Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“አይነ'ላህ?” የሚለው ሐዲስ እና በሱ ዙሪያ የአህባሾች ማምታቻ

“አይነ'ላህ?” የሚለው ሐዲስ እና በሱ ዙሪያ የአህባሾች ማምታቻ


ሐዲሱ የሚከተለው ነው…

ሙዓዊያ ቢን ሐከም አሱለሚእንዲህ ይላል “ለኔ በኡሁድና ጀዋኒያህ ተራሮች መሀል (በምእራብ መዲና) በአንዲት ባሪያ የማስጠብቃቸው በጎችና ፍየሎች ነበሩኝ፡፡አንድ ቀን ስመለከት ተኩላ መጥቶ (ከጠባቂዋ) ፍየል ይስድባታል፡፡ እኔም የአደም ልጅ ነኝና ተናድጄ (ባሪያዬን) መታኋት፡፡ ይህንንሁኔታም ለነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጥቼ ነገርኳቸው፡፡ ነቢዩም(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ነገሩን በኔ ላይ አካበዱብኝ፡፡


እኔም “የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) ሆይ ነጻ ላውጣት?” አልኳቸው፡፡
እሳቸውም “ጥራት!”አሉኝና ጠራኋት፡፡
ነቢዩም(ሰለላሁ ዓለይሂወሰለም) “አላህ የት ነው?” አሏት
እሷም “በሰማይ” አለች
እሳቸውም “#እኔ ማን ነኝ?”ሲሏት
እሷም “#አንተ የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ነህ”አለች
እሳቸውም “ ነጻ አውጣት እሷ አማኝ ነች” አሉኝ፡፡


ሙስሊም በሶሂሁ ላይእንዲሁም በይሀቂ እና አቡ-ዓዋናህ ዘግበውታል፤ ሶሂህ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡ በተጨማሪም አቡ-ዳውድ፣ ኢብን አቢ-ሸይባህ እናኢብን አቢ-ዓሲም ዘግበውታል፡፡ 

መቼም ይህን የመሰለግልፅ ማስረጃ ከሶሂህ(ትክክለኛ) ሐዲስ ቀርቦ አላህ በሰማይ መሆኑን አልቀበልም የሚል ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ወንድምዬ! ይህችንባሪያ በዚያ በምርጡ የነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አንደበት “እሷ አማኝ ነች” ያስባላት ምን ሆነና? “አላህ በሰማይ ነው፡፡አንተም የአላህ መልእከተኛ ነህ” ብላ በመመስከሯ አይደል እንዴ አማኝነቷ በነቢያት አለቃ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አፍ ያረጋገጠላት፡፡ምን አለ እኔ እሷን ብሆን?

የሚገርመው ግን አንዳንድየኔ ቢጤ የዋሆች ይህን ሀዲስ ሲሰሙ የሚደናገሩባቸው ጥቂት ውዥንብሮች አሉ፡፡ ሐዲሱ ሶሂህ መልእክቱ ግልጽ ቢሆንም እነኝህ ወንድሞችግር ስለተሰኙ በአላህ ፈቃድ ውዥንብሩን እናስወግድላቸው፡፡
ተከተሉኝ …

አንደኛ ውዥንብር ፡-
የዋሆቹ እንደሚሉት “ስለ አላህ በሰማይ መሆን የሚያወራው ሐዲስ ኢዝጢራብ አለበትወይም የተምታታ ነው” ሲባል ሰምተናል አሉ፡፡ ለምን? ሲባል “በሙስነድ” እንደተዘገበው ባሪያዋ “አላህ የት ነው?” የሚለው ጥያቄሲቀርብላት “ወደ ሰማይ አመለከትች” የሚል ዘገባ አለ፡፡ ስለዚህ እዚህ ጋር በሙስነድ የተዘገበው “ወደ ሰማይ አመለከተች” እያለእዚህ ጋር ደግሞ በሙስሊምና ሌሎች ዘጋቢዎች የተዘገበው “በሰማይ ነው” ብላ መልሳለች ማለቱ ስለሚምታታ ሐዲሱን አንቀበልም ዶኢፍነው አሉ”፡፡ አስተውል! ይምታታል ያሉት ባሪያዋ ለቀረበላት ጥያቄ አመላለሷሲዘገብ በአንደኛው ዘገባ “ወደ ሰማይ አመለከተች” የሚለውና በሌላኛው ዘገባ ደግሞ “በሰማይ ነው” ብላለች የሚሉትን ቃላት ነው፡፡
Take this asa base point:- በሙስጠለሀል ሐዲስ(በሐዲስ ጥናት ዘርፍ) እንደሚታወቀው በአንድ ሐዲስ ላይ ዘጋቢዎቹ በሰነዱ(ማለትም የሐዲሱአስተላላፊዎች ሰንሰለት ዝርዝር) አሊያም በመትኑ(በሐዲሱ መልእክት) ላይ ማስማማት ወይም የተሻለውን ማውጣት በማይቻልበት ሁኔታዘገባዎቹ ከተቃረኑ ሐዲሱ “ሙዝጠሪብ”/የተምታታ ይባላል፡፡

