Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሲዲቁል አክበር


By Ibnu Munewor
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ መስጂደል አቅሷ በተወሰዱ ጊዜ (ኢስራእ) የሰው መነጋገሪያ ይሄ ሆነ፡፡ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አምነው ከነበሩት የተወሰኑት አፈነገጡ፣ ከኢስላም ተመለሱ፡፡ ወደ አቡ በክርም ረዲየላሁ ዐንሁ ተንከልክለው እንዲህ አሉት፡- “ከዚህ በኋላ ከጓደኛህ (ሙሐመድ) ምን አለህ? ‘ዛሬ ሌሊት በይተል መቅዲስ ሄጄ ነበር’ እያለ ይሞግት ይዟል::”
አቡ በክር፡- “እውን እሱ እንዲያ ብሏል?” አላቸው
“አዎ!” አሉ
“ብሎ ከሆነ እውነት ብሏል” አላቸው::
“በአንድ ሌሊት በይተል መቅዲስ ደርሶ ከጎህ በፊት ተመለስኩ ሲል ታምነዋለህ?” አሉት
አቡ በክር፡- “ከዚህም በራቀ አምነዋለሁ፡፡ ጧት ማታ በሚወርደው በሰማይ ዜና አምነዋለሁ” አለ፡፡
ከዚህ ቀን በኋላ አቡበክር አሲዲቅ ተብሎ መጠራት ያዘ፡፡
ሸይኹል አልባኒ “ሶሒሕ” ብለውታል፡፡ (ሲልሲለቱል አሓዲሡ አሶሒሓህ፡ 1/306)