ሸይኻችንን አስተማሪያችንን መካሪያችንን አጣን
اللهم آجرنا في مصيبتنا وأخلفنا خيرا منه
ሸይኽ ሙሀመድ አህመድ ዑመር አል ባሲጢይ ታላቅ ዓሊም በዒልማቸው የሚሰሩ ትጉህ ዳዒ ነበሩ።
ዓቂዳና ሱና ላይ ጠንካራ የነበሩ፣ ረዥም አመታት ዲንን በማስተማር እድሜያቸውን የፈጁ፣ ለዱንያ ከሚገባው በላይ ማይጨነቁ ፈፅሞ የሰው እጅ ከማየት የራቁ፣ የዳዕዋን ሲስተም በማስተማርና የትም የማይገኝ ምክር በመለገስ ወደር የሌላቸው ታላቅ ተምሳሌት ነበሩ።
ሸይኻችን አልባሲጢይ በማህበራዊ ጉዳይ ሁሉም በሰላማዊነትና በሳልነት የሚመሰክርላቸው ከጎሮቤትና ዘመድ አዝማድ ጋር የፍቅርና የአባትነት ትሪትመንት የሚሰጡ በኢስላማዊ ተርቢያ የተገነባ ቤተሰብን ያፈሩ ያልታወቀላቸው አንበሳ ነበሩ።
ሸይኻችን አልባሲጢይ ወጣቱ በአእምሮውና በትኩስ ጉልበቱ ሁለንተናዊ እውቀትና በሂክማ የተሞላ እንቅስቃሴ ኖሮት ዲኑን እንዲያገለግል በአንፃሩ ደግሞ በችኮላ መንገድን እንዳይስትና በሰውና ጂን ሸይጣን መረብ እንዳይጠለፍ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጉ ነበር።
ባለውለታችን ክቡር አባት የተማሪዎች የዒልም ሂደት የዑለማዎችን መንገድ የተከተለ እንዲሆንና ኡሱሉል ፊቅህ፣ ነህው፣ ሰርፍ፣ የፊቅህ መሰረታዊ መትኖችና ወሳኝ የዒልም መርሆችን ትኩረት ያደረገ እንዲሆን የተጫወቱት ሚና ይህ ነው የሚባል አይደለም።
ውዱ ሸይኻችን የዳዕዋ ጉዳይ ዘወትር የሚያሳስባቸው የሀገር ውስጥና የውጭ የዳዕዋ መሰናክሎች ሲፈራረቁ ተጨናንቀው ዱዓ በማድረግና ዱዓቶች መጠቀም ያለባቸውን ሲስተሞች አበክረው በመምከር የሚታወቁ ከልብ ምሁር ነበሩ።
ስለሳቸው የሚናገር ማንኛውም ሰው ከብዙ ጥቂቱን የሚዳስስ ቢሆን እንጂ ሁሉንም የሚያዳርስ ነው ብዬ አላስብም በዘርፈ ብዙ የዲን እውቀትና ተግባሮች የሚታወቁ ንቁ ዓሊም ነበሩ።
የእኛስ እጣ ፈንታ ምን ይሆን? ከሞታችን ምን የሚታጣ ነገር አለ???
رحم الله شيخنا رحمة واسعة وأسكنه فسيح جنانه
إنا لله وإنا اليه راجعون اللهم آجرنا في مصيبتنا وأخلفنا خيرا منه
سلسبيل ذو مكانة

0 Comments