Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማነው ኢስላምን ለማጥቃት ከመንግስት ጋር የሚተባበረው


Ibnu Munewor

ማነው ኢስላምን ለማጥቃት ከመንግስት ጋር የሚተባበረው
ሰሞኑን ኢኽዋንና በኢኽዋን ቫይረስ የተለከፉ ሰዎች የተለመደ ጩኸታቸውን ከወትሮው በተለየ መልኩ ማራገብ ይዘውታል፡፡ እንደ ማስረጃ ሲጠቀሙባቸው የነበሩት የሹብሃት ቡቱቶዎች ተበጣጥቀው እርቃናቸውን ሲቀሩ ጊዜ በእጃቸው ያለውን ትልቁን መሳሪያ እየተኮሱ ነው፡፡ ውሸት!! ማስረጃን በማስረጃ በመመለስ ፋንታ “በደሊል የሚያናግሯቸውን ወንድሞችና እህቶች “የወያኔ ቅጥረኞች” በማለት ሰው ማስረጃ አገናዝቦ ሳይሆን በጥርጣሬ በርግጎ እንዲሸሽ ለማድረግ እየሰሩ ነው፡፡ ግን እውነት ለመናገር ማነው ከሰፈር ሹማምንትና ደህንነቶች ጋር ተለጥፎ ሲያጠቃ የነበረው? ትላንት በየመንግስት መስሪያ ቤቱ ሲሰገሰጉ ሌሎች እንዲገቡ ሲጎተጉቱ የነበሩት እነሱው ናቸው፡፡ ያለምንም ጥንቃቄ ከእስልምና ገዳይ (መጅሊስ) እስከ ከባንክ ቤት ሲገቡም ሲያስገቡ ነበር፡፡ ትላንት ዐብደላህ አልሀረሪ እንኳን ባቅሙ ከሚያከፍራቸውና ከሚያወግዛቸው ቲጃኒያ ሱፍዮች ጋር በየ ክ/ሀገሩ እየዞሩ ሲታረቁ ሲያስታርቁ በተውሒድ ደዕዋ ላይ ሲያሴሩ ነበር፡፡ በርካቶች በስም የሚታወቁትን ጨምሮ የኢህአዴግ የድርጅት አባላት እና ካድሬዎች ናቸው፡፡ ደግሞም አያፍሩም “በየዩኒቨርሲቲው ሴቶች በሒጃብ ምክኒያት ሲባረሩ የት ነበራችሁ?” ይሉናል፡፡ እነሱስ የት ነበሩ? ቀድሞ ነገር ኒቃብ ስለለበሱ ብቻ ሴቶችን በጥርጣሬ የሚያዩት እነማን ናቸውና? “ሒጃባችሁን ጥላችሁ ጀማዐ ሰላቱንም ትታችሁ ተማሩ” እያሉ ፈትዋ ሲሰጡ የነበሩት “ሙፍቲዎች” እነማን ናቸው? 400 ኪሎ ሜትር አቋርጠው ባደረጉት ሰበካ ሴቶችን ኒቃብ ያስጣሉት እነማን ናቸው? ትላንት በኢትዮጵያ የስብሰባ አዳራሽ ህገ-መንግስቱን ከቁርኣንና ከሐዲሥ ጋር እያገናኙ በመተንተን ለመንግስት በመቀስቀስ መንግስትን በደስታ ጮቤ ያስረገጡት እነማን ናቸው? ትላንት በጃሊያ አዳራሽ የአዲስ አበባ ሙስሊም ተማሪዎችን ከህብረተሰቡ ጋር ሰብስበው ወላሂ እያለቀሱ ለመንግስት የቀሰቀሱት እነሱ እንጂ እነማን ናቸው? ወላሂ አስታውሳለሁ የተቃውሞ ሀሳብ ያሰሙትን “እብድ” እያሉ በህዝብ ፊት በማይክራፎን ሲወርፉ ነበር፡፡ በየዩኒቨርሲቲው፣ በየ ሹራ አባላቱ ለመንግስት ባደረጉት ቅስቀሳ “ምን አገባችሁ” በሚል ተቃውሞ የተነሳበት ካምፓስ ሁሉ አውቃለሁ፡፡ ደግመው ደጋግመው የሚወተውቱት ነገር ተፅእኖ አሳድሮብን በማይመለከተን ጉዳይ ሲያስገቡን ነበር፡፡ እነሱ ከመንግስት ጋር ሲለጠፉ “ለኢስላም ለመስራት ነው ሙስሊሞችን ለመጥቀም” ይሉታል፡፡ አላሁ አዕለም፡፡ እኛ ግን በተጨባጭ ከዚያም ያለፈ ነገር አይተናል፡፡ በየመስሪያ ቤቱ ያለቻቸውን ስልጣን ተጠቅመው ለ “ደህንነት” አሳልፈው ሲሰጡን “ተክፊሮች ናቸው” እያሉ ሲያስጠቁሩን ነበር፡፡ ይሄ ነው ለኢስላም መስራት?!! ወላሂ የኢኽዋን ሰባኪዎች ከካፊር ጋር ሆነው በሚዶልቱት ሴራ ስንት ወንድሞች ታስረዋል፡፡ ስንት ቂራኣት ታግዷል፡፡ ለዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች እና ለግቢ ፖሊሶች የቅጥፈት ውንጀላ እየለጠፉ ስንት ወንድሞችን አንገላተዋል?!
