Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢብኑ ተይሚያ በዐሊሞች አንደበት

ኢብኑ ተይሚያ በዐሊሞች አንደበት
1- ሐፊዝ አቡል ሐጃጅ አልሚዚ፡- “አምሳያ አላየሁለትም፡፡ እሱ እራሱ አምሳያውን አላየም፡፡ የአላህን ኪታብና የመልእክተኛውን ሱና ከሱ በላይ የሚያውቅና የሚከተል አላየሁም” (አልዑቁዱዱሪያ፡11)
2- ሐፊዝ ዐብደላህ አዘህቢ፡- “ገድሉ የኔ አምሳያ ከሚገልፀው በላይ ነው፡፡ በሩክንና በመቓም መሀል ሆኜ ብምል በአይኖቼ አምሳያውን እንዳላየሁ እምላለሁ፡፡ በአላህ ይሁንብኝ በዒልም እሱ እራሱ አምሳያውን አላየም” (አልዑቁዱዱሪያ፡82)
3- ኢብኑ ደቂቀልዒድ፡- “አላህ እንዳንተ አይነቱን መፍጠሩን አቁሟል ብዬ ነበር የማስበው” (ዘይሉጦበቃቱል ሐናቢላ)
4- ዘመልካኒ፡ “ሰይዳች፣ ሸይካችን፣ አል ኢማም፣ አልዓሊም፣ አል አውሐድ፣ አልሐፊዝ፣ አልሙጅተሂድ፣ አዛሂድ፣ አልዓቢድ፣ አልቁድዋ፣ የመሪዎች መሪ፣ የኡማው አርአያ፣ ዐላመቱል ዑለማህ፣ የነብያት ወራሽ አኺሩል ሙጅተሂዲን፣ ከዲኑ ዐሊሞች አንዱ፣ የኢስላም በረከት፣ሑጀቱል ዐላም፣ ቡርሃኑል ሙተከሊሚን፣ የሙብተዲዎች ቆራጭ፣ ከፍ ያሉ እውቀቶችና የዲንቅ ዘርፎች ባለቤት፣ የሱና ህይወት የሚዘራ፣ በሱ ምክኒያት የአላህ ውለታ ከፍ ያለበት፣ በጠላቶቹ ላይ ሑጃ ያቆመበት፣ በበረከቱ ድኑ ግልፅ የሆነበት፣ ተቅዩዲን ኢብኑ ተይሚያ” ሲል ይገልፀዋል፡፡
5- አልሐፊዝ አልዐባኢ “ጌታየ ሆይ ድንቅ በሆኑት የኢብኑ ተይሚያ እውቀቶች አስጠቅመን በዱኒያም በአኺራም የምንጠቀም አርገን” (አዱረሩል ካሚና:1/160)
6- ቃዲ ሸምሰዲን ኢብኑ አደይሪ፡- “በይተል መቅዲስ ውስጥ ዐላኡዲን አልበስጧሚን እንዲህ ስል ጠየቅኩት፡- ‘ኢብኑ ተይሚያን አይተኸዋል?' ‘አዎ' አለኝ፡፡ ‘ምን ይመስል ነበር?' አልኩት፡፡ እሱም ‘ቁበተሶኽራን አይተሃል?' አለኝ፡፡ ‘አዎ' አልኩት፡፡ ‘በቃ ኪታብ የተሞላ ተናጋሪ ምላስ ያለው ቁበተሶኽራ ማለት ነው!!'” (አልጀዋሂር ወዱረር፡1/177)
7- ሲዩጢ:- “ባለፋት 500 አመታት እንደኢብኑ ተይሚያ ያለ ሐፊዝ አላውቅም” (አልአሽባህ ወነዟኢር፡ 3/681)
8- ሙሐመድ ሙሕዩዲን ዐብዱል ሐሚድ- የቱሕፈቱሠኒያ አዘጋጅ ታዋቂው የነሕው ዐሊም፡- “ዒልሙ(የኢብኑ ተይሚያ) በአስር ለሚቆጠሩ ዐሊሞች ቢከፋፈል ይሰፋቸው ነበር፡፡ እንዳውም እያንዳንዳቸው በጣት የሚጠቆም ስመ-ገናና ዐሊም ይወጣው ነበር” (ተሕቂቅ አሷሪሙል መስሉል፡3-4)

ይህን ነው እንግዲህ ኢብኑ ተይሚያ ዐሊሞቹ ዘንድ፡፡ መሀይሞች ምን እንደሚሉ ማወቅ የፈለገ አሕባሾችን ይጠይቅ፡፡ ኢማሙዘህቢን አላህ ይማረውና እንዲህ ይላል፡ “ጃሂል የራሱን ልክ አያውቅም፡፡ ታዲያ እንዴት የሌሎችን ልክ ሊያውቅ ይችላል?!!” ረሒመላሁ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብ፡፡ “የራሱን ልክ አውቆ ከድንበሩ የቆመን ሰው አላህ ይማረው” የሚለው ንግሩ በወርቅ ቀለም የሚፃፍ ነው፡፡

ያ ለመስቀለኞች ሲያብር የነበረው
ይሄውና ዛሬም ታሪኩን ደገመው
የእባብ ልጅ አባብ ነው አይስትም ጎዶውን
አሕባሽ መድገም ያዘ ካባቱ ያየውን
ታሪክ የምታውቁ እስኪ ተናገሩ
የኻሊዱል ቀስሪ የት ነበር አገሩ
የጀዕድን ጭንቅላት ያህባሾቹን አያት
ቀንጥሶ የጣለው ሌላ እንዲማርበት
እስኪ ተናገሩ የት ነበር አገሩ
ጀዕድ መጥቷል አሉ ካፖርቱን ቀይሮ
ጀህም መጥቷል አሉ አይሁድ ጋር ተባብሮ