Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽል ኢስላም አህመድ ኢብን ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላል

Sadat Kemal Abu Nuh

ሸይኽል ኢስላም አህመድ ኢብን ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላል የአለምን ሁኔታ ያስተዋለ (ያስተነተነ) ማንኛውም ምድር ላይ የሚታይ መስተካከል (የምድር መመቻቸቷ፤ መበጀቷ) ሰበቡ እና ምክንያቱ፤ አላህን አንድ በማድረግ ማምለክ እና መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መታዘዝ ነው፡፡ በአለም ላይ ያለ ሸር ነገሮች ማንኛውም መከራ፤ ስቃይ፤፤ አደጋ፤ ድርቅ መከሰት፤ እንዲሁም ጠላት (ሙስሊሞች ላይ) የበላይ መሆኑ እና የመሳሰሉት መንስኤያቸው፤ መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መቃረን እና ከአላህ ውጭ ያሉ አማልክቶችን መጣራት ነው፡፡ የሸይኽል ኢስላም ንግግር እዚህ ላይ አበቃ፡፡ ከአላይ የተቀመጠው መልካም ንግግር፤ የሸሃደተይን መሟላትን እና መጓደልን የሚያመጣውን ውጤት ነው በግልፅ ያስቀመጠው፡፡ አለምን አሁን ባለንበት ጌዜ በተጨባጭ ሁኔታ ስንመለከታት፡፡ ኢራቅ ላይ አብድል ቃድር ጀይላኔ ይመለካል፤ ኢራን ላይ አልይ፤ሁሴን፤ፋጢማ፤ ዘይነብ፤ ነፊሳ (ረድየላሁ አንሁማ) እና የመሳሰሉት፤ ህንድ እና ፓኪስታን ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች በወልይ ስም ይመለካሉ፤ ሱዳን የቀብር እና የጠንቃይ መዓት ይመለካል፤ ግብፅ ሲመጣ አህመድ በደዊ፤ ነፊሳ፤ ሁሴን እና የመሳሰለውን እየተባለ፤ አገራችን ኢትዬጵያ ላይ ሲመጣ አብሬት፤ ቃጥባሪ፤ ጫሌ፤ ጀማ ንጉስ፤ ኑር ሁሴን፤ በይዲ፤ አልከስዬ፤ አህመድ ቲጃኒ፤ የቦረናው ሸይህ፤ የዳንግላው ሸይህ፤ ሰይፉ ጨንገሬ፤ አዳል ሞቴ፤ ሸህ አንበሶ እየተባለ ጂንን ሁሉ በማምለክ ሽርክ ይሰራል፡፡ በጣም የሚገርመው ነብየላህ ኢሳን (አለይሂ ሰላምን) ያውም በህይወት ሁለተኛ ሰማይ ላይ ያሉትን፤ መጨረሻ ዘመን ላይ ወርደው ሰው የሚሞተውን ሞት የሚሞቱትን ኢሳን የሚያመልኩትን ሰዎች እነዚህ ካፊሮች ናቸው ብለው የሚጠሩት ሰዎች፤ እነሱ ለጀይላኔን፤ ለአህመድ በደዊ፤ እና መሰሎች፤ ካፊሮች ለኢሳ እና ለጂብሪል ከሚያደርጉት በላይ አምልኮ ሲፈፅሙ ይታያል፡፡ የሚገርመው አነሱም ልክ እንደ ካፊር አላህ የሚጠላውን ሽርክ፤ ከካፊር እኩል እየሰሩ ካፊርን እናሸንፋለን ብለው ሁሌ ይናገራሉ፡፡ ይህ ገርሞ የሚገርም ነገር ነው፡፡ ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመቃረን የቢድዓ መዓት፤ አላህ፤ መልክተኛው፤ ሰሃባዎች፤ ሶስቱ ምርጥ ክፍለ ዘመን፤ አራቱ አኢማዎች የማያውቁት ዝባዝንኪ ሁላ ዲን ተደርጎ ተይዟል፡፡ ለምሳሌ መውሊድ (ከነ ሽርካ ሽርኩ) ከሰላት በኋላ ኢማሙ ወደ ህዝቡ ዞሮ ዱዓ ማድረግ፤ ሸእባን 15 ሀሙስ ማታ እየተባለ ከመግሪብ እስከ ኢሻ መሰጂድ ውስጥ በጀመዓ ሰለዋት፤ ከሸሂ የተቀበልኩት የዚክር ጠሪቃ ነው በማለት ከሸሂ ዚህር ፍንክች አልልም ማለት፤ እና የመሳሰሉትን፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ የሚገርመው፤ ተራውን ህዝብ ለዱንያ ጥቅም እና ቢድዐቸውን ለማራመድ ሲሉ ይህን ሁሉ ጥፋት አለም ላይ እያዩ፤ ዝም የሚሉት እውቀትን የተሰጡ ሰዎች ነው፡፡ ይህ የዩሁዳ ባህሪ መሆኑን ረሱትን፤ አላህ አያያዙ የበረታ እንደሆነ ረሱን??? ታድያ አላህን በብቸኝነት ሳያመልኩ፤ የአላህን መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ (ሱና) ሳይከተሉ መመቻቸት እና ጠላትን ማሸነፍ ፈለጉን??? ይከልከሉ፤ ቅድሚያ ለተውሂድ እና ሱና ይስጡ፡፡ መጀመሪያውም፤ መሃከሉም፤ መጨረሻውም፤ ተውሂድ እና ሱና እንጂ የትኛውም ቦታ ላይ ሽርክ እና ቢድዓ መስራትም፤ ሲሰራ እያዩ ዝም ብሎ፤ ያውም አብሮ አፅድቆ ማለፍ አይፈቀድም፤ እውነት ሞቶ መቀስቀስ አለ፤ ሂሳብ አለ፤ ብሎ ለሚያምን ሰው፡፡ አላህ ሆይ! ሀቁን መንገድ ምራን፤ ዲንን አስገንዝበን፤ ሰላት እና ሰላምህ በነብያት እና ሩሱሎች ሁሉ ኢማም ላይ፤ የሳቸውንም ፈለግ እስከ መጨረሻው በተከተሉ ላይ ይሁን፡፡ አላሁመ አሚን፡፡