Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሂጃብ



አላሁ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ሴትን ልጅ ካዘዘበት ነገር የርሷ ተቃራኒ ከሆነ ወንድ አልያም እርሷን ሊያገቡ ከሚችሉ ወንዶች ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ያስቀመጠላት መስፈርት ነው፡፡እርሱም ሂጃብ ነው፡፡ሂጃብ የአማኝ ሴት መገለጫ የንጽናዋ ማስታወቂ ነው እንዳትደፈርና ክብሯ እንዳይነካ መከላከያ መሳሪያዋ:: ሂጃብ የለበሰች ሴት በህይወት ጉዞዋ የነቃችና የበቃች ናት ፡፡ ለራሷም ይሁን ለሌሎች በምታበረክተው መልካም አስተዋጽኦ በጽናት እንድትወጣ ሂጃብ ታላቁ ደጋፊዋ ነው ፡፡ ምክንያቱም፡- ለሰው ልጆች አጥፊና አውዳሚ ከሚባሉት ሁለት ፈተናዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የስሜትን ፈተና በሂጃብ ልጎም እንዳትሰረው ስለሚያስችላት ነው፡፡አዎ! ህጋዊ ሃላል ባልሆነ መንገድ የሚደረግ ልቅ የሆነ የሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ግንኙነትና መደባለቅ ከግለሰብ አልፎ ማህበረሰብን ያወደመ ከባድ ወረርሽኝ ነው፡፡ የታሪክ መዛግብት ብናገላብጥ ይህ የወረርሽኝ ምችና ልክፍት አጣሞ ጥሏቸው የጠፍና እየጠፍም ያሉ ህዝቦችን እንመለከታለን፡፡ በዚህ ስሜት ላይ ያላቸው እይታ ልጔመ ቢስ ልቅ በመሆኑ ለራሳቸውም ይሁን ለሌሎች መልካምና ጠቃሚ ነገሮችን የማበርከት መቅኒያቸውን አፈሰሰባቸው ፡፡ታዲያ በትምህርት ገበታውም ይሁን በስራ ቦታዎች ላይ ሳይቀር ፍጹም ዘግናኝና እንስሳዊ ግንኙነቶቸ ተንሰራፍ ፡፡ፈጣሪ ያስቀመጠውን ተስማሚና ምቹ ህግን በመጣሳቸው ሚደሰቱበትና ሚረኩበት ቢያጡ ከእንስሳውም ከግኡዙም አካል ጋር ተያያዙት ፡፡በተመሳሳይ የጾታ ባለቤቶች መካከልም የሚደረገው ግንኙነት ከዚህ ውስጥ የሚገባ ነው ፡፡በርግጥ ይህ ለናሙና ተገለጸ እንጂ የዚህ የዘቀጠ ግንኙነት አራማጆች አጠቃላይ ሁኔታና የዘቀጡበትን የጥፋት ማእበል እንዘርዝር ቢባል ብእሮች በዋዛ ሚወጡት አይሆንም ፡፡እንደሚባለው ብልጥ ልጅ በጥቆማ ይገባዋል በማለት በዚህ ብንወሰን ይሻላል፡፡ኢስላም ከዚህ አይነት መስመር ዘለልና ፈር ለቀቅ አካሄድ ለመዳን የጥፋቱ ሰለባ ከመሆን ለመቅረፍ ለሴት ልጅ ሂጃብን ደንግጔል ፡፡በመቀጠል ስለ ሂጃብ ያለውን ነገርና ከርሱ ጋር በተያያዥነት የተቀመጡት ብይኖችን ለመዳሰስ እሞክራለው::አላሁ (ሱብሃነሁ ወተአላ) እንዲህ ብሏል ፡-«ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡» (ምእራፍ አንኑር ቀጥር 31)

https://m.facebook.com/tenbihat