አሸንዳ፣ ቡሄ፣ እንቁጣጣሽ
. እነዚህ በዓላት አንዳንዶቻችን እንደባህል ነው የምንቆጥራቸው ነገር ግን መሰረታቸውን የኦርቶዶክስ ክርስትና ያደረጉ ሀይማኖታዊ በዓላት ናቸው። . አሸንዳ የክርስቲያኖችን የፍልሰታ ፆም ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን ቡሄ የደብረታቦር በዓል የሚሉት ነው። ሁለቱም ነሐሴ አጋማሽ ላይ የሚከበሩ ሐይማኖታዊ በዓሎቻቸው ናቸው። . እንቁጣጣሽ ደግሞ በክርስትና የዘመን አቆጣጠር አዲስ አመት ማብሰሪያ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ ምንትስ እየተባለ ተደራቢ ስም የሚሰጠው ሀይማኖታዊ በዓልም ነው። . (ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ ስህተት የሚፈፀምባቸው የጥምቀት ታቦት ሽኝት እና የገና ጨዋታ እንዲሁም ተያያዥ ተግባራትንም ማውሳት ያስፈልጋል) . እኛ ሙስሊሞች እንደነዚህ አይነት የኩፍር በዓላትን መሳተፍም ሆነ ማክበር ዲናችን አይፈቅድልንም።. ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ... . "ከሰዎች የተመሳሰለ፤ እርሱ ከነርሱው ነው" ብለዋልና . እንኳንስ እኛ በነርሱ በዓል ልንሳተፍ ይቅርና 'እንኳን አደረሳችሁ' ማለት እንኳ በዑለሞች ኢጅማዕ/ስምምነት የተከለከለ መሆኑን ዓሊሞች ይናገራሉ። . ታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) ... ለኩፍር በዓላት የ'እንኳን ደስ አላችሁ' መልእክት ማስተላለፍ ልክ መጠጥ የሚጠጣን ወይም ሰው የሚገድልን አሊያም ዝሙት የሚፈፅምን ሰው 'እንኳን ደስ አለህ' እንደማለት ነው ብለዋል። እሳቸው እንዳሉት ይህ ተግባር ለመስቀል የሚሰግድን ሰው 'እንኳን አደረሰህ' እንደማለት ከዚያም የከፋ ነው ብለዋል። . ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) አሁንም ምን ይላሉ ... አንድን ሰው አላህን ለማመፁ ወይም ለክህደቱ አሊያም ለቢድዓው 'እንኳን ደስ ያለህ' የሚል ሰው ራሱን ለአላህ ቁጣ አጋልጧል። . የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ሷሊህ አል-ዑሠይሚን (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው በነዚህ በዓላት ላይ እንዲገኝ ግብዣ ቢቀርብለት ሊቀበል አይገባም ይላሉ። አያይዘውም አንድ ሰው በነሱ በዓል ላይ መመሳሰሉ ወይም ስጦታ መቀባበሉ አሊያም ምግብና ጣፋጮችን መስጠቱ የተከለከለ ነው ይላሉ።
. እውቁ ዓሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) ... ካፊሮችን በነዚህ ክብረ በዓላት መመሳሰል በእነርሱ የውሸት እምነትና ስራ ሰውየው መማረኩን ያሳያል። ይህ ደግሞ ካፊሮች ደካማውን እንዲያሸማቅቁ እና እንዲያጠሙ ተስፋ ይሰጣቸዋል ይላሉ። . ሸይኽ ዑሠይሚንም (ረሂመሁላህ) ... ምንም እንኳ ሰውየው ይህን የሚያደርገው ካለው ለስላሳ ባህሪ ወይም አይናፋርነት ወይም ጓደኝነት የመነጨ ቢሆንም ከወንጀለኝነት አይድንም ይላሉ። እንዳውም ነገርየው እስከ ኒፋቅ እንደሚሄድ እና ከሀድያን በሀይማኖታቸው ኩራት እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ ይገልፃሉ። . መለስ ብለን ከላይ የጠቀስናቸውን በዓላት ስንመለከት ግን እኛ ራሳችን በነዚህ በዓላት ላይ ወይም የቤተሰባችን አባላት አሊያም የምናውቃቸው ሙስሊሞች ይሳተፉ ነበር። ይህ ከባድ ስህተት በየግዜው የከበደ ወንጀል እንዲፃፍብን ምክንያት ሁኗል፤ አላህ ማርታውን ይለግሰን እንጂ! . ከሀድያንም በዚህ ምክንያት የበላይነትና ኩራት እንዲሰማቸው በአንፃሩ አላዋቂ ወንድሞቻችን የበታችነትና ሐፍረት እንዲወራቸው ምክንያት ሁኗል።
. በተጨማሪም በዓላቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ዘፈንና ጭፈራ፣ የሴቶች መገላለጥ፣ የወንድና ሴት መቀላቀል (እንዳውም ለብልግና መፈላለግ) እንዲሁም አስካሪ መጠጥ ስለሚኖርባቸው በዚህ የተሳተፉ ሙስሊሞች እነኝህን ፀያፍና ከባባድ ሐራም ተግባራት እንዲፈፅሙ ሰበብ ሆኗል።
. ይህም ጥቂት ለማይባሉ ሙስሊሞች ከዲናቸው መራቅ፣ ወንጀል ውስጥ መዘፈቅ፣ በቢድዓ መሸወድ እና ከሀድያንን መከተል ብሎም ኩፍር ውስጥ መግባት ምክንያት ሁኗል። . ይህ ሊበቃ ይገባል!
. ሴት እህቶቻችን አሸንዳ ለመጫወት ወይም አበባዮሽ ብለው ሲወጡ 'አይ ይህ የከሀድያን በዓል ነው፤ እኛ ሙስሊሞች ነን። አናከብርም!' ልንላቸው ይገባል። ወንዶች ልጆች 'ሆያ ሆዬ' እንበል ወይም ጅራፍ እናስጩህ ሲሉም 'የለም ይህ በካፊሮች በዓል ነው። በነሱ በዓል መሳተፍ ወንጀል ነው። አላህ ጋር ያጣላናል' ብለን ልንከላቸው ይገባል። ይህን ካላደረግን ግን እኛም የወንጀሉ ዳፋ ይደርሰናል። . ከዚህም ባሻገር በአሸንዳም ሆነ አበባዮሽ ወላ ሆያሆዬ የሚሉ ልጆች መጥተው ሳንቲም ቢጠይቁ በመስጠት ልንተባበራቸው አይገባም። ይህ ከሀድያን አላህን በማመፅ የሚያከብሩት እንደመሆኑ ለነርሱ ገንዘብ ወይም ማበረታቻ መስጠት ወንጀሉን ማበራታት ነው። . አላህ እንዲህ ብሎናል . وَتَعَاوَنُواْ عَلَى الْبَرِّ وَالتَّقْوَى وَلاَ تَعَاوَنُواْ عَلَى الإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَاتَّقُواْ اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ . "በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፤ ግን በኃጢያትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ። አላህንም ፍሩ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና" አል-ማኢዳ 2 . አላህ ባነበብነው የምንጠቀም ያድርገን!
0 Comments