Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አስርቱ የዙል ሒጃ ቀናት part 2

★ በነዚህ በተመረጡ አስር ቀናቶች ውስጥ መልካም ስራዎችን እንድናበዛ መታዘዛችንን ባለፈው ክፍል ላይ በአጭሩ አይተናል አሁን ደግሞ በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ልንተገብራቸው ተነጥለው ከወጡልን የኢባዳ አይነቶች ውስጥ
★ ሀጅ እና ኡምራ ፦ እነዚህ የኢባዳ አይነቶች በአስርቱ ቀናት ውስጥ ከሚተገበሩ የኢባዳ አይነቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ « ከአንድ ኡምራ እስከ ሌላ ኡምራ በመሀከላቸው ያለውን ወንጀል ያብሣል ፣ ትክክለኛ የሆነ ሀጅ ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም»
★ እነዚህን ቀናቶች በፆም ማሣለፍ ፦አስርቱን ቀናቶች ወይም ከአስሩ ስር የቻለውን ያክል መፆም ሡና ነው
የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም « ፊቱን ከጀሀነም እሣት ሠባ አመት አላህ ያራቀው ቢሆን እንጂ አንድ ሙዕሚን በአላህ መንገድ ላይ አይፆምም »
☞ የአረፋን ቀን ግን ሊተወው ወይም ቸል ሊለው የማይገባ ቀን ነው
የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም « የአረፋን ቀን እየተሣሠበ የፆመ ሠው ያለፈወን እና የሚመጣውን አመት ወንጀል አላህ ያብስለታል?

★ ተክቢራ እና ዚክር ማብዛት ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል « በታወቁ ቀናቶች ውስጥ አላህን አውሱ» የታወቁ ቀናቶች የሚባሉት አስርቱ የዙል ሒጃ ቀናቶችን ነው
★ ተውበት ማብዛት
★ ሡና የሆኑ ነገሮችን ማብዛት እና የመሣሠሉት ይገኙት
ተመልሼ እመጣለው
-----
------
------
------------
----------------
… በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚሠሩ ስራዎች መካከል
★ ተውበት ማድረ እንዲሁም ወንጀል የሆኑ ተግባራቶችን መራቅ ወንጀል ከአላህ መራቅን እን መጠላትን ያተርፋልበአንፃሩ ደግሞ አላህን መታዘዝ ወደ አላህ መቃረብን እና የአላህ ውዴታን ያስገኛል
★ በአጠቃላይ መልካም የተባሉ ተግባራቶችን በነዚህ ቀናቶች በብዛት መስራት ለምሣሌ ሠደቃ ፣ ሠላት ፣ ቁርአን መቅራት ፣ በመልካም ማዘዝ ፣ ከመጥፎ መከልከል
★ከፈርድ ሠላቶች ቡሀላ ተክቢራ ማብዛት
ተመልሼ እመጣለው
----
-----------
---------------------
------------------------
… በእነዚህ ቀናቶች ውስጥ ከሚሠሩ ስህተቶች መካከል
★እነዚህን አላህ ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ያላቸውን ቀኖች ከሌላው ቀን ባልተለየ መልኩ ማሣለፍ ፦ አንዳንድ ግለሠቦች ዘንድ እነዚህ ቀናቶች ምንም ቦታ የላቸውም ከዚህም የቸነሣ በነዚህ ቀናቶች ውስጥ መልካም ነገራትችን ለመቸግበር ወይም ወንጀልችን ለመተው አይነሣሱም ነገር ግን የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ብለዋል
" ﻣﺎ ﻣﻦ ﺃﻳﺎﻡ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﺍﻟﺼﺎﻟﺢ ﻓﻴﻬﻦ ﺃﺣﺐ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﻨﻪ ﻓﻲ ﻫﺬﻩ ﺍﻷﻳﺎﻡ ﺍﻟﻌﺸﺮ ."
«ከእኘዚህ አስርት ቀናቶች ውጪ መልካም ስራ አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሚሆንበት ቀን የለም»

☞ በነዚህ ቀናቶች ከሚባሉ አዝካሮች ጋር በተያያዘ መልኩ የሚሠሩ ስህተቶች
★ ተክቢራውን አስርቱ ቀናቶች ከጀመሩበት ቀን አንስቶ አያመ ተሽሪቅ በሚያበቃበት ቀን መጀመር እና መጨረስ አለበት አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል
« ﻭَﻳَﺬْﻛُﺮُﻭﺍ ﺍﺳْﻢَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓِﻲ ﺃَﻳَّﺎﻡٍ ﻣَّﻌْﻠُﻮﻣَﺎﺕٍ»
« የአላህን ስም በሚታወቁ ቀናቶች ስር አውሱ»
አብደላህ ኢብኑ መስኡድ (( ﻓِﻲ ﺃَﻳَّﺎﻡٍ ﻣَّﻌْﻠُﻮﻣَﺎﺕ)) የሚለውን አስርቱ ቀናቶች ናቸው ብሏል
★ ተክቢራው በሚባልበት ወቅት በጀመአ (አውጪ እና ተቀባይ ባለበት ሁኔታ) መባል የለበትም አንድ ላይ ተሠብስበው ቢሉም ሁሉም የየግሉን ይልል ከገጠመ ገጠመ ነው ሆን ብሎ ግን አንድ ላይ ማለት ክልክል ነው
★ የተለያዩ ክላሢካ (ድቤ) እየጨመሩ እየጨፈሩ ማለት አይቻልም ኢባዳ እንደመሆኑ መጠን ለአላህ እየተናነሡ እና እየተዋረዱ በእርጋታ መፈፀም ነው ያለበት
★ በአዝካር ስም ከልክ ያለፋ ሙገሣዎች እና ሽርኪያት የሆኑ ቃላቶችን ከማነብነብም ከሚያነበንቡ ሠዎችም ጋር አብሮ መቀማመጥንም ልንጠነቀቅ ይገባል
★ ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ዘንድ ከመጣው አዝካር ላይ መጨመርም መቀነስም ክልክል ነው ከሣቸው የመጣው አዝካር ይዘቱ ይሄን ይመስላል
- ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ ﻭﻟﻠﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ .
- ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ ﻛﺒﻴﺮًﺍ .
☞ ከሁለቱ የተክቢራ አይነቶች ውጪ ማንኛውንም አይነት አዝካር መጨማመር የተከለከለ ነገር ነው
★ ሤቶች ተክቢራ ሢያደርጉ ድምፃቸውን ቀንሠው መሆን አለበት የሙእሚኖች እናት የሆኑት የነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሚስቶች ተክቢራ ያደርጊ ነበር ሆኖም ድምፃቸውን ግን ከፍ አያደርጉም ነበር

Post a Comment

0 Comments