Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጓደኞቼ

‎<<°°°°>>   
               `````````````   
👥    ጓ     ደ  󾆚  ኞ     ቼ   👥
󾔧  ابو فوزان

    በዐረብኛው አባባል " ጀሊስ ወይም ጁለሳእ " ተብሎ የሚታወቀው ገለፃ አብዛኛውን ግዜህን አብረህ የምታሳልፈው ፣ አቀማማጭህ የሆነ የቅርብ ጓደኛ እንደ ማለት ነው። 

   ታዲያ ጓደኛ አድርገህ የያዝከው ጀሊስህ (አቀማማጭህ) ማነው ?

   ጓደኛችሁ  መልካም የሆነ ሙስሊም ከሆነ ጠበቅ አድርጋችሁ ያዙት። 
  
     ከተቻላችሁ እንዲያውም ተንጠልጠሉባቸው፣ ብዙ ይፈይዳሉና።

                ለመሆኑ
ከደህና ሰው መቅረብ ምን ይፈይዳል
     ደህናው ሰውስ ማን ነው  ?

አብዛኛው ሰው ____ ሆኗል ይባላል።

ለማንኛውም ከደህና ሰው ጋር ላስተዋውቃችሁ……… 

󾮜   ደህና ሰው የሚባለው 

~> ዲኑን በስርዓት የሚተገብር
~> መልካም ባህሪ ያለው 
~> ጌታውን የሚፈራ፣ 
~> ከሙሀረማት የሚርቅ…

*  ባጠቃላይ ጥሩ ዓርዓያ የሆኑ ሙስሊም ወንድ ወይም ሴትን ያጠቃልላል።

   ይህ ሲባል ግን 100% ስህተት የማይነካው፣ የማይወነጅል፣ ጥቡቅ ብሎም ምሉእ የሆነ ማለት አይደለም።

√ ጥቡቅነት ለነቢያት ብቻ ሲሆን፣ ይህም ጌታችን ሱብሃነሁ ወተዓላ ከኃጢኣት፣ ከስህተት ስለሚጠብቃቸው ነው።

√ ምሉእነት ደግሞ ለአላህ ፣አዝዘ ወጀልለ ብቻ የሚገባ ነው፣ ከጉድለት የጠራው የፀዳው ፣ እንከን አልባ የሆነው እሱ ብቻ ነው ።

    ፍጡር ሁሉ ደግሞ ምሉእነት (የተሟላ ፣ ቅዱስነት ፣ ከምንም እንከን የፀዳ) መሆን አይችልም ።

   እነሆ ከመካከላችን ወደ ዲን የተሻለ ቅርበት ያላቸው ፣ ጥሩ ሰዎችን እንጎዳኝ ።

 ለወንድሙ በቻለው አቅም እንዲጠቅም የአላህ መልእክተኛ
                  صلى الله عليه وسلم 
 የመከሩትን ይተገብራል። በዚህም እድለኛ ከሆንን ድጋፉ ይደርሰናል ።

   ጥሩነቱ ለራሱ ቢሆንም ከእንደዚህ አይነቱ ሰው መጎዳኘት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሰፊ ጠቀሜታ ኣለው።

               በመሆኑም
󾆚ጥሩ   ጓ  ደ  ኛ   ማፍራት 👥

አነሰ ቢባል  ምን ፋኢዳ ይኖረዋል  ?

