Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የቃዲ ዒያድ በሆነው ተርቲበል መዳሪክ (2/54)] ላይ እንዲህ ያላል:-

የቃዲ ዒያድ በሆነው ተርቲበል መዳሪክ (2/54)] ላይ እንዲህ ያላል:-
ከኢማሙ ማሊክና ከባልደርቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለን ሳለ ከ‹ናስቢዒን› የሆነ አንድ ሰው ወደኛ መጣና እንዲህ አለን:-
‹‹ እኛ አካባቢ ‹ሱፊይ› ተብለው የሚጠሩ ሰዎች አሉ እህል በጣም ከበሉ በኋላ ባለብዙ ስንኝ የሆነ ግጥም እየገጠሙ ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ..››
ኢማሙ ማሊክም:- ‹‹ እነዚህ ሰዎች ህፃናቶች ናቸው ?..›› ብለው ጠየቁ
ሰውየውም:- ‹‹ በጭራሽ አይደሉም!..›› አላቸው
ኢማሙ ማሊክም:- ‹‹ ምን አልባት ወፈፌዎች ይሁኑ ? ..››
ሰውየውም:- ‹‹አረ በጭራሽ ትላልቅ ሰዎች ናቸው ደግሞም ጤነኞችም ናቸው.›› (ይሄን ሲያደርጉ ሲቀር)
ኢማም ማሊክም:- ‹‹በኢስላም ውስጥ እንደዚህ የሚያደርግ ሰምቼም አላውቅም.›› አሉ::
ሰውየውም ቀበል አድርጎ:- ‹‹ በርግጥም የሚያደርጉት ይመገቡና ተነስተው ይጨፍራሉ አንዳንዶቹ አናታቸውን ሲመቱ አንዳንዶቹ ደሞ ፊታቸውን ይመታሉ ››
ኢማም ማሊክም ሳቁና ተነስተው ወደቤታቸው ሄዱ ። የኢማሙ ማሊክ ባልደረቦቹም ለሰውየው እንዲህ አሉት:-
‹‹ አንተ ከኛ (ከኢማሙ ማሊክ) ባልደረቦች የተሻልክ ዕድለኛ ነህ ። ከኢማሙ ማሊክ ጋር ‪#‎ለሰላሳ_አመታት‬ (30) ተቀማምጠናል ከዚህ ቀን ውጪ ‪#‎ስቀው‬ አይተናቸው አናውቅም.. ››
_____________
[ ቃዲ ዒያድ ተርቲብ አል መዳሪክ ሊ'ቃዲ ኢብኑ ዒያድ (2/54)]
_____________
ኢማሙ ማሊክ የኛ ሃገሮቹ ቢያዩ ምን ይሉ ነበር ?
ጫቱን በልተው ድቤ እየደለቁ ተነስተው ዱብ ዱብ የሚሉት ?
ሰርግ ላይ ድቤ ተሸክመው መጥተው እየተሽከረከሩ የሚጨፍሩት ?
ጫቱን ቅመው ክብ ሰርተው የሽርክና ኹራፋት ግጥሞችን የሚያነበብንቡት ?
በየመኪናው ትራንፖርቱ በየስልክ ሚሞሪ ውስጥ ይሄን ግጥም እየሰሙ የሚያጣጥሙት?
______
ኢማሙ ማሊክ አሁን ቢኖሩ ምን ይሏቸው ነበር ይሁን ?