Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በነገራችን ላይ ይሄም ሒክማ ነው፡፡

by Ibnu Munewor
በነገራችን ላይ ይሄም ሒክማ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ ጠንከር ያለ የዐሊሞች ወይም የሰለፎች ንግግር በሰሙ ቁጥር “ይሄ ሒክማ አይደለም” የሚሉ ደፋሮች በዝተዋል፡፡ “ይሄ እኮ የእከሌ ዓሊም ንግግር እንጂ የኔ አይደለም” ሲባሉ “ቁርኣን ላይ ከፊርዐውን ወዲያ አመፀኛ እሱን እንኳን ለዘብ ያለ ቃል እንዲያናግሩት ለሙሳና ለሀሩን ነግሯቸዋል” ይላሉ፡፡ ሐዲሶችንም ያጣቅሳሉ፡፡ እርግጥ ነው በአብዛሃኛው አካሄዳችን ለስላሳ መሆን አለበት፡፡ ይህ ማለት ግን የምንጠነክርበት ቦታ የለም ማለት አይደለም፡፡ እንድንለሰልስ ያስተማረን ቁርኣን እጅግ ጠንካራ ቃላትንም ተጠቅሟል፡፡ ለምሳሌ፡-
- “ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎችና እውሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ አይመለሱም!”
- “ከተንቀሳቃሾች ሁሉ አላህ ዘንድ ክፉዎቹ እነዚያ የማያውቁት ደንቆሮዎቹና ዲዳዎቹ ናቸው”
- “የነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልሰሩባት ሰዎች ምሳሌ መፅሀፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው፡፡”
- “…ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡”
ይህንና የመሳሰሉ ሲነገራቸው “እንዴ ይሄማ ለካፊሮች እኮ ነው” ይላሉ፡፡ እኛም እንበላ “አሃ ታዲያ የፊርዐውንን ምሳሌ መጥቀሳችሁ ምን ማለት ነው? እሱ ሙስሊም ነው እንዴ? ደግሞስ ለካፊር ሒክማ አይስፈልግም ማለት ነው?”
መለስ እንበልና ስለ ሒክማ ያስተማሩት አዛኙ ነብይም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የለሰለሱበት እጅግ ብዙ አጋጣሚ እንዳላቸው ሁሉ የጠነከሩበትም ብዙ አጋጣሚ አላቸው፡፡ ለምሳሌም ዑመርን፣ ሙዐዝን፣ ዓኢሻን፣… አጥብቀው የተናገሩበት ሁኔታ አለ፡፡ ኡሳማን እጅግ አጥብቀው ከመናገራቸው የተነሳ “መስለሜ ከዚያ በፊት ባልሆነ” ብሎ እስከሚመኝ ደርሷል፡፡ በራሳቸው ጉዳይ ብዙ የሚያልፉት ነብይ የአላህ ሐቅ ሲደፈር ግን ቁጣቸው ከፊታቸው ይነበብ ነበር፡፡ ይስተዋል! ይሄም ሒክማ ነው፡፡ በኢስላም የገደለ ይገደላል፣ የሰረቀ ይቆረጣል፣ ዝሙት የሰራ ያገባ ከሆነ በድንገጋይ ተወግሮ ይገደላል፣ ያላገባ ከሆነ መቶ ጂራፍ ይገረፋል፣ ዐይን ያጠፋ ዐይኑ ይጠፋል፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበራል፣ ያቆሰለ ይቆሰላል፣ ወዘተ፡፡ ይስተዋል ይህም ሒክማ ነው፡፡
ኢብራሂም ጣኦቶችን ሰባብረው ፈላልጠው ጥለዋል፡፡ ይሄም ሒክማ ነው፡፡ እነኚህ ሻንጣ የሚሸከሙት ሰዎች ግን “አብረህ ጦዋፍ እያረግክ ኹሩጅ እያስወጣህ ነው መስበክ ያለብህ” ይሉሃል፡፡ አያችሁ ይህን ከኢብራሂም የሚበልጥ ሒክማ?i
የዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ተማሪዎች ድቤ እየመቱ የሚዘፍኑ ልጃገረዶችን እየቀሙ ይቀዳድዱባቸው ነበር፡፡ ይሰተዋል ይህም ሒክማ ነው፡፡ እነዚያ ሻንጣ የሚሸከሙትና አባሪዎቻቸው ግን ጫት የሚቅሙትን ጫት እየገዛህላቸው አብረሃቸው እየተቀመጥክ ቀስ ብለህ ነው ማስተው ያለብህ” ይሉሃል፡፡ አያችው ይህን ከታቢዖች የሚበልጥ ሒክማ?i
ሶቢግ የሚባል ሰው ሙታሻቢህ የሆኑ አያዎችን ሲከታተል ዑመር ኢብኑ ኸጣብ በዱላ እራስ እራሱን ቀጥቅጦታል፡፡ አልበቃውም አመት ሙሉ ማንም እንዳያናግረው ወስኖበታል፡፡ ይስተዋል! ይህም ሒክማ ነው፡፡ ዛሬ ሶቢግ ከሰራው ጥፋት ብዙ እጥፍ የከፋ እየሰሩ “በሒክማ” የሚከላከሉላቸው ብዛታቸው የትየሌሌ ናቸው፡፡ ጀዕድ ኢብኑ ዲርሃም ያፈነገጠ አስተሳሰብ ሲያመጣ እንደ በግ ታርዶ ተጥሏል፡፡ ይስተዋል! ይህም ሒክማ ነው፡፡
ስለዚህ ሒክማ ማለት እንደ ቦታው፣ እንደጊዜው፣ እንደሁኔታው ሲያስፈልግ እየለሰለሱ፣ ሲያስፈልግ እየጠነከሩ ማስተማር እንጂ ሁሌ አንገት ማቅለስለስ አይደለም፡፡ ይህን ደግሞ እኒህ “እንለስልስ” ባዮቹም አያደርጉትም፡፡ ያለባቸውን ቢድዐ ወይም የቢድዐ ቁንጮዎቻቸውን፣ … አጋልጡና ሲያንዘፈዝፋቸው ተመልከቱ፡፡
አዎ ‪#‎ብዙውን‬ ጊዜ ልንለሰልስ ይገባል፡፡ ይህን የሚያመላክቱም ‪#‎እጅግ‬ ‪#‎በርካታ‬ ማስረጃዎች አሉ፡፡‪#‎አብዛሃኛውን‬ ጊዜም ከመጠንከር ይልቅ መለስለስ የተሻለ ውጤት ያመጣል፡፡ ሁልጊዜ ግን አይደለም፡፡ የሰው ባህሪው ብዙ ነው፡፡ ስትጠነክር የሚሻለው አለ፡፡ ስትቆጣ የሚደነግጥ አለ፡፡ በመጠንከርህ እሱ ባይማርበት ሌሎች የሚማሩበት ሁኔታም አለ፡፡ ልብ በሉ! ከላይ ጠንከር ያሉትን ብቻ መዘርዘሬ “ይህም ሒክማ ነው” ለማለት እንጂ “‪#‎ከመለስለስ‬ ‪#‎መጠንከር‬ ‪#‎ይሻላል‬” እያልኩ አይደለም፡፡ ይህን‪#‎ደጋግማችሁ‬ ‪#‎አስምሩልኝ‬፡፡ መደጋገሜ የተፃፈውን ሳይሆን የሚፈልጉትን ብቻ የሚረዱ “ቦርቃቃዎች” እንደ አሸን ስለፈሉ ነው፡፡
ጠንካራ የሰለፎችን አባባሎች በሰሙ ቁጥር “ይሄ ሒክማ አይደለም” እያሉ ከዐሊሞቹ በላይ የሚንጠራሩ ባለ “ሒክማዎች” ግን እራሳቸውን በሒክማ አደብ ቢያስተምሩ መልካም ነው፡፡ ዓሊሞችን ማክበር ሰለፎችን ከማክበር እንጂ ለሙብተዲዖች ከመከላከል አይጀምር፡፡ “ሙብተዲዕን ያደነቀ ኢስላምን በመናድ ላይ ተባብሯል” ይላል ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ፡፡ ጀናባውን እንዴት ማውረድ እንዳለበት የማያውቅ መሀይማንን እየሰበሰቡ የ “ሒክማ” ኮርስ የሚሰጡ ሰባኪዎች ተበራክተዋል፡፡ ሌሎችን እያሳጡ ለራሳቸው ዝናን ይሸምታሉ፡፡ ከሺርክ ያልተላቀቀን ማህበረሰብ “ሒክማ ሒክማ” እያሉ ደዕዋ ገምጋሚ ያደርጉታል፡፡ አሊፍ ትቁም ትጋደም የማያውቀው ሁላ ስሜቱ በተነካበት ቁጥር “ሒክማ ተበላሸን” ያስተጋባል፡፡ አሁን ይሄ የማን ገፀ-በረከት ነው? አዎ የነዚያ በሐቅ ሂሳብ ሁሉንም ማግበስበስ የሚሹ፣ ቡድናዊ አላማ ያነገቡ ኢኽዋንዮች ወይም የነሱ ሶፍትዌር የተጫነባቸው በቀቀኖች በረከት ነው፡፡