Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሸይኹል አልባኒ ጋር ፈገግ ይበሉ


አንድ ሱፊ ሸይኹል አልባኒ ባሉበት እንዲህ አለ፡- “እናተ ሱፍያን ትሳደባላችሁ አይደል? እኔ ከአላህ ሰዎች አንዱ ነኝ፡፡ ከፈለጋችሁ ማስረጃዎችን እሰጣችኋለሁ፡፡ እናንተም የአላህ ሰዎች ከሆናችሁ እኔ እንደማደርገው አድርጉ፡፡ እኔ አንዲት ጠብታ ደም ጠብ ሳትል ቢላዋ በቀኝ ጎኔ አስገብቼ በግራ ጎኔ አወጣለሁ፡፡”የዚህን ጊዜ ሸይኹል አልባኒ እንዲህ አሉት፡- “አይ ቢላዋ አያስፈልገንም፡፡ እስፒል ይበቃል፡፡ እስፒል አቀብለኝማ ቅንጥህ ላይ ነው የምሰካልህ”ሱፍያው፡- ባንተ እጅ አይደለም በእኔ እጅ ነው መሆን ያለበት” አለ፡፡ሸይኹል አልባኒ፡- “አንተ ከአላህ ሰዎች ውስጥ አይደለህ? ባንተ እጅ ቢሆን በኔ እጅ ቢሆን ምን ልዩነት አለው?” አሉትሱፍዩ “በራሴ እጅ” ካልሆነ ብሎ እምቢ ብሎ መመለስ ያዘ፡፡ እየተመለሰ እያለ ሸይኹል አልባኒ እንዲህ አሉት “ሰለፊይ ልትቀልድበት አይመችህም!”ከሙነጂድ የተወሰደ