ያልተነገረላቸው የዒልም አርበኛ!!
ከግማሽ ክፈለ ዘመን በላይ በመማር ማስተማር የተጉ ድንቅ አሊም
ዑለሞቻችን ሲዘከሩ... የአንድ ሰዉ ስም ከተጠራ ለኢትዪጵያ ሙስሊም ከፍተኛ አስተዎጾ ማበርከታቸዉ ብዙ ባይነገርም ብዙዎች ግን "ተምሬባቸዋለው" ይላሉ። እኚህ ሰዉ ተዉሂድን በማስተማር ለአስርት አመታት ታግለዋል። ሚሊየኖች የሚታደሙበት የመረጃ መረቦችና የሀርድ ኮፒ ሲዲዎች ሳይኖሩ በፊት፤ ከደሴው አረብ ገንዳ እስከ አንዋርና ሀሺም መስጂዶች ለረጅም አመታት በሰጧቸዉ የተዉሂድ፣ የሀዲስና የተፍሲር ትምህርቶች ለብዙ ኢትዬጵያውያን ሙስሊሞች መድረስ የቻሉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ባለውለታ ናቸው።
ለመሆኑ እኚህ ሸይኽ ማናቸዉ???
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ ይባላሉ።
👉 ዉልደት
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ በወሎ ከተማ ምዕራብ ደሴ የባሲጥ እጅ መንደር በ1938 እ•ኢ•አ በ1945 እ•ኤ•አ ከተከበረ ሙስሊም ቤተሰብ ተወለዱ። የአባታቸዉ ስም አህመድ ዑመር የእናታቸዉ ስም ዘይነቡ ሽፋ ይባላል። የሸይኽ አልባሲጢይ አባት አህመድ ዑመር የዘመነ መሳፍንት ባላባት ናቸው። እናታቸው ዘይነቡ ሽፋ የሸይኽ ልጅ ናቸው።
👉 የ22 ዓመታት የዒልም ጉዞ
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ የልጅነታቸውን ጊዜ በጥሩ ኢስላማዊ አስተዳደግ ያሳለፋት። ገና በልጅነታቸው በባሲጥ የጁ መንደር ውስጥ ቁርዐንና ሌሎች ተዛማጅ የሸሪዐ ትምህርቶችን ቀስመዋል። በጨቅላነታቸዉ ቁርዐንን ከእናታቸዉ ዘመድ ከሸኽ አሊ ቡሩ ቀሩ።
√ ለ9 አመታት በለገሂዳ መንደር ሸይህ አሊ አደም ዘንድ የፊቅህ እውቀትን አዳርሰው ቀስመዋል። እኚህ ሸይኽ የታዋቂዉ የመካ አሊም ሸይኽ ሙሀመድ አሊ አደም አል–ወሎዊ አባት ናቸው።
√ በመቀጠል ወደ ቃሉ ወረዳ አጋምሳ መንደር ሸህ ተማም ዘንድ በመሄድ ለ 6 አመታት ነህውና ሰርፍ ተምረዋል።
√ ከቃሉ ሳይወጡ በቦሩ መንደር ሀጅ ቡሰይር ዘንድ ለአንድ አመት ተኩል ተፍሲር ቀርተዋል።
√ ወቅቱ ታላቁ አሊም አል ሐጅ ራፊዕ ወደ ከረጅም አመታት ቆይታ በኃላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ማስተማር የጀመሩበት ወቅት ስለነበር ቀጣጤ መንደር በመዘዋወር ለሁለት አመታት ቡኻሪና ሙስሊምን ቀርተውባቸዋል። ከሸይኹ ጋር የነበራቸው ቆይታ ይህ ብቻ አልነበረም። ሸይኹ የኃላ ኃላ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡም ተከትለው በመምጣት ለተከታታይ ሶስት አመታት ከኩቱቡ ሲታ ያልተማሯቸውን አራቱን ሱነኖች አንጥረው ቀርተዋል።
በጥቅሉ ወደ ዳዕዋ መንደር ሳይገቡ ለ22 አመታት የሸሪዕ ዕውቀትን ቀስመዋል።
👉🏻 የታላላቅ ኡለማዎች ማእድ
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የከተማ ዳዕዋና የመማር ማስተማር ህይወትን አሀዱ ብለዉ የጀመሩት በ1970ዎቹ እ•ኢ•አ ነው። በአዲስ አበባ ከሀጅ መሀመድ ሳኒ ሀቢብ ዘንድ ብዙ የተማሩ ሲሆን ሀዲስን በተመለከተም ከሸይኽ ሙሀመድ ራፊዕ ብዙ ተምረዋል።