ወላሂ አይደለም እነሱ እንደሚያላዝኑት ኢስላምን ለማስመታት ቀርቶ ምንም አይነት ግንኙነት ከመንግስት ጋር እንደሌለን ብዙዎቹ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን በማጠልሸት፣ ስም በማጥፋት የተካኑ ናቸው፡፡ በማስረጃ መጋፈጥ ሲያቅታቸው ቀጥታ የሚጠጉት ወደ ውሸት ውንጀላ ነው፡፡ ፈጥሮ፣ ቀጣጥሎ ቀጣጥፎ ስም ማጥፋት፡፡ የኢኽዋን ፊክራ የሰረፀው አብዛሃኛው ሰው እሱ የገባበትን ጥፋት ስትቃወሙት ከጠላት ጋር እንደምትተባበሩ ነው የሚገልፃችሁ፡፡ “የሃሳብ ሽብር” ለመፍጠር፡፡ ብዙ ጊዜ ወደ ባጢል ይጣራሉ፡፡ በማስረጃ የሚሞግታቸው ሲመጣ ግን ያለምንም ጥንቃቄ ያከፍራሉ፡፡ ያለምንም ማስረጃ ምንም ሳይሰለቹ ደግመው ደጋግመው ይወነጅላሉ፡፡ “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” የሚለው የሂትለው የፕሮፓጋንዳ ሃላፊ መፈክር ኢኽዋን ሰፈር በሰፊው ይሰራበታል፡፡ አላማቸውን ለማሳካት የትኛውንም አማራጭ ይጠቀማሉ፡፡ የመረጡት አማራጭ ከቁርኣን ከሱና ቢጋጭ፣ ከሞራልና ግብረ-ገብነት ጋር ቢጣረስ አያገባቸውም፡፡ “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” ከሚል ሀገርኛ ብሂል ጋር የሚቀራረብ የማኪያቬሊ መርህ ነው መመሪያቸው፡፡ ስም ለማጥፋት ደግሞ ከማንም በላይ የተካኑ ናቸው፡፡ ይሄን ደግሞ እራሳቸውም ያውቁታል፡፡ እንዳውም ይሄ ዐለም አቀፍ መታወቂያቸው ነው፡፡ ከነሱው አመራሮች አንዱ የሆነው ሰዒድ ሐዋ የተናገረውን ተመልከቱማ “የአሜሪካ እና የሩሲያ ተቋማትና የስለላ ድርጅቶች የአንድን ሰው ዝና ለማጉደፍ ቢሰባሰቡም ኢኽዋነልሙስሊሚን የደረሱበትን ያክል አይደርሱም!!” ይላል፡፡ አያችሁ አይደል?! ይህን ሰይጣናዊ ታክቲካቸውን የሚጠቀሙት ደግሞ በቀዳሚነት ሱናን ለመዋጋት ነው፡፡
“ጂሃድ”፣ “ሰልፍ”፣ ወዘተ እያሉ የሚማግዱት ምንም የማያውቀውን መሀይም ነው፡፡ አብዛሃኞቹ (ሁሉም አላልኩም) ነገሩ ተፋፍሞ ስኬታማ ሊሆን ነው ብለው ሲያስቡ ነው ብቅ ብቅ የሚሉት፡፡ ያለበለዚያ ከጓዳ ሆነው ነው በሁለት ቢላዋ የሚበሉት፡፡
“ታክቲክ ታውቂ የለ የጦር ሜዳ ታክቲክ
ካልጋ ስር መሰውር ተጣጥፎ እንደላስቲክ!!” ያለው ማን ነበር?
