Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተሸቡህ (መመሳሰል) በኡስታዝ መሀመድ ሀሰን (አቡ አብደላህ) ሃፊዘከሏህ


ተሸቡህ (መመሳሰል)
በኡስታዝ መሀመድ ሀሰን (አቡ አብደላህ) ሃፊዘከሏህ
ተሸቡህ ወይም መመሳሰል ፦ ማለት ከእስልምና ሃይማኖት ውጭ ያሉ ሃይማኖቶች በሙሉ ለራሳቸው ብቻ የሚሰሯቸው ማንኛውም ስራ ሙስሊሙ ከሰራው ተሸቡህ ይባላል።
ይህንን አስመልክቶ ታላቁ ዓሊም ሼህ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ "ካፊር የሚታወቅበት ስራ ላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከሰራው እና ከተቀበለው ከእነሱ ጋር መመሳሰል ነው" አሉ።
ሼህ ኢብኑ ተይሚያ ደግሞ እንደዚህ ይላሉ፦ "የውጭ ገጽታ ከአንድ አካል ጋር መመሳሰል በውስጥ የሚመሳሰሉ ሰዎች አንድ እንዲሆኑ እና እንዲቀራረቡ በሁሉም ነገር እንዲስማሙ ያደርጋል።"
ብዙህን ጊዜ ተሸቡህ የሚታየው በበዓላት እና በደስታ ሰዓቶች ላይ ነው። ምክኒያቱም በዓል ማለት ከሃይማኖት መገለጫዎች ሁሉ ትልቁ እና ዋናው ነው። አብዛኛው ሙስሊም ህብረተስብ በማወቅም ሆነ ባለ ማወቅ እንደዚህ አይነት የተከለከሉ ስራዎችን ሲሰሩ እና ሲያደንቁ ይታያሉ። ይህንን አስመልክቶ ዲናችን ሙሉ መሆኑንና ምንም የሚጨመር እና የሚቀነስ አለመኖሩን እንዲሁም አንድ ሙስሊም ከካፈር ጋር መመሳሰል እንደሌለብት በብዙ በቁርዓንና በሀዲስ ቦታዎች ላይ ተገልጾል።
ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَـٰمَ دِينًۭا ۚ فَمَنِ ٱضْطُرَّ فِى مَخْمَصَةٍ غَيْرَ مُتَجَانِفٍۢ لِّإِثْمٍۢ ۙ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ ﴿٣﴾
ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ። በረሃብ ወቅት ወደ ሃጢአት ያዘነበለ ሳይሆን (እርም የኾኑትን ለመብላት) (የተገደደ ሰውም ይብላ)። አላህ መሀሪ አዛኝ ነውና።
ስለዚህ አላህ የኛን ሃይማኖት ከየትኛውም ሃይማኖት እንዳስበለጠ ነግሮን ሳያበቃ ይህን የነብዩን ዑማ አወድሷል። አሏህ እንዲህ ይላል " ወደ እዚህ ዓለም ለሰው ልጆች ከተፈጠሩ ሰዎች መሀል በጣም ምርጥ የሆናችሁ ናችሁ። በመልካም ታዛላችሁ ከመጥፎ ትከለክላላችሁ በአላህም ታምናላችሁ" ሌሎች ግን ሙንከር አይተው መለወጥ አልቻሉም። ከመቃውም ይልቅ ዝምብለው አብረው መቀጠል እና መነዳት ጀመሩ አላህም ረገማቸው። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዑማቸው ምርጥ መሆኑን ሲናገሩ ' እኛ አመጣጣችን የመጨረሻ ደረጃችን ግን የመጀመርያ ነው።" የቂያማ ቀን ኪታብን ከእኛ በፊት ከመሰጣታቸው በፊት። ኢብኑ ሀጀር አስቀላኒ ይህን ሃዲስ በኪታባቸው ላይ ሲያብራሩት እንዲህ ይላሉ፦
"ይህ ዑማ አመጣጣቸው የመጨረሻ ቢሆንም በዱኒያ ረገድ በአኺራ ግን የመጀመሪያ ናቸው መጀመሪያ ፍርድ የሚፈረድላቸው ይህ ዑመት ነው። የመጀመሪያ ጀነት የሚገቡትም በህዝብ ደረጃ የነብዪ ዑመት ናቸው።" አሁንም አላህ በመጽሐፉ እንዲህ ይላል ፦
"لُعِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ عَلَىٰ لِسَانِ دَاوُۥدَ وَعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ ۚ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوا۟ وَّكَانُوا۟ يَعْتَدُونَ ﴿٧٨﴾ كَانُوا۟ لَا يَتَنَاهَوْنَ عَن
مُّنكَرٍۢ فَعَلُوهُ ۚ لَبِئْسَ مَا كَانُوا۟ يَفْعَلُونَ"
"በኢሳ እና በዳውድ አንደበት ተረገሙ ድንበር ስለ ሚያልፉ እና የአላህ መመሪያ ስለ ማይጠብቁ ይሰሩት የነበረው ጥፋትና ወንጀል አንዱ ሌላውን አይከለክልም ነበር"
