Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሰሞኑ መንግስት 400 ሰዎችን አሰልጥኖ አሰማርቷል እያሉ ነው ወንድሞቻችን

ከሰሞኑ መንግስት 400 ሰዎችን አሰልጥኖ አሰማርቷል እያሉ ነው ወንድሞቻችን፡፡ በርግጥ “ይሄ በፍፁም የማይሆን ነገር ነው” አልልም፡፡ ቢሆንም ግን ወሬው የተሰማው ከኢኽዋኖች አካባቢ ስለሆነ ተጨባጭ ማስረጃ ሳላገኝ ላምን አልችልም፡፡ ልብ በሉ አልተከሰተም አላልኩም፡፡ ያለመረጃ ግን አይደለም ከእነንቶኔ ከማንም አንቀበልም፡፡ እነሱ ሰውን ስሜታዊ አድርገው፣ ወይም በፍርሃት ሸብበው አስደንብረው በማስረጃ መቋቋም ያቃታቸውን በውንጀላ መሸፈን ይፈልጋሉ፡፡ እነሱ የተውሒድ ደዕዋ ሲሰሙ ዐይናቸው ደም ይለብሳል፡፡ ፀረ ተውሒድ ሆነው ሳለ “አይደለንም” ይላሉ፡፡ እንዳውም “ለተውሒድ ደዕዋ እንቅፋት የሚሆን አንድም የለም” እያሉ ነው፡፡ ዐብደላህ አልሐረሪ እንኳን ንቆ ከሚያከፍራቸው ቲጃኖች ጋር ህብረት ስትፈጥሩ አልነበር፡፡ ታዲያ እነሱ የተውሒድ ችግር የላቸውም ማለት ነው፡፡ ይሄን ካላወቃችሁ የራሳችሁን ማንነት እያጋለጣችሁ ነው፡፡ እያወቃችሁ ከሆነ ከቲጃኒያ ጋር ስትታረቁ ስታስታርቁ የነበራችሁት እናንተ ናችሁ፡፡ ታዲያ ይሄ አይን ያወጣ የተውሒድ ጠላትነት አይደለምን፡፡ ተውሒድ የሚቃወም ከሌለ እስኪ በአልከሶ፣ በአብሬት፣ በነጃሺ፣ በዳና፣ በአና፣ በአናጂና፣… በተለያዩ የሀገራችን የሱፍያ መስጂዶች ግቡና ስለተውሒድ በትክክል አስተምሩ፡፡ በህይወት ከተመለሳችሁም ያገኛችሁን ንገሩን፡፡ ይልቅ የተውሒድ ደዕዋ ሰው እያሳጣችሁ ስለሆነ፣ ሰው ማንነታችሁን እያረጋገጠ ሲመጣ አንድ ሰሞን “ተውሒድ ተውሒድ” አላችሁ፡፡ ተውሒድን ልክ እንደ በክት ለዶሩራ ልትጠቀሙ፡፡ የሚገርመው ግን እንኳን በተግባር በተውሒድ ማስመሰያችሁ ልትቀጥሉ በዶለታችሁት የግማሽ ገፅ ፅሁፍ እንኳን መቀጠል አልቻላችሁም፡፡ “ሶፍያ ወንድሞቻችንን እንዳናስከፋ መጠንቀቅ አለብን” አላችሁን፡፡ ደግሞ ማን ናት ሶፍያ፡፡ አሃ ሱፍያ ማለታችሁ ነው፡፡ እሺ ይሁን ሱፍያን ሳታስከፉ የምታስተምሩት ተውሒድ ምን አይነት ተውሒድ ነው ሴራችሁ ግልፅ ነው፡፡ አንድ ሰሞን የተግባር ሳይሆን የመፈክር ተውሒድ አሰምታችሁ መንቃት የጀመሩባችሁን ልታስተኙ ነው፡፡