ከታላላቅ ኡለማዎች በቀሰሙት ጥልቅ እውቀት ለማስተማር የብቃት ማረጋገጫ ኢጃዛ የተሰጣቸው ኢጃዛ በእጃቸው ይገኛል። ከዚህም መካከል የሀዲስ ሊቁ አል ሐጅ ራፊዕ እና የሸይኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ ኢጃዛ ይገኙበታል።
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ በሸይኾቻቸው ዘንድ ተወዳጅና ተመራጭ ነበሩ።
ሀጅ ራፊእ በታላቁ አንዋር መስጂድ በራሳቸው ቦታ ላይ ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም ተፍሲር እንዲያስቀሩ አድርገዋቸው ነበር። እንደዚሁ ሀጂ ሳኒንን ተክተው በአንዋር ትልቁ መስጂድ ውስጥ የተፍሲር ትምህርት መስጠታቸው ይታወሳል።
ከዘመናችን ታላቅ አሊም ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ኢብኑ ባዝ ጋር ጥሩ ወዳጅነት የነበራቸው ሲሆን፤ ሸይኹ ለዳእዋ እንዳበረታቷቸው እና የኢልም ብቃት ፈተናዎችን ካለፉ በኃላ ብዙ መልካም ውለታዎችን እንደዋሉላቸው ይጠቅሳሉ።
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ በዘመናችን የፊቅህ ፈርጥ የሆኑትን ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን ብዙ የሚያደንቁና በእጅጉ የሚወዱ ከመሆናቸው ባሻገር ከኪታቦቻቸውም ብዙ ተምረዋል። የአላህ ፍቃድ ሆኖም በመካ ለአስር ቀናት የቆየ የኢልም ኮርስ ታድመዋል። ያዩትን የሸይኽ ኡሰይሚን ትህትና፣ ጥልቅ እውቀትና ግርማ ሞገስ ሲያወጉ በሰፊው ነው።
👉🏻 ረጅሙ የዳዕዋና የታእሊም ስራ
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ በአዲስ አበባ ከተማ ከ38 አመታት በመማር ማስተማር እና በዳዕዋ ላይ የታገሉ፤ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሙስሊሙን በማገልገል ላይ የሚገኙ ታላቅ አሊም ናቸው። ባለፉት ሶስት አስርት አመታት የሸኹ የተፍሲር ደርሶች ብዙ መስጂዶችን ያስዋቡ ነበሩ። በተለይም አንዋር፣ ሀሽም እና አባቦራ መስጂዶች በሸይኹ የኢልም መሽሊሶች የደመቁ ሆነው ቆይተዋል።
ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ ሀቅን ለመናገር ባላቸው ጀግንነት ጥንካሬና ለኢስላም የመቆርቆር ስሜት ይታወቃሉ።
ኑር መስጂድ አጠገብ በነበረው ፈትህ መስጂድ ለ22 አመታት ያስተማሩ ሲሆን ከመድረኮቻቸው በአላህ ፍቃድ አያሌ ተማሪዎችን አፍርተዋል። ብዙዎችም የሳቸውን ፈለግ በመከተል በኢልምና በዳዕዋ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በቅርቡ በአሜሪካ አትላንታና ዲሲ የነበራቸው የዳእዋ ቆይታ ፍሬያማ የነበረ ሲሆን በሳውዲም በተለያዩ አጋጣሚዎች የዳእዋ ስራዎች ላይ ተሳትፈዋል።
👉🏻 የሸይኹ ድርሳናት
ሸይኽ አልባሲጢይ በአረብኛ አያሌ መፅሀፍትን የደረሱ ሲሆን በተለይም በቅርቡ ጠንካራ ጥናቶችና ጠቃሚ መልእክቶችን ለንባብ አብቅተዋል። ከነዚህም መካከል፤
1) ኑሩሸምዓህ ፊ መሳኢሊ የውሚል ጁምዓህ
2) ተፍሲሩ ጁዝ ዓምመ
3) ሪሳላህ ፊል ኢማን ቢላህ
4) መዛየል ኢስላም
5) አል መርአቱ ፊል ኢስላም
እና ሌሎችም ይገኙበታል።
አላህ እድሜያቸውን እንዲያረዝመውና ለኡመተል ኢስላም ይበልጥ ጠቃሚ ያደርጋቸው ዘንድ እንለምነዋለን!!
ሙሰፋ ሙሳ
የካቲት 13/2008
https://t.me/albasity