የሁዳዎችንና ነሷራዎችን አላህ በእነሱ ላይ የመንፈስ ድህነትን ወስኖባቸወል፤ ወራዳ አድርጓዎቸዋል፤ በዱኒያም ምንም ክብር እንደሌላቸውና የአላህ ቁጣ እንደወረደባቸው አላህ ራሱ ነግሮናል። እና ታዲያ አላህ የረገማቸውን እና የጠላቸውን ለምን ወዳጅ አድርገን እንይዛለን ለምንስ ከእነሱ ጋር እንመሳሰላለን? አላህ እንዲህ ይላል "በእርግጥም ለአንተ ቁርዓን ሰጥቻዓለሁ ስለዚህ በዚህ ልትኮራና ልትመሰጥ ይገባል ይህን ከረሳህ ግን ችላ ካልክ እነዛ ዱንያን ብቻ ለሰጠናቸው ሰዎች አይንህን አስረዝም በእነሱ ብልጭልጭ አትቅና" አሁንም በሌላ የቁርዓን አያዕ በጥቅሉ ከእነሱ ጋር እንዳንመሳሰል አስጠንቅቋል በተለይ በልብ ድርቀት እንዳንመሳሰል እንዲህ ይላል፦ "ወንጀል በማብዛትና በማመጽ ከእነሱ ጋር ከመመሳሰል መቆጠቢያ ጊዚያቸው አልደረሰም እንዴ" ይለናል አላህ በቁርዓኑ።
۞ أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلْحَقِّ وَلَا يَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَـٰبَ مِن
قَبْلُ فَطَالَ عَلَيْهِمُ ٱلْأَمَدُ فَقَسَتْ قُلُوبُهُمْ ۖ وَكَثِيرٌۭ مِّنْهُمْ فَـٰسِقُونَ" ﴿١٦﴾
"ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርአንም ለወረደው ልቦቻቸው ሲፈሩ እንደዚህም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው።"
እስቲ ወደ ሀዲስ እንዙርና ስለ መመሳሰል የተጠቀሱትን እንይ፦ የአሏህ መልዕክተኛ በሰሂህ ሀዲስ እንዲህ ይላሉ " "من تشبه بقومين فهو مينهم
“ከአንድ ሰው ጋር የተመሳሰለ በእርግጥ ከእነሱ ጋር ነው"። አኽረጀሁ አህመድ አልባኒ ሀዲሱን ሰሂህ ብለውታል ።
ሼህ ኢስላም ኢብን ተይሚያ ይህን ሀዲስ ሲፈስሩት "የውጭ ገጽታ መመሳሰል ውስጥ ፍቅር እና ውዴታን ያስከትላልና"
ነብዩ በሌላ ሀዲስም እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ በፊት የነበረውን መንገድ ትከተላላችሁ ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ እንዲሁም የአርጀኖ እንስሳ ጉርጓድ አለ እዛ ቢገቡ እንኴን ተከትላችሁ ትገባላችሁ አሏቸው። ሰሃቦችም ጠየቁ የሁዳንና ነሷሯ ነው ወይ? ነቢዩም “ታዲያ ማነው"
ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ቀናት ሲናገሩ "ልዩ ቀናችን ጁምዓ ነው አሉ ከዛም በሚቀጥለው የሁዳዎች ናቸው ቀጣዩ ደግሞ ክርስቲያኖች ናቸው።" አሉ
ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ከካፊር ጋር መመሳሰል እንደሌለብን አላህ እና መልክተኛው በቁርዓን እና በሀዲስ አስጠንቅቀዋል። ማለትም፦
- ከሚዘጋጀው ምግብ ከመብላት መቆጠብ።
- ከእነሱ ጋር ያለን ግኑኝነት መቀነስ። ከቻልን ቀኑን መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ በመውጣት ዒባዳዎችን በማብዛት፤ ዚክርን በማዘውተር፤ ቁርዓንን በመቅራት፤ ኪታቦችን በመሞጠል እና ሱናዎችን በማብዛት ከተሸቡህ እንራቅ።
- ሰላምታን አለማብዛትና "እንኳን አደረሰህ" የሚለውን ቃል አለመጠቀም።
- ስጦታን ከመስጠትም ሆነ ከመቀበል መቆጠብ።
በአጠቃላይ እነሱ ከሚሰሩት ስራ ልንርቅ፤ በቀልባችን በመጥላት ከተሸቡህ ልንርቅ ይገባል። ይህንን አስመልክቶ ነቢዩ እንዲህ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አሉ፦ "አንድ ሰው ከሚወደው ሰው ጋር ነው የሚቀሰቀሰው" ካፊር የወደደ ከካፊር ጋር ሙስሊም የወደደ ከሙስሊሙ ጋር ይቀሰቀሳል። አላህ ይጠብቀን።
በመጨረሻም አንድ የኡመር ኢብን ኸጣብ ሀዲስ ልጥቀስና ንግግሬን ልጨርስ፦ ኡመር ኢብን ኸጣብ እንዲህ ይላል
" የሁዳ እና ነሷራዎች በግላቸው ሃይማኖታዊ በሆነ ባህላቸው እና ሌሎችም በዓል ላይ ራቋቸው እነሱ በሚሰበሰቡበት ጊዜ የአላህን ቁጣ በእርግጥ በእነሱ ላይ ይወርዳልና በዛ ሰዓት እነሱ ላይ ያወረደውን እናንተ ላይ እንዳያገኛችሁ እፈራለሁእና በእነሱም ቋንቋ አትመሰጡ መመሰጣችሁ ስነ ምግባራችሁ ላይ ተጽዕኖ ስለ ሚያሳድርባችሁ።”
ላልሰማ እናሰማ። መልካምን ያመላከተ እንደሰራ ይቆጠራል።
አላህ ሰምተው ከሚሰሩት ያድርገን።
ወደ ዲናቸው ከሚመለሱ አላህ ያድርገን።
በዲናቸው የሚኮሩ ሰዎች አላህ ያድርገን።