     ምላሹን ከሸይኽ 
ዐብዱረህማን ቢን ናስር
አል ሰዕዲይ ረሂመሁላህ
        እንከታተል…
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻌﻼﻣﺔ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺑﻦ ﻧﺎﺻﺮ ﺍﻟﺴﻌﺪﻱ -ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﯽ :-" ﻭ ﺃﻗﻞ ﻣﺎ ﺗﺴﺘﻔﻴﺪﻩ ﻣﻦ ﺍﻟﺠﻠﻴﺲ ﺍﻟﺼﺎﻟﺢ. ﻭﻫﻲ ﻓﺎﺋﺪﺓ ﻻ ﻳﺴﺘﻬﺎﻥ ﺑﻬﺎ - ﺃﻥ ﺗﻨﻜّﻒ ﺑﺴﺒﺒﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﺴﻴﺌﺎﺕ ﻭ ﺍﻟﻤﻌﺎﺻﻲ ٬ ﺭﻋﺎﻳﺔ ﻟﻠﺼﺤﺒﺔ ٬ ﻭ ﻣﻨﺎﻓﺴﺔ ﻓﻲ ﺍﻟﺨﻴﺮ ٬ ﻭ ﺗﺮﻓﻌﺎ ﻋﻦ ﺍﻟﺸﺮ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﻳﺤﻔﻈﻚ ﻓﻲ ﺣﻀﺮﺗﻚ ﻭ ﻣﻐﻴﺒﻚ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﺗﻨﻔﻌﻚ ﻣﺤﺒﺘﻪ ﻭﺩﻋﺎﺅﻩ ﻓﻲ ﺣﻴﺎﺗﻚ ﻭ ﺑﻌﺪ ﻣﻤﺎﺗﻚ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﻳﺪﺍﻓﻊ ﻋﻨﻚ ﺑﺴﺒﺐ ﺍﺗﺼﺎﻟﻪ ٬ ﻭ ﻣﺤﺒﺘﻪ ﻟﻚ ﺃﻣﻮﺭﺍ ﻻ ﺗﺒﺎﺷﺮ ﺃﻧﺖ ﻣﻮﺍﻗﻌﺘﻬﺎ ٬ ﻛﻤﺎ ﺃﻧﻪ ﻗﺪ ﻳﺼﻠﻚ ﺑﺄﺷﺨﺎﺹ ﻭ ﺃﻋﻤﺎﻝ ﻳﻨﻔﻌﻚ ﺍﺗﺼﺎﻟﻚ ﺑﻬﻢ . ﻭ ﻓﻮﺍﺋﺪ ﺍﻷﺻﺤﺎﺏ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ ﻻ ﺗﻌﺪ ﻭ ﻻ ﺗﺤﺼﯽ ٬ ﻭ ﺣﺴﺐ ﺍﻟﻤﺮﺀ ﺃﻥ ﻳﻌﺘﺒﺮ ﺑﻘﺮﻳﻨﻪ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﻳﻜﻮﻥ ﻋﻠﯽ ﺩﻳﻦ ﺧﻠﻴﻠﻪ"
"󾔁 ﺑﻬﺠﺔ ﻗﻠﻮﺏ ﺍﻷﺑﺮﺍﺭ "
    للعلامة الشيخ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ 
       ﺑﻦ ﻧﺎﺻﺮ ﺍﻟﺴﻌﺪﻱ -
        ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﯽ 
__________________
 
¹• « በትንሹም ቢሆን ከመልካም ጓደኛ
(ከጀሊስህ፣ማለትም ከአቀማማጭህ)
የምትጠቀመው የማይናቅ ፋኢዳህ (ጥቅም) ኣለህ። 

²•  ከሱ ጋር ያለህ ጓደኝነት እንዳይበላሽ፣ መልካም ተግባር ላይ ለመሽቀዳደም ፣ እና ከመጥፎ ነገርም ራስህን ለማቀብ  ስትል ኃጢኣቶችን፣ ወንጀሎችን ከመስራት ትቆጠባለህ። 

³•  አብረኸው እያለህም ይሁን በሌለህበትም ጥበቃ ክትትል ያደርግልሃል ።

⁴•  የሚለግስህ ውዴታና የሚያደርግልህ መልካም ዱዓእ በህይወት እያለህም ሆነ ከሞትክም በኋላ ይጠቅመሃል። 

⁵•  አንተ ይደርስብኛል ብለህ ያልገመትከውንና በቦታውም መገኘት ያልቻልከውን ችግርህን ካየ እሱ እንዳንተ ሆኖ ይመክትልሃል። 

⁶•  ብትገናኝ ሊጠቅሙህ ከሚችሉ ግለሰቦችና ስራዎች ጋርም ያገናኘሃል። 

⁷•  የመልካም ጓደኞች ፋኢዳ ወይም ጥቅም ተቆጥሮ አያልቅም። 

⁸•  እንደየ ግለሰቡ ቁርኝት ይገለፃል።
   " ሰውየው በወዳጁ ዲን ላይ ነው የሚገኘው "  እንደተባለውም  ይሆናል። »

