***********የኡዱሒያን እርድ የሚመለከቱ ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች**********
ኡዱሒያህ ማለት በዒደልአድሓ ቀን ወደ አላህ ለመቃረብ ታስቦ የሚታረድ እርድ ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በተግባር ፈፅመውታል፡፡ መዲና ላይ አስር አመት ሲኖሩም ኡዱሒያን ያርዱ ነበር፡፡ (ሚሽካት፡ 1475) እንዲፈፀምም አዘዋል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው ሰው ሊፈፅመው ይገባል ማለት ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “አቅሙ እያለው ኡዱሒያን ያላረደ ሰው መስገጃችንን እንዳይቀርብ” ብለዋል፡፡ (ከኡሑዲያህ ጋር የተያያዙ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች
የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት
1. የሚታረደው እንስሳ ከሚከተሉት የእንስሳት አይነቶች ብቻ መሆን አለበት፡- በግ፣ ፍየል፣ ከብት እና ግመል፡፡
2. ከነዚህ እንስሳቶች የትኛውን ማረድ ነው የሚበልጠው? በቅደም-ተከተል 1ኛ/ ግመል፣ 2ኛ/ ከብት፣ 3ኛ/ በግ 4ኛ/ ፍየል 5ኛ/ ግመል በጋራ 6ኛ/ ከብት በጋራ ማረድ (ፈትዋ ለጅነድዳኢማህ) (ኢብኑ ዑሠይሚን፡ አሕካሙልኡዱሒያ ወዘካት) ከብትና ግመልን በጋራ ማረድ የፈለገ አንዱ ለ7 ሰው ነው መሆን ያለበት፡፡
3. የሚታረደው እንስሳ እድሜው የደረሰ መሆን አለበት፡፡ በግ 6 ወር፣ ፍየል 1 አመት፣ ከብት 2 አመት፣ ግመል ከሆነ 5 አመት የሞላው መሆን አለበት፡፡
4. የሚታረደው እንስሳ እውር፤ በሽተኛ፤ አንካሳ፤ በጣም ያረጀ፣ አብዛሃኛው ወይም ግማሽና ከዚያ በላይ የሆነ ጆሮው፣ ጅራቱ፣ ላቱ፣ ቀንዱ፣ የተቆረጠ ወይም የተሰበረ መሆን የለበትም፡፡
5. የሚታረደው እንስሳ ህጋዊ በሆነ መልኩ የራስ ንብረት መሆን አለበት፡፡ (የተሰረቀ፣ የተነጠቀ፣ የተጭበረበረ ..መሆን የለበትም)
6. የሚታረደው የግድ በተገደበው ጊዜ መሆን አለበት፡፡ እሱም ከዒድ ሶላት በኋላ እስከ ዙልሒጃ 13 ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ዒድ) ከመሰገዱ በፊት ያረደ በሷ ቦታ (እርዱን) ይድገም፡፡ ያላረደ ይረድ” ይላሉ፡፡ (ቡኻሪ)
7. ያለምንም ልዩነት ከሁለቱም ፆታ ከወንድም ከሴትም ለኡዱሒያ ማረድ ይፈቀዳል፡፡ (ኢብኑ ባዝ፣ ፈታዋ ኑሩን ዐለደርብ፡ ካሴት ቁ. 72)
8. ቆዳውንም ይሁን የትኛውንም ክፍሉን መሸጥ አይፈቀድም፡፡ ለአራጁ የሚከፈለውም ከኡዱሒያው ቆዳ ወይም ሌላ ክፍሉ መሆን የለበትም፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የኡዱሒያውን ቆዳ የሸጠ ኡዱሒያ የለውም!!” ብለዋል፡፡ (ሶሒሑልጃሚዕ፡ 2/1055) ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከኡዱሒያው ስጋ፣ ሞራ፣ ቆዳ፣ ወይም ሌላ ነገር መሸረጥ ክልክል ነው፡፡ ምክኒያቱም ለአላህ ያወጣው ገንዘብ ስለሆነ ልክ እንደ ሰደቃ መመለስ አይቻልም፡፡ (ፈታዋ ኢብኑ ዑሠይሚን፡ 25/162) ባይሆን ስጦታ የተሰጠው ሰው ቢሸጥ ምንም ችግር የለበትም፡፡
9. ስጋው ምን ይደረጋል? በእለቱ ከቤት ይበላል፤ ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ለምስኪን ይሰድቃል ወይም ስጦታ ይሰጣል፣ ቀሪ ከኖረ ያስቀምጣል፡፡ ስጦታ የተሰጠው ሰው ግን መሸጥን ጨምሮ ሐላል በሆነ መልኩ ለፈለገው አገልግሎት ማዋል ይችላል፡፡
10. ኡዱሒያውን እራሱ ባለቤቱ ቢያርድ በላጭ ነው፡፡ ካልቻለ ወይም ካልተመቸው ግን ሰው መወከል ይችላል፡፡
ከተለያዩ ፈትዋዎች የተሰበሰበ ነው፡፡ ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡
Ibnu Munewor