Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነፃ_አውጣት‬ !


‹‹ ‪#‎ነፃ_አውጣት‬ ! ››
‪#‎አንተ_ሙስሊም_ሆይ‬ !!
በአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማለትም በ ‪#‎ኢስላም‬ መስፈርት
‹‹ አላህ ከአርሽ በላይ ነው›› ያልክ እንደሆን አንተ አማኝ ነህ !
በዐብዱላህ ሃረሪና በተከታዮቹ አሕባሾች መስፈርት ግን
‹‹ አላህ ከአርሽ በላይ ነው›› ያልክ እንደሆን ግን አንተ ከሃዲ ነህ !
‪#‎THE_DIFFERENCE_IS_VISIBLE‬ !
"ነፃ አውጣት!"
by:- bro. Mohammed Ibrahim Ali
ሙዓዊያ ቢን ሐከም አሱለሚ እንዲህ ይላል “ለኔ በኡሁድና ጀዋኒያህ ተራሮች መሀል (በምእራብ መዲና) በአንዲት ባሪያ የማስጠብቃቸው በጎችና ፍየሎች ነበሩኝ፡፡ አንድ ቀን ስመለከት ተኩላ መጥቶ(ከጠባቂዋ) በግ ወሰደባት፡፡ እኔም የአደም ልጅ ነኝና ተናድጄ (ባሪያዬን) መታኋት፡፡ ይህንን ሁኔታም ለነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጥቼ ነገርኳቸው፡፡ ነቢዩም(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ነገሩን በኔ ላይ አካበዱብኝ፡፡
እኔም “የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሆይ ነጻ ላውጣት?” አልኳቸው፡፡
እሳቸውም “ጥራት!” አሉኝና ጠራኋት፡፡
ነቢዩም(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) “አላህ የት ነው?” አሏት
እሷም “በሰማይ!” አለች
እሳቸውም “እኔ ማን ነኝ?” አሏት
እሷም “አንተ የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ነህ” አለች
እሳቸውም “ነጻ አውጣት፤ እሷ አማኝ ነች!” አሉ፡፡
ሙስሊም በሶሂሁ ላይ እንዲሁም በይሀቂ እና አቡ-ዓዋናህ ዘግበውታል፤ ሶሂህ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡ በተጨማሪም አቡ-ዳውድ፣ ኢብን አቢ-ሸይባህ እና ኢብን አቢ-ዓሲም ዘግበውታል፡፡
፨ማስታወሻ፦ ማንኛውም ከበላይ ያለ ነገር ሁሉ እንደ ደመና፣ ሰባት ሰማያት፣ ኩርሲ፣ ዓርሽ እንዲሁም ከዚያም በላይ ያለው ሁሉ ሰማይ በሚል መጠሪያ ይታወቃል። በብዙ ቦታ ቁርዓን ይህን አገላለፅ የተጠቀመበት ሲሆን ለምሳሌ ሱራ አል-በቀራ 22 እንዲሁም ሱረቱ ዙመር 21 ላይ መመልከት ይቻላል። ስለዚህ "በሰማይ" የሚለው የባሪያዋ ምላሽ አንዳንዶች እንደሚያስቡት አላህ ከዓርሽ በላይ መሆኑን የሚቃረን አይደለም የሚደግፍ እንጂ!
መቼም ይህን የመሰለ ግልፅ ማስረጃ ከሶሂህ(ትክክለኛ) ሐዲስ ቀርቦ አላህ ከሰማያት ከፍ ብሎ ከዓርሹ በላይ መሆኑን አልቀበልም የሚል ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡
አላህ ቀናውን ጎዳና ይምራን!