Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አስርቱ የዙል ሒጃ ቀናት Part 1

አስርቱ የዙል ሒጃ ቀናት
☞ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ከነገሮችሁሉ እሡ ዘንድ በደረጃ ከፍ የሚያደርጋቸው ወይም ከአምሣያቸው የሚለያቸው ነገሮች አሉ ለምሣሌ ከነብያቶች በአጠቃላይ ነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም መረጠ ፣ ከቦታዎች ካእባን ልክ እንደዚሁ ከጊዜያቶችም መርጧል ከተመረጡ ጊዜዎች መካከል አንዱ ከቀናቶች ቡሀላ የምናገኘው የዙልሒጃ ወር ነው ከሷም ውስጥ የመጀመርያዎቹኔ አስርቱ ቀናቶች መረጠ እንዲህም ሢል ማለባት (( ﻭَﻟَﻴَﺎﻝٍ ﻋَﺸْﺮٍ)) ((በአስርቱ ለሊቶች እምላለው)) ከመልዕክተኛውም አንደበት ስለዚህች ቀን እንዲህ ሲሉ መሠማቱ በትክክለኛ ሠነድ መጥቷል
""ﻣﺎ ﻣﻦ ﺃﻳﺎﻡ ﺃﻋﻈﻢ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﻻ ﺃﺣﺐ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﺃﻳﺎﻡ ﺍﻟﻌﺸﺮ، ﻓﺄﻛﺜﺮﻭﺍ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﺘﺴﺒﻴﺢ، ﻭﺍﻟﺘﺤﻤﻴﺪ، ﻭﺍﻟﺘﻬﻠﻴﻞ، ﻭﺍﻟﺘﻜﺒﻴﺮ "
""ከነዚህ አስርቱ ቀናቶች ውጪ አላህ ዘንድ የተላቀ ቀን እና መልካም ስራም ይበልጥ የሚወደድበት ቀን የለም , በአስርቱ ቀናት ውስጥ "ሡብሀነላህ" ፣ "ወልሀምዱ ሊላህ "፣ "ላኢላሀ ኢለላህ " ፣ "አላሁ አክበር" ማለትን አብዙ ""

ይህች አስር ቀን አላህ ዘንድ ደረጃዋ እጅጉኑ ከፍ ያለ ነው ደረጃዋን ከፍ ካደረጉት ነገሮች ውስጥ
★ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ በተከበረው ቁርአኑ ምሎ ባቸዋል (( ﻭَﻟَﻴَﺎﻝٍ ﻋَﺸْﺮ))) ((በአስርቱ ቀናቶች እምላለው))
☞ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ምንግዜም የሚምለው ከበድ ያሉ ጉዳዬችን በሚያስተላልፍበት ወቅትነው የሚምልበትም ነገር እሡ ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ነገር ላይ ነው
★ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ከሌሎቹ ቀናቶች ለይቶ በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ኢባዳዎችን እንድናበዛ ማዘዙ
""ﻣﺎ ﻣﻦ ﺃﻳﺎﻡ ﺃﻋﻈﻢ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﻻ ﺃﺣﺐ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﺃﻳﺎﻡ ﺍﻟﻌﺸﺮ، ﻓﺄﻛﺜﺮﻭﺍ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﺘﺴﺒﻴﺢ، ﻭﺍﻟﺘﺤﻤﻴﺪ، ﻭﺍﻟﺘﻬﻠﻴﻞ، ﻭﺍﻟﺘﻜﺒﻴﺮ "
""ከነዚህ አስርቱ ቀናቶች ውጪ አላህ ዘንድ የተላቀ ቀን እና መልካም ስራም ይበልጥ የሚወደድበት ቀን የለም , በአስርቱ ቀናት ውስጥ "ሡብሀነላህ" ፣ "ወልሀምዱ ሊላህ "፣ "ላኢላሀ ኢለላህ " ፣ "አላሁ አክበር" ማለትን አብዙ ""  
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል!!!

Post a Comment

0 Comments