Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ›› ምክር ለውዷ እህቴ

‹‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ››
ምክር ለውዷ እህቴ
ውዷ እህቴ ሆይ! አላህ ይዘንልሽ እና እወቂ፤ ሂጃብ በአንቺ ላይ የደነገገው የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ አላህ ነው፡፡
ሀፍረት የአማኝ ሴት መገለጫ ነው፡፡ ወንዶችን ሌላ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ጀግንነት አይተሸ ትልቅ አድርገሽ ብታስቢያቸውም በሴት ጉዳይ ግን በጣም ደካማዎች ናቸው፡፡ የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሴት ልጅ ለወንድ ልጅ ከባድ ፈተና እንደሆነች ተናግረዋል፡፡ አሁንም የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ በኒ ኢስራኢል ወንዶች ፈተና እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ‹‹የመጀመሪያው የኢስራኤል ልጆች ፈተና ሴት ነበር እሱንም ወደቁ››፡፡
ታድያ ውዷ እህቴ ሆይ! ወንድ ልጅ በናንተ በሴቶች ጉዳይ እንዲህ ደካማ መሆኑን ካወቃችሁ ለምን አላህን አትፈሩም??? በአለባበሳችሁ፤ በአነጋገራችሁ፤ በምትቀባቡት እና በመሳሰለው???
ወንድ ልጅ እንዲሁም እንዲህ ነው ‹‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ›› እንደሚሉት አንቺ ውዷ እህቴ
1) ሂጃብ መስፈርቱን የማያሟላ አለባበስ ለብሰሽ፤
2) ድምፅሽን እያለሰለስሽ፤ ጮቅ ብለሽ እያወራሽ፤
3) ወንዶችን ሁሉ የሚፈትን ሽታ ያላቸው ነገሮች ሁሉ ተቀብተሸ፤
4) በየ ሶሻል ሚድያ (ፌስ ቡክ…..) ፎቶሽን እየለቀቅሽ፤ እና የመሳሰለውን እየፈፀምሽ
መንገድ ለመንገድ እየዞርሽ ወንዶችን መፈተኑ አይቀርብሽምን???
አላህን ፍሪ እህቴ፡፡ ወንድምሽ በሌላ ሴት ቢፈተን እንደማትፈልጊው ልብሽ ያውቀዋል፡፡ ታድያ አንቺ ለምን የአንዷ እህትሽን ልጅ፤ ወንድም፤ ባል፤ አባት ትፈትኛለሽ???
አላህን ፍሪ፤ አላህን እንፍራ፡፡
አላህ ሆይ! እኛንም እህቶቻችንንም አንተን ፍራቻ ለግሰን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያ ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻችው ላይ ይሁን፡፡