓሮ በር ቢገባ የኔና ያንተ መጨረሻ ምንድነው? የቤት ስራ

Post a Comment

0 Comments