Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ውዱእ ማድረግ ግዴታ የሚሆንላቸው ነገሮች



አንድ ሰው የሚከተሉትን ነገሮች ለመስራት ሲፈልግ በቅድሚያ ውዱእ ማድረግ አለበት፦ 
1. ሰላት ለመስገድ፦ ኢብኑ ዑመር በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል “አላህ ያለውዱእ ሰላትን አይቀበልም ከተሰረቀም ነገር ምፅዋትን አይቀበልም፡፡” ( ሙስሊም ዘግበውታል) 
2. ግዴታም ይሁን ሱና ካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፦ነብዩ “በቅድሚያ ውዱእ አድርገው ከዚያ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ አድረገዋል፡፡” ( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
እንዲሁም ነብዩ እንዲህ ብለዋል “በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ሰላት ነው፡፡ ልዩነቱ ግን ጠዋፍ ላይ መናገር አላህ ፈቅዷል፡፡” እንዲሁም ደግሞ “የወር አበባ ያለባትን ሴት እስክትፀዳ ድረስ ጠዋፍ እንዳታደርግ ከልክለዋል” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) 
3. ቁርአንን ያለግርዶሽ ለመንካት፦ አላህ እንዲህ ብሏል‹‹የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡›› (ዋቂዓህ 79)ነብዩም እንዲህ ብለዋል “ቁርአንን ንፁህ እንጂ እንዳይነካ”