☑  እሱን ጓደኝነቱን ላለማጣት፣ በሱ ዘንድ ዝቅ ብለህ ላለመታየት ስትል በመጥፎ ተግባራትህ ታፍርና ራስህን ታሻሽላለህ።
 
☑  የምትፈልገው ጓደኛህ ነውና ልክ እንደሱ ሁሉ እየተከተልከው የዲንህን ግዴታዎች ለመወጣት ትታገላለህ።

☑  በዚህ ጓደኛህና በሱ ሰበብ ካወቅካቸው በሌሎቹ ጓደኞቹ ፊት ላለመዋረድ ትጥራለህ።

~ ውድቅ ቦታ ባለመገኘትም ራስህን ከፍ ታደርጋለህ።  

☑   እነሆ የዚህ አይነቱ ጓደኛህ በጣም የሚወደድም የሚቀረብም ነው።

 ~•  ክብርህን፣ ገንዘብህን፣ ህይወትህን ሆነ ቤተሰብና ንብረትህን ችላ አይልም። 

~•  የኔ ነው የምትለውን ነገር በቻለው አቅምና ሁኔታ ለአደጋ እንዳይጋፈጥ ይከላከልልሃል ። ልክ እንደራሱ ጉዳይ ይመለከተዋል።

☑  ስለሚወድህና ሁሉ ነገሩ ከልቡ ለአላህ ብሎ ስለሆነም ሁሌም መልካምን ይመኝልሃል።

~• ክፉ ነገር እንዲወገድልህ፣ መልካም እድል እንዲገጥምህ ባስታወሰህ ልክ ዱዓእ ስለሚያደርግልህ በውዴታው ተጠቃሚ ነህ።

☑  ካንተ ጋር መልካም ግንኙነትና ወዳጅነት ስላለውና ለተጎዳኘው ሰው መልካም መዋል እንዳለበት ስለሚያምን በዲንህ፣ በክብርህ፣ በህይወትህ፣ በንብረትህና በቤተሰብህ የመጣ ጎጂ ነገር ካየ ከሰማ ችላ ሳይል ይከላከልልሃል።

☑  መልካም መረጃዎችን ሳይሰስት ያቀብለሃል ። ስለሆነም ለራሱ ሚወደውንና ሚፈልገውን መልካም ነገር ላንተም ከማካፈል፣ ከመጠቆም ብሎም ከማመቻቸት ወደ ኋላ አይልም።

☑ በዚህ ርዕስ ዙርያ ይህች ለናሙናና እንዲያው በጥቂቱ የምናገኘውን ፋኢዳ ለመጠቆም የቀረበች ማስታወሻ ናት እንጂ በጣም ብዙ ፅሁፍ ማቅረብ ይቻላል።
  
~• ምክንያቱም የመልካም ጓደኛን ጥቅም በጥሞና ስናስተውል እጅግ በርካታ ቁምነገሮችን እናገኝበታለን።

☑  መቸም ሁሉ ሰው አንድ አይነት ባህሪ እንደሌለው እንስማማለን፣  በመሆኑም የምታገኘው ጥቅምም እንደተቀባዩና እንደሰጪው ይለያያል።

~•  እንኳንስ ውድቁ ጓደኝነት ይቅርና የመረጥከው የመልካም ጓደኛ አይነትም ኣንዱ ካንዱ ይበላለጣል። 

~•  ወዳጅ አድርገህ የምትይዘው ሰው ተፅእኖ በጣም ከባድ ነው። 

~• ንግግሩን ትሰማዋለህ
~• አስተያየቱን ትቀበለዋለህ
~• ምክሩን ትሰራበታለህ
~• የወደደውን ትወዳለህ
~• የጠላውን ትጠላለህ
~• ቀልዱ ጨዋታው ይመቸሃል
~• ትደግፈዋለህ ትታዘዘዋለህ
~• የበላይነቱን ስለተቀበልክ
      ትከተለዋለህ።

 ስለዚህም መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት:

  قال النبي صلى الله عليه وسلم :
" المرء على دين خليله فلينظر أحدكم من يخالل. "    رواه أحمد وغيره

« አንድ ግለሰብ በወዳጁ (በጓደኛው) ዲን ላይ ነውና የሚገኘው ማንን በወዳጅነት እንደያዘ ያስተውል (ያጥና) ። »

󾮜 እንዲሁም ሰው ሰው ነው እኔ ጥሩውን ወስጄ መጥፎ ነገሩን እጥላለሁ ወይም እተዋለሁ እንዳትል ባብዛኛው ከመጥፎ መጥፎነትን እንጂ ደህና ነገሩን መውረስ እንደማይቻልህ ጠቁመውሃል።

 " مثل الجليس الصالح وجليس السوء كحامل المسك ونافخ الكير. "
 رواه البخاري ومسلم

« የመልካም ጓደኛ (ጀሊስ፣አቀማማጭ) እና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌው ምስክ እንደያዘና (እንደሚነግድና) ወናፍ እንደሚነፋ ሰው ብጤ ነው። » 

󾮜 ጥሩ ጠረን ያለው ነገር የያዘ ሰው ዘንድ ከተቀመጥክ ያንኑ ጥሩ ሽታ ትላበሳለህ።

󾮜 መጥፎ ጠረን ያለው ነገር ጋር የሚውል ሰው ጋር ከዋልክም ያንኑ ክፉ ሽታ መላበስህ አይቀርም።

󾮜 በሌላ በኩል መጥፎ ጓደኞች ጥፋት እያሰሩህ፣ ወደ ክፋት እየነዱህና እያበላሹህ ከርመው የቁርጥ ቀን ላይ እንደማያውቁህ ይሆኑብሃል ይክዱሃል።

󾮜 በተቃራኒው መልካሞቹ ፈሪሃ አላህ የሆኑ ጓደኞች ካለን ግን ከላይ እንደተብራራው መቸም ቢሆን ያቅማቸውን ያህል ከጎናችን ይሰለፋሉ።

قال تعالى: { الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِين. }
َ {الزخرف:67}

« ወዳጆች በዚያን ቀን ከፊሎች ለከፊሎች ጠላት ናቸው። አላህን ፈሪዎች የሆኑት ሲቀሩ። »
አልዙክሩፍ:67

                 """"""""""""
* የሃሳቡ ምንጭና መነሻ 
  በህጀቱ ቁሉቢል አብራር

* ተጨማሪ ማብራርያዎች
ከተለያዩ የቁርኣንና ሀዲስ መልእክቶች

አላህ ከመልካሞች የምንጎዳኝ ያድርገን
መጥፎነታችንንም ያንሳልን ያስወግድልን
_____________________
16 ሰፈር 1436
󾔧Abufewzan 09 Dec 14
°°°°<<<<<<<•••>>>>>>>°°°°‎

👥 ጓ ደ 👤 ኞ ቼ 👥
ابو فوزان
በዐረብኛው አባባል " ጀሊስ ወይም ጁለሳእ " ተብሎ የሚታወቀው ገለፃ አብዛኛውን ግዜህን አብረህ የምታሳልፈው ፣ አቀማማጭህ የሆነ የቅርብ ጓደኛ እንደ ማለት ነው።
ታዲያ ጓደኛ አድርገህ የያዝከው ጀሊስህ (አቀማማጭህ) ማነው ?
ጓደኛችሁ መልካም የሆነ ሙስሊም ከሆነ ጠበቅ አድርጋችሁ ያዙት።
ከተቻላችሁ እንዲያውም ተንጠልጠሉባቸው፣ ብዙ ይፈይዳሉና።
ለመሆኑ
ከደህና ሰው መቅረብ ምን ይፈይዳል
ደህናው ሰውስ ማን ነው ?
አብዛኛው ሰው ____ ሆኗል ይባላል።
ለማንኛውም ከደህና ሰው ጋር ላስተዋውቃችሁ………
ደህና ሰው የሚባለው
~> ዲኑን በስርዓት የሚተገብር
~> መልካም ባህሪ ያለው
~> ጌታውን የሚፈራ፣
~> ከሙሀረማት የሚርቅ…
* ባጠቃላይ ጥሩ ዓርዓያ የሆኑ ሙስሊም ወንድ ወይም ሴትን ያጠቃልላል።
ይህ ሲባል ግን 100% ስህተት የማይነካው፣ የማይወነጅል፣ ጥቡቅ ብሎም ምሉእ የሆነ ማለት አይደለም።
√ ጥቡቅነት ለነቢያት ብቻ ሲሆን፣ ይህም ጌታችን ሱብሃነሁ ወተዓላ ከኃጢኣት፣ ከስህተት ስለሚጠብቃቸው ነው።
√ ምሉእነት ደግሞ ለአላህ ፣አዝዘ ወጀልለ ብቻ የሚገባ ነው፣ ከጉድለት የጠራው የፀዳው ፣ እንከን አልባ የሆነው እሱ ብቻ ነው ።
ፍጡር ሁሉ ደግሞ ምሉእነት (የተሟላ ፣ ቅዱስነት ፣ ከምንም እንከን የፀዳ) መሆን አይችልም ።
እነሆ ከመካከላችን ወደ ዲን የተሻለ ቅርበት ያላቸው ፣ ጥሩ ሰዎችን እንጎዳኝ ።
ለወንድሙ በቻለው አቅም እንዲጠቅም የአላህ መልእክተኛ
صلى الله عليه وسلم
የመከሩትን ይተገብራል። በዚህም እድለኛ ከሆንን ድጋፉ ይደርሰናል ።
ጥሩነቱ ለራሱ ቢሆንም ከእንደዚህ አይነቱ ሰው መጎዳኘት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሰፊ ጠቀሜታ ኣለው።
በመሆኑም
👤ጥሩ ጓ ደ ኛ ማፍራት 👥
አነሰ ቢባል ምን ፋኢዳ ይኖረዋል ?
ምላሹን ከሸይኽ
ዐብዱረህማን ቢን ናስር
አል ሰዕዲይ ረሂመሁላህ
እንከታተል…
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻌﻼﻣﺔ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺑﻦ ﻧﺎﺻﺮ ﺍﻟﺴﻌﺪﻱ -ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﯽ :-" ﻭ ﺃﻗﻞ ﻣﺎ ﺗﺴﺘﻔﻴﺪﻩ ﻣﻦ ﺍﻟﺠﻠﻴﺲ ﺍﻟﺼﺎﻟﺢ. ﻭﻫﻲ ﻓﺎﺋﺪﺓ ﻻ ﻳﺴﺘﻬﺎﻥ ﺑﻬﺎ - ﺃﻥ ﺗﻨﻜّﻒ ﺑﺴﺒﺒﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﺴﻴﺌﺎﺕ ﻭ ﺍﻟﻤﻌﺎﺻﻲ ٬ ﺭﻋﺎﻳﺔ ﻟﻠﺼﺤﺒﺔ ٬ ﻭ ﻣﻨﺎﻓﺴﺔ ﻓﻲ ﺍﻟﺨﻴﺮ ٬ ﻭ ﺗﺮﻓﻌﺎ ﻋﻦ ﺍﻟﺸﺮ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﻳﺤﻔﻈﻚ ﻓﻲ ﺣﻀﺮﺗﻚ ﻭ ﻣﻐﻴﺒﻚ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﺗﻨﻔﻌﻚ ﻣﺤﺒﺘﻪ ﻭﺩﻋﺎﺅﻩ ﻓﻲ ﺣﻴﺎﺗﻚ ﻭ ﺑﻌﺪ ﻣﻤﺎﺗﻚ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﻳﺪﺍﻓﻊ ﻋﻨﻚ ﺑﺴﺒﺐ ﺍﺗﺼﺎﻟﻪ ٬ ﻭ ﻣﺤﺒﺘﻪ ﻟﻚ ﺃﻣﻮﺭﺍ ﻻ ﺗﺒﺎﺷﺮ ﺃﻧﺖ ﻣﻮﺍﻗﻌﺘﻬﺎ ٬ ﻛﻤﺎ ﺃﻧﻪ ﻗﺪ ﻳﺼﻠﻚ ﺑﺄﺷﺨﺎﺹ ﻭ ﺃﻋﻤﺎﻝ ﻳﻨﻔﻌﻚ ﺍﺗﺼﺎﻟﻚ ﺑﻬﻢ . ﻭ ﻓﻮﺍﺋﺪ ﺍﻷﺻﺤﺎﺏ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ ﻻ ﺗﻌﺪ ﻭ ﻻ ﺗﺤﺼﯽ ٬ ﻭ ﺣﺴﺐ ﺍﻟﻤﺮﺀ ﺃﻥ ﻳﻌﺘﺒﺮ ﺑﻘﺮﻳﻨﻪ ٬ ﻭ ﺃﻥ ﻳﻜﻮﻥ ﻋﻠﯽ ﺩﻳﻦ ﺧﻠﻴﻠﻪ"
"📙 ﺑﻬﺠﺔ ﻗﻠﻮﺏ ﺍﻷﺑﺮﺍﺭ "
للعلامة الشيخ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ
ﺑﻦ ﻧﺎﺻﺮ ﺍﻟﺴﻌﺪﻱ -
ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﯽ
__________________
¹• « በትንሹም ቢሆን ከመልካም ጓደኛ
(ከጀሊስህ፣ማለትም ከአቀማማጭህ)
የምትጠቀመው የማይናቅ ፋኢዳህ (ጥቅም) ኣለህ።
²• ከሱ ጋር ያለህ ጓደኝነት እንዳይበላሽ፣ መልካም ተግባር ላይ ለመሽቀዳደም ፣ እና ከመጥፎ ነገርም ራስህን ለማቀብ ስትል ኃጢኣቶችን፣ ወንጀሎችን ከመስራት ትቆጠባለህ።
³• አብረኸው እያለህም ይሁን በሌለህበትም ጥበቃ ክትትል ያደርግልሃል ።
⁴• የሚለግስህ ውዴታና የሚያደርግልህ መልካም ዱዓእ በህይወት እያለህም ሆነ ከሞትክም በኋላ ይጠቅመሃል።
⁵• አንተ ይደርስብኛል ብለህ ያልገመትከውንና በቦታውም መገኘት ያልቻልከውን ችግርህን ካየ እሱ እንዳንተ ሆኖ ይመክትልሃል።
⁶• ብትገናኝ ሊጠቅሙህ ከሚችሉ ግለሰቦችና ስራዎች ጋርም ያገናኘሃል።
⁷• የመልካም ጓደኞች ፋኢዳ ወይም ጥቅም ተቆጥሮ አያልቅም።
⁸• እንደየ ግለሰቡ ቁርኝት ይገለፃል።
" ሰውየው በወዳጁ ዲን ላይ ነው የሚገኘው " እንደተባለውም ይሆናል። »
☑ እሱን ጓደኝነቱን ላለማጣት፣ በሱ ዘንድ ዝቅ ብለህ ላለመታየት ስትል በመጥፎ ተግባራትህ ታፍርና ራስህን ታሻሽላለህ።
☑ የምትፈልገው ጓደኛህ ነውና ልክ እንደሱ ሁሉ እየተከተልከው የዲንህን ግዴታዎች ለመወጣት ትታገላለህ።
☑ በዚህ ጓደኛህና በሱ ሰበብ ካወቅካቸው በሌሎቹ ጓደኞቹ ፊት ላለመዋረድ ትጥራለህ።
~ ውድቅ ቦታ ባለመገኘትም ራስህን ከፍ ታደርጋለህ።
☑ እነሆ የዚህ አይነቱ ጓደኛህ በጣም የሚወደድም የሚቀረብም ነው።
~• ክብርህን፣ ገንዘብህን፣ ህይወትህን ሆነ ቤተሰብና ንብረትህን ችላ አይልም።
~• የኔ ነው የምትለውን ነገር በቻለው አቅምና ሁኔታ ለአደጋ እንዳይጋፈጥ ይከላከልልሃል ። ልክ እንደራሱ ጉዳይ ይመለከተዋል።
☑ ስለሚወድህና ሁሉ ነገሩ ከልቡ ለአላህ ብሎ ስለሆነም ሁሌም መልካምን ይመኝልሃል።
~• ክፉ ነገር እንዲወገድልህ፣ መልካም እድል እንዲገጥምህ ባስታወሰህ ልክ ዱዓእ ስለሚያደርግልህ በውዴታው ተጠቃሚ ነህ።
☑ ካንተ ጋር መልካም ግንኙነትና ወዳጅነት ስላለውና ለተጎዳኘው ሰው መልካም መዋል እንዳለበት ስለሚያምን በዲንህ፣ በክብርህ፣ በህይወትህ፣ በንብረትህና በቤተሰብህ የመጣ ጎጂ ነገር ካየ ከሰማ ችላ ሳይል ይከላከልልሃል።
☑ መልካም መረጃዎችን ሳይሰስት ያቀብለሃል ። ስለሆነም ለራሱ ሚወደውንና ሚፈልገውን መልካም ነገር ላንተም ከማካፈል፣ ከመጠቆም ብሎም ከማመቻቸት ወደ ኋላ አይልም።
☑ በዚህ ርዕስ ዙርያ ይህች ለናሙናና እንዲያው በጥቂቱ የምናገኘውን ፋኢዳ ለመጠቆም የቀረበች ማስታወሻ ናት እንጂ በጣም ብዙ ፅሁፍ ማቅረብ ይቻላል።
~• ምክንያቱም የመልካም ጓደኛን ጥቅም በጥሞና ስናስተውል እጅግ በርካታ ቁምነገሮችን እናገኝበታለን።
☑ መቸም ሁሉ ሰው አንድ አይነት ባህሪ እንደሌለው እንስማማለን፣ በመሆኑም የምታገኘው ጥቅምም እንደተቀባዩና እንደሰጪው ይለያያል።
~• እንኳንስ ውድቁ ጓደኝነት ይቅርና የመረጥከው የመልካም ጓደኛ አይነትም ኣንዱ ካንዱ ይበላለጣል።
~• ወዳጅ አድርገህ የምትይዘው ሰው ተፅእኖ በጣም ከባድ ነው።
~• ንግግሩን ትሰማዋለህ
~• አስተያየቱን ትቀበለዋለህ
~• ምክሩን ትሰራበታለህ
~• የወደደውን ትወዳለህ
~• የጠላውን ትጠላለህ
~• ቀልዱ ጨዋታው ይመቸሃል
~• ትደግፈዋለህ ትታዘዘዋለህ
~• የበላይነቱን ስለተቀበልክ
ትከተለዋለህ።
ስለዚህም መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት:
قال النبي صلى الله عليه وسلم :
" المرء على دين خليله فلينظر أحدكم من يخالل. " رواه أحمد وغيره
« አንድ ግለሰብ በወዳጁ (በጓደኛው) ዲን ላይ ነውና የሚገኘው ማንን በወዳጅነት እንደያዘ ያስተውል (ያጥና) ። »
እንዲሁም ሰው ሰው ነው እኔ ጥሩውን ወስጄ መጥፎ ነገሩን እጥላለሁ ወይም እተዋለሁ እንዳትል ባብዛኛው ከመጥፎ መጥፎነትን እንጂ ደህና ነገሩን መውረስ እንደማይቻልህ ጠቁመውሃል።
" مثل الجليس الصالح وجليس السوء كحامل المسك ونافخ الكير. "
رواه البخاري ومسلم
« የመልካም ጓደኛ (ጀሊስ፣አቀማማጭ) እና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌው ምስክ እንደያዘና (እንደሚነግድና) ወናፍ እንደሚነፋ ሰው ብጤ ነው። »
ጥሩ ጠረን ያለው ነገር የያዘ ሰው ዘንድ ከተቀመጥክ ያንኑ ጥሩ ሽታ ትላበሳለህ።
መጥፎ ጠረን ያለው ነገር ጋር የሚውል ሰው ጋር ከዋልክም ያንኑ ክፉ ሽታ መላበስህ አይቀርም።
በሌላ በኩል መጥፎ ጓደኞች ጥፋት እያሰሩህ፣ ወደ ክፋት እየነዱህና እያበላሹህ ከርመው የቁርጥ ቀን ላይ እንደማያውቁህ ይሆኑብሃል ይክዱሃል።
በተቃራኒው መልካሞቹ ፈሪሃ አላህ የሆኑ ጓደኞች ካለን ግን ከላይ እንደተብራራው መቸም ቢሆን ያቅማቸውን ያህል ከጎናችን ይሰለፋሉ።
قال تعالى: { الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِين. }
َ {الزخرف:67}
« ወዳጆች በዚያን ቀን ከፊሎች ለከፊሎች ጠላት ናቸው። አላህን ፈሪዎች የሆኑት ሲቀሩ። »
አልዙክሩፍ:67
""""""""""""
* የሃሳቡ ምንጭና መነሻ
በህጀቱ ቁሉቢል አብራር
* ተጨማሪ ማብራርያዎች
ከተለያዩ የቁርኣንና ሀዲስ መልእክቶች
አላህ ከመልካሞች የምንጎዳኝ ያድርገን
መጥፎነታችንንም ያንሳልን ያስወግድልን
_