ለምሳሌ በአንዱ ሰነድየመጣውን ሐዲስ ያስተላለፉት ዘጋቢዎች ተርታ በሌላኛው ሰነድ ሙሉውን ወይም በከፊሉ ተዘባርቆ ቢመጣ ወይም ሐዲሱ በአንዱ ሰነድ የተቀጠለበሌላኛው ድግሞ የተቋረጠ ሆኖ ቢዘገብ ወይም መትኑ/መልእክቱ ላይ የተጠቀሱ አንኳር ነጥቦች በአንዱ ዘገባ ያለው ከሌላው ጋር ከተጋጨይህ ሐዲስ “ሙዝጠሪብ” ወይም የተምታታ ይባላል፡፡ በመሆኑም የተጋጩትን ዘገባዎች ማስማማት እስካልተቻለ አሊያም ከተጋጩት ዘገባዎችመካከል አንደኛው ዶዒፍ ሆኖ ሌላኛው ተቀባይነት እስካላገኘ ድረስ ሁሉም ዘገባ በኢዝጢራቡ ምክንያት ይዶእፋል/ደካማ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል በዘገባዎቹላይ ኢዝጢራቡ ያለው መትኑ/መልእክቱ ላይ ሆኖ የተምታተው ነጥብ በሐዲሱ መልእክት ላይ ተፅእኖ የማያሳድር እስካልሆነ ድረስ በሁሉምሰነዶች የመጣው ሐዲስ ዶዒፍ/ደካማ ይሆንና ለማስረጃነት የማያገለግል ይሆናል፡፡ (ለበለጠ ትንታኔ የሸይኽ አህመድ ሻኪርን አል-ባዒሱል-ሐሲስወይም የሸይኽ ኡሰይሚንን ሸርህ መንዙመቱል በይቁኒያ ይመልከቱ)

ወደ ጉዳያችን እንመለስና..ሰዎቹ የሚሉት እንግዲህ “ይህ ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) “አላህ የት ነው” ብለው በጠየቁበት ሐዲስ የባሪያዋ አመላለስ በአንዱዘገባ የመጣው ከሌላኛው ጋር ስለሚጋጭ እንደምንም ይህን ሐዲስ ከዶዒፍ ተርታ መድበን ከፊታችን ዞር እናድርገው ነው” ሆይ ሆይ!የምን ሩጫ ነው? “ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” ነው ነገሩ፤ እስቲ ቀስ እንበልና የሰዎቹን አሉባልታ በመረጃ እናበጥረው፡፡