አላማቸው ህዝበ-ሙስሊሙን ሳይታወቀው ኢኽዋናዊ አስተሳሰብ (ሜንታሊቲ) እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ ኢኽዋንነቱን የማያውቅ ኢኽዋን ማድረግ!!! ሰላህ ሻዲ የተባለው ቁንጮ ኢኽዋኒ ይህን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡፡ (ድርጅት የሌለው ድርጅት ነው የምንፈልገው!!) ከገባህ “ኢኽዋንነትህን ሳታውቅ ኢኽዋን እናደርገሃለን” እያለህ ነው፡፡ ህዝቤ ሆይ! ምን እየተዶለተልህ እንደሆነ በጥንቃቄ አስተውል!! በፍየል ዘመን በግ መሆን አያዋጣም!!! እንደገና እየተጠረብክ ነው ዳግም እየተሰራህ!! ስሜትህን የማይጋፋ፣ ከጥፋትህ “ሀይ” የማይልህ የነቃህ እየመሰለህ የሚያስተኛህ ኢኽዋናዊ ኢስላም ነው እየቀረበልህ ያለው፡፡ የምታነበው፣ የሚተረጎምልህ፣ የሚቀርብልህ የኢኽዋን ኪታብ ነው፣ በሂደቱም የኢኽዋንን አመለካከት የማታንፀባርቅበት ምንም ምክኒያት አይኖርም፡፡ ከዘመናት በኋላ ያለምንም ጥርጥር ኢኽዋንኛ ትተነፍሳለህ፡፡ ንፁሁን አየር ትበክላለህ፡፡ የነሰይድ ቁጥብ፣ ሐሰኑልበና፣ ቀርዳዊ ስራን ነው ጧት ማታ እንድትከታተል የምትደረገው፡፡ እንኳን የእምነት መፅሃፍ እንደሆነ እያሰብክ አንብበኸው ቀርቶ ምእራቡ ዓለም በፊልም አይደል እንዴ የአመለካከትና የባህል ወረራ እየፈፀመ ያለው?! ስለዚህ የነዚህን ሰዎች ስራ በሰፊው በተከታተልክ ቁጥር ይበልጥ ወደ ቡድኑ እየቀረብክ ነው፡፡ አይደለም ስንት መፅሃፋቸውን እየኮመኮምክላቸው ቀርቶ በአንዲት የቢድዐ ንግግር ብቻ ገደል የገቡ ስንቶች ናቸው! እነዚህ የኢኽዋን ቁንጮዎችን እንደኢስላም ታላላቅ ስብእናዎች መቁጠርህ እራሱ ምንድን ነው የሚያሳየው?! ሰይድ ቁጥብ ሰሐባ ሲሳደብ ያላመመህን የሱ ጥፋት ሲጋለጥ ካንቀጠቀጠህ እንዴት ብለህ ጤነኛ እንደሆንክ እስኪ አስረዳኝ!!! ይልቅ በሽታህን የማታውቅበትን ምክኒያት ልንገርህ፡፡ በሽታህ ድግምት ነው፡፡ እነኚህን የኢኽዋን ተራሮች የኢስላም ምሁራን አድርገህ እንድትስል ያላሰለሰ ድግምት ተሰርቶብሃል፡፡ “ካገላለፅም ድግምት አለ” ይላሉ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡ ድግምታቸው ከሰራ ሰዎቹ ይወዱሃል፡፡ ከወደዱህ የፈለገ ከዲን ብትርቅ ጥሩ ሰው ነህ፡፡ አመለካከታቸውን ካልተቀበልክ የፈለገ ለዲን ቅርብ ብትሆን ስምህን ያጎድፉታል፣ ክብርህን ያንቋሽሹታል፡፡ በብልግና ስምህን ያነሱታል፡፡ በሌለህ ስም ይሰጥሃል፡፡ ያልሰራሃውን ይለጥፉብሃል፡፡ ከቻሉ ከብዙ ያሰናክሉሃል፡፡ የተቆጣጠሩት መስሪያ ቤት ካለ የሚሰበሰበው ሁሉ እየተመረጠ የነሱ ሰው ነው፡፡ አንተ መመዘኛውን ብታልፍም የሚቀርህ ትልቅ መስፈርት አለ፡፡ በኢኽዋን ፀበል መጠመቅ!!! በየቦታው፣ በያጋጣሚው በክፉ ያነሱሃል፡፡ አንተ ደቡብ ወይም ምእራብ ሆነህ ያላየህ የማያውቅህ ሁሉ ሰሜን ወይም ምስራቅ ሆኖ በክፉ ያውቅሃል ይጠላሃል፡፡ ድንገት የታየህ ቀን “ይሄ ነው” ብሎ መጠቆም ብቻ እንጂ ስላንተ መዘርዘር አያስፈልግም፡፡ ቀድሞ ማንነትህ ተነግሯልና፡፡ “እንዴት ባልሰራሁት በሌለሁበት ይለጥፉብኛል?” ብለህ አትደነቅ፡፡ ሰዎቹ የዲን ቀርቶ የሞራል ገደብም የላቸው፡፡ እራሳቸው እንደሚናገሩት “አንድን ሰው መጣል ስንፈልግ ወደ ቤተሰቦቹ፣ ወደ ግል ቤቱ ጉዳይ እንገባለን” ይላሉ፡፡
ይቀጥላል