መልስ አንድ፡-

በሙስነድ የተዘገበው“ወደ ሰማይ አመለከተች” የሚለው ሐዲስ ሰነዱ ጤነኛ(ዶዒፍ ያልሆነ) እስከሆነ ድረስ በሙስሊም እንዲሁም በሌሎች ዘጋቢዎች ከተዘገበው“በሰማይ” ብላ መለሰች ከሚለው ሀዲስ ጋር ምንም አይጋጭም፡፡ ምክንያቱም በሁለቱም ሐዲሶች መካከል ምንም የመልእክት መቃረን አይታይምና!እንደውም ሁለቱም አላህ በሰማይ መሆኑን ያመላክታሉ እንጂ የተምታታ መልእክት አያስሰተላልፉም፡፡ ወደ ሰማይ ማመልከቷም ሆነ በአፏበሰማይ ነው ብላ መናገሯ በሁለቱም አገላለጽ የአላህ መገኛ ከሰማያት በላይ መሆኑን ከማመላከት ውጪ የሚያሳየው ምንም መምታታት ወይም“ኢዝጢራብ” የለም፡፡
ስለሆነም ከላይ asbase point እንደተጠቀሰው ሁለት ዘገባዎች መትን/መልእክት ላይ የተጠቀሱ ነጥቦች ማስማማት በሚቻል መልኩ ቢለያዩ የኢዝጢራብሁክም ስለማያርፍባቸው ይህን ሐዲስ ሙዝጠሪብ ነው ብሎ ከዶኢፍ(ደካማ) ሰነዶች መንጋ ለመዶል የሚደረገው ጥረት መና ይቀራል ማለትነው፡፡
ለነገሩ ሐዲሱ ዶዒፍቢሆን ኖሮ ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ኢማሙ ሙስሊም በሶሂህ/በትክክለኛ ሐዲሶች/ መዝገቡ ላይ ባላሰፈረው ነበር፡፡ የሚደንቀው ግን ሙስሊምከዘገበው ሰሂህ ሀዲስ ጋር ይጋጫል ተብሎ የሚወራለት የሙስነድ ዘገባ ራሱ ጤና የጎደለው ነው፤ መልስ ሁለትን ይመልቱ …

መልስ ሁለት፡-
ይህ መልስ" አይነ'ላህ"/አላህ የት ነው የሚለው ሐዲስ "ሙዝጠሪብ"/የተምታታ ነው ብለው ለሚከራከሩ ሁሉ ወገብየሚቆርጥ ነው፡፡ ምክንያቱም በሙስነድ የተዘገበው ማለትም ስትጠየቅ “ወደ ሰማይ አመለከተች” የሚለው ሐዲስ ከሌላ ሶሂህ ከሆነ ሐዲስጋር ሊነፃፀር ቀርቶ ለራሱም ሰነዱ ጤነኛ ያልሆነ ደካማ ሐዲስ ነው፡፡ ይህ የሆነውም በሐዲሱ ሰንሰለት ውስጥ/ሐዲሱን ካስተላለፉትሰዎች መካከል/ አንዱ ዓብደረህማን ቢን ዓብደላህ ቢን ዑትባህ ቢን መስዑድ አል-ኩፊ የሚባል በሂፍዙ ደካማ የሆነ (የሐፈዘው ሐዲስየተዘባረቀበት) ግለሰብ በመኖሩ ነው፡፡(ሲየር አዕላም አኑበላእ) በመሆኑም በሙስነድ የሰፈረው ዘገባ እንኳን በሶሂህ ሙስሊምና በሌሎችከተዘገበው ሐዲስ ጋር ተነፃፅሮ ያንን ግልጽ ሐዲስ “ሙዝጠሪብ” ሊያደርግ ቀርቶ ለራሱም ቀጥ ብሎ የማይቆም ደካማ/ዶኢፍ በመሆኑውዝግቡ ያከትምለታል፡፡ አለቀ ደቀቀ!
እናም አላህ ከሰማይበላይ መሆኑን የሚጠቁመው በሰሂህ ሙስሊምና በሌሎች ሰነዶች የተዘገበው የመጀመሪያው ሐዲስ ሰሂህነቱን ጠብቆ ያለምንም ጥርጥር ይቀጥላልማለት ነው፡፡ አልሀምዱሊላህ!

መቼም ከዚህ ምላሽ ኋላየሚያጉተመትም ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ሆኖም የዋሆቹ የሰመጡበት ውዥንብር አላበቃምና ሌላም ግር ያላቸውን ነገር ይጠቅሳሉ፡፡እስቲ እንየው …

ውዥንብር ሁለት፡-

አንዳንዶች እንዲህ ሲሉሰምተናል አሉ “ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይህችን ባሪያ “አላህ የት ነው?” ብለው መጠየቃቸው `የአላህ ሀይል ምን ያህልነው?` እንደማለት ነው፡፡ እሷ ደግሞ “በሰማይ ነው” ማለቷ `የአላህ ሃይሉ እስከ ሰማይ ነው` ብላ ለመመለስ ፈልጋ ነው” አሉ፡፡ሱብሀን አላህ! አሁን ይሄ እውን ያደናግራል? ነው ወይስ ውዥንብር ጠፍቶ ነው? አይ የየዋህ ነገር “ስጋ ቁጠር ቢሉት ‘ጣፊያ አንድ’አለ” አለ ያገሬ ሰው!
ውዥንብሩ ገብቷችኋል?እርግጥ ነው እጅግ ደካማ ውዥንብር ነው፡፡ ሆኖም ሰዎቹ በብዥታው መደናገራቸው ከሀቅ ስላገዳቸው ቀስ አድርገን ካሉበት መደናገርልንገላግላቸው ይገባልና ውዥንብሩ ግልጽ እንዲሆን ትንሽ እናብራራው …
ነገሩ እንዲህ ነው፡-አንዳንዴ በቋንቋ የአንድን አካል ሀያልነት፣ ግነት ወይም የሰውን ምኞት የመሳሰሉትን ለመጥቀስ “ሰማይ” የሚለውን ቃል ከሌሎች የማጋነኛቃላት ጋር በማጀብ እንጠቀማለን፡፡ ለምሳሌ “ሰማይ ጠቀስ ፎቅ!”፣ “ሰማይ ደርሶ ተፈጠፈጠ!”፣ “ልቡ ሰማይ ነው”፣ “እሱማ ሰማይደርሷል!” የመሳሰሉት … ፡፡ በምሳሌው ላይ እንደምትመለከቱት “ሰማይ” የሚለው ቃል በመሰረቱ የሚጠቁመው ከበላይ ያለን ነገር ቢሆንምነገሮችን ለማጋነን ሲባል በትውስትነት ከሌሎች ቃላት ጋር “አገባቡን” ጠብቆ አንዳንድ መልእክቶችን ለማስተላለፍ ይረዳል፡፡
እንግዲህ ሰዎቹ ከላይያሳለፍናቸውን ቋንቋዊ ምሳሌዎች መሰረት አድርገው “ምናልባት ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ባሪያይቱን ሲጠይቋት እንደው ምናልባትእሷም ስትመልስ የፈለገችበት መልእክት የአላህን ሀያልነት ለመግለጽ ሊሆን ይችላል” እያሉ ነው ግራ ገብቶናል የሚሉት፡፡ አሁን ውዥንብራቸውግልጽ ነው አይደል?

መልስ
አስተውል “ጥያቄው ገብቶህመልሱ ካልገባህ አደጋ ነው” ይላል ኡስታዝ ኤልያስ ስለዚህ መልሱን በጥሞና ተከታተል፡፡
የመጀመሪያው ምላሽ“ሰማይ” የሚለው ቃል በቋንቋ ደረጃ በአንዳንድ አገባቦች የነገሮችን ግነት ለመጠቆም ይመጣል፡፡ ሆኖም ቦታን የሚያመላክቱ ቅጥያዎችከእርሱ ጋር ተቆራኝተው ከመጡ ፍፁም መሰረታዊ መልእክቱን ይይዛል እንጂ የግነት አሊያም ሌላ የትውስት ግልጋሎት አይኖረውም፡፡ ለምሳሌልክ በሐዲሱ ላይ እንዳለው መገኛን አመልካች የሆነው በዓረብኛው የ“ፊ” በአማርኛው የ”በ” ቅጥያ አብሮት ሲመጣ የሚወራlት ነገርየት እንደሚገኝ ይጠቁማል እንጂ ውዥንብሩን እንደሚነዙት አካላት አተረጓጎም በምንም አይነት መልኩ ኃያልነትን አይጠቁምም፡፡ ምሳሌልስጣችሁ
“አውሮፕላኑ በሰማይበረረ” ምን ትረዳላችሁ? … ግልጽ ነው፡፡ አውሮፕላኑ ሰማይ በሚባለው አካል ላይ እየበረረ መሆኑን ትረዳላችሁ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ“በ” የምትለዋ ቦታን አመልካች ቅጥያ ከሰማይ ጋር ተያይዛ መምጣቷ መገኛን እያመለከተች መሆኑ ነው፡፡ በዚህ አይነት አገባብ የሚመጣዓረፍተ ነገር የሚያመለክተው መገኛን በመሆኑ በሀዲሱ ላይ ባሪያይቱ የመለሰችው መልስ ማለትም “አላህ የት ነው?” ስትባል “በሰማይ”ማለቷ የማያወላዳ ትርጓሜ ይኖረዋል ማት ነው፤ እሱም “አላህ ከሰማያት በላይ” መሆኑ የሚገልፅ ነው፡፡
የሚገርመው “በሰማይ”የሚለውን ምላሽ ከቀረበው ጥያቄ ጋር ስታቆራኘው ጭራሽ ሰዎቹ የሚነዙት ውዥንብር ወድቅ መሆኑን ትረዳለህ፡፡ ጥያቄው “የት … ”መልሱ ደግሞ “በ…” የሚል ሲሆን በቁርጥ ከምልልሱ የምትረዳው የሚጠየቀው ነገርን መገኛ ለማወቅ እንደሆነ ነው፡፡ ለዛም ነው ውዥንብሩእጅግ ደካማ፣ የማይረባ እና ውድ የሆነውን ጊዜያችንን የሚያባክን የሆነው፡፡ ሆኖም መልሱን አስፍረናል፤ ወሊላሂል ሐምድ፡፡
ያ ጀመዓ! እነኝህ ሰዎችበዚህ ውዥንብር ሲምታቱ የሰሩትን ስህተት አያችሁ? “በሰማይ ነው” የሚለውን ቃል በማይሆን መልኩ ሲተረጉሙ የአላህን ሐይል “እስከሰማይ” ብለው ገደቡት! ከባድ ስህተት!!! አላሁ ሙስተዓን፡፡
ሰዎቹ በቀላሉ ውዥንብሩአይለቃቸውም ቅር ቅር የሚላቸው ነገር ይኖራል፡፡ ከስሜት የተቆራኘ ነገር ቶሎ አይለቅማ፡፡ አሁንም በዚህ ሐዲስ የተጠቀሰውን የአላህከሰማይ በላይ መሆን እንዳይቀበሉ የጋረዳቸው አንድ የቀረ ውዥንብር ይጠቅሳሉ፡፡ ይኸውም …

ውዥንብር ሶስት
ሰዎቹ “ባሪያዋ ለቀረበላትጥያቄ ስትመልስ “ፊ ሰማእ/በሰማይ ነው” ማለቷ እኮ የአላህን መገኛ በሰባቱ ሰማይ ውስጥ እንደ መገደብ ነው፤ ይህ ደግሞ ለአላህልዕልና የማይገጥም ስለሆነ ሐዲሱ ዶዒፍ ነው” አሉ፡፡ ሲላ እነዚህ ሰዎች ሐዲሱን ዶዒፍ ለማድረግ ምን አንጦለጦላቸው? ይህ ሐዲስዶዒፍ ቢሆን እነኳ አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን የሚጠቁሙ ማስረጃዎች እልቆ-መሳፍርት ናቸው፡፡ ወይ ልፋት!
ግን የሚገርመው እነኝህሰዎች በዚህ የማይረባ ውዥንብር ሲቀዣበሩ ቁርዓን ምን እንደሚላቸው አለማስተዋላቸው ነው፡፡

መልስ፡-
እንደሚታወቀው ሰማይማለት ሁለት ትርጓሜን ይይዛል፡፡ አንደኛው ትርጓሜ፡- ሰባቱ ከበላያችን የሚገኙት ጠጣርና ግዙፍ የአላህ ፍጡራን የሚያመላክት ሲሆንሁለተኛው ትርጉሙ ደግሞ ማንኛውም ከበላይ ያለ ነገር ማለትም እንደደመና፣ ሰማያት፣ ዓርሽ፣ ኩርሲ የመሳሰሉትን ሰማይ የሚለው ቃልበአንድነት ይጠቁማል፡፡ ይህንንም አላህ በቁርአኑ ነቢዩም(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሐዲሳቸው ተጠቅመውበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ጆንያሙሉ ማስረጃ ማቅረብ ቢቻልም ፅሁፉ እንዳይረዝም አንድ ምሳሌ ብቻ ልጥቀስ
أَلَمْ تَرَ أَنَّاللَّهَ أَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً [٣٩:٢١]
“አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደ አላየህምን?” ዙመር 21
በእርግጥም አላህ ዝናብንማውረዱን አይተናል! አስተውል፤ እዚህ ጋር ዝናብ የሚወርደው ከደመና ቢሆንም አላህ ደመናን ሰማይ ብሎ ጠርቶታል ምክንያቱም በዓረብኛቋንቋ ከበላይ ያለ ነገር ሁሉ ሰማይ በሚለው መጠሪያም ስለሚገለፅ፡፡
ስለዚህ ያቺ አማኝ ባሪያከነቢያችን “አላህ የት ነው?” የሚለው ጥያቄ ሲቀርብላት “በሰማይ ነው” ብላ መመለሷ በፍፁም "አላህ በሰባቱ ጠጣር ሰማያትውስጥ ነው" የሚል መልእክትን አያስይዝም፡፡ ይልቁኑ "ሰማይ" የሚለው ቃል ከበላይ ያለን ነገር ሁሉ የሚያካትትትረጓሜም አለውና የልጅቷ መልስ አላህ ከሰማያት በላይ ልክ እራሱ በቁርዓኑ እንደገለፀው ከአርሹ በላይ ከፍ እንዳለ የሚገልጽ መልስነው፡፡ አላሁ አክበር!

በመጨረሻም ሰዎቹ እንዲያምኑውስጣቸው ላይ አንድም ቅር የሚያሰኛቸው ነገር መኖር የለበትምና እዚህ ጋር ሊያነሱት የሚችሉትን ጥያቄ መልሼ ልለፍ፡፡
እንዲህ ይላሉ “ታዲያ‘በሰማይ’ በሚለው ቃል የተፈለገበት ‘ከሰማያት በላይ' ማለት ከሆነ ባሪያዋ ስተመልስ 'ፊ ሰማእ’ ከምትል ለምን ‘ዓለ ሰማእ’አላለችም?" የሚል ነገር ያነሳሉ፡፡ መልሱ ቀላል ነው፡፡ ግን ጥያቄው ያልገባን ካለን ለማብራራት ያክል፤ “ፊ ሰማእ” ስትል“ፊ” የምትለው የዓረብኛ ቃል “ውስጥ” የሚለውን ትርጉም ታስይዛለች ስለዚህ “ፊ ሰማእ” ማለት “በሰማይ ውስጥ” ማለትን ስለሚያስይዝ“አላህ በሰማይ ውስጥ ነው” የሚል መልእክትን ያስይዛልና ቅድም ከተገለፀው ጋር ተምታቶብናል አልገባንም አብራሩልን” እያሉ ነው፡፡አብሽሩ ይገባችኋል! እንላለን ፡)
#መልሱ፡- በዓረብኛቋንቋ በመሰረታዊነት “ፊ” የምትለው ቃል “ውስጥ” የሚልን ትርጓሜ ብታስይዝም አንዳንዴ ግን “ፊ” የምትለው ቃል “ዓላ” ወይም“ከላይ” የሚል ትርጓሜንም ይዛ ትመጣለች፡፡ ይህንንም ትርጓሜ አላህ በአንዳንድ አንቀፆች ላይ ተጠቅሞበታል፡፡ ለምሳሌ
وَلَا تَمْشِفِي الْأَرْضِ مَرَحًا [١٧:٣٧]
“በምድርም ላይ የተንበጣረረክ ሆነህ፤ አትሂድ” አል-ኢስራእ 37
አየህ! አላህ በቁርዓኑ“በምድር ላይ የተንበጣረርክ/የኮራህ ሁነህ አትሂድ” ሲል በዓረብኛው የተጠቀመው “ፊ ል-አርዲ” የሚለውን ቃል ነው፡፡ እዚህ ቦታላይ “ፊ” የሚለው ቃል “ከላይ” የሚልን ትርጓሜ ይዟል፡፡ አሊያማ “ፊ” የሚለውን ቃል ሁሌም “ውስጥ” ማለት ነው ብንል ኖሮ የዚህየቁርዓን አንቀጽ ትርጉም “በመድር ውስጥ የተንበጣረርክ ሁነህ አትሂድ” የሚል በሆነ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ የተሳሳተ ትርጓሜ ነው፡፡ግልጽ ነው አይደል?
አንድ ምሳሌ ልጨምርላችሁ፤ጥጋበኛው ፊርዓውን ከሙሳ ጋር እንዲወዳደሩ ያዘጋጃቸው ድግምተኞች ባልተጠበቀ ሁኔታ በሙሳ በትር ተሸንፈው ጭራሽ ኢስላምን ሲቀበሉሲመለከት “ቡራ ከረዩ” አለ፡፡ “እጅና እጋራችሁን እቆርጣለሁ በቴምር ዛፍ ላይም እሰቅላችኋለሁ” ብሎ ፎከረ፡፡ ለምን ብሎ መሰለህ“እንዴት ሳልፈቀድላችሁ ለሙሳ ታምናላችሁ” ወቸ ጉድ! ኢስላምን ለመቀበልም እርሱን ማስፈቀድ ነበረባቸው፤ ሆይ ሆይ! እስቲ ወደርእሳችን እንመለስና ቁርዓኑ የፊርዓውንን ዛቻ ሲገልጽ ምን እንዳለ እንመለከት
وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْفِي جُذُوعِ النَّخْلِ [٢٠:٧١]
“በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ (አለ)” ጣሀ 71
እንግዲህ አምባገነኑፊርዓውን ሰዎቹን በተምር/ዘንባባ ግንድ ላይ እንደሚሰቅላቸው የተናገረውን ፉከራ አላህ በቁርዓኑ ሲተርክልን የተጠቀመው ቃል “ፊጁዙዒ ነኽለቲ” የሚለውን የዓረብኛ ቃል ነው፡፡ እንገዲህ “ፊ” የምትለው ቃል እዚህ ጋር ይዛው የመጣችው ትርጉም “ዓላ”/ላይ የሚለውንይሆናል፡፡ እንዲያማ ባይሆን ኖሮ የቁርዓኑ ትርጉም እንዲህ በሆነ ነበር “በዘንባባ ግንዶች ውስጥ እሰቅላችኋለሁ” ይህ ደግሞ የማይሆንነገር ነው፡፡
ስለዚህ በሐዲሱ ላይባሪያይቱ “ፊ ሰማእ”/በሰማይ ብላ ስትመልስ “ፊ” የምትለዋ ቃል የተፈለገበት መልእክት “አላህ ከሰማይ በላይ ነው” የሚለውን ግልጽመልእክት ያስይዛል ማለት ነው፡፡ አትርሳ! ባሪያዋ መልሱን ብትሳሳት ኖሮ እኮ ነቢዩም(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የመለሰችውን አያጸድቁላትምነበር፡፡ እንደውም መልሷ ለአማኝነቷ ማረጋገጫ ሆነላት እንጂ፡፡ ሱብሀን አላህ!
እንግዲህ እንዲህ ያለዝርዝር ውስጥ የገባነው ማንም ሰው ቀልብ ላይ ውል የሚል ውዥንብር እንዳይኖር በሚል ነው፡፡ አላህ ራሱን በገለፀበት እንዲሁም የእርሱታማኝ መልዕክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አላህን በገለፁት መሰረት ሳንጨምር ሳንቀንስ፣ አኳኋኑን ሳንገልፅ፣ የተቀመጠውን አስቀምጠን፣የተነገርን አምነን፣ ያልተነገረንን ሳንፈላፈል እናልፋለን፡፡ ይህም የቀደምት ሶሀቦችና የእነርሱን ፈለግ የተከተሉ ሁሉ ፋና እንደሆነእናውቃለን፤ አውቀንም እንከተላለን፡፡ አንዳንዶች እንደሚቀጥፉብን “አላህ ተቀምጧል፣ ይህን ያህላል፣ ያን ይመስላል” እያልን አንዘባርቅም፡፡አልወጣንም፤ አይወጣንምም፡፡
ወንድሞቼ ለመዝጊያነትእንዲሆን ከላይ ያወሳነውን ሐዲስ አስመልክቶ ታላቁ ዓሊም ኢማሙ ዘሀቢ የተናገሩትን አስፍሬ ልሰናበታችሁ፡፡

ኢማሙ ዘሀቢ እንዲህይላሉ
“በዚህ ሐዲስ ላይ ሁለት መጠይቆች አሉ፡፡ አንኛው ሙስሊም “ዓይነላህ”/አላህ የት ነው? ማለትእንደሚችል መደንገጉ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ (አላህ) በሰማይ መሆኑ ነው፡፡ እነዚህን ሁለት መጠይቆች ያወገዘ እሱ የሚያወግዘው ሙስጠፋን(ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) ነው!” ሙኽተሰር አል-ዑሉው

ሼር ማድረጉን እንዳይረሱ
ባነበበብነው የምንጠቀምያርገን! 

Post a Comment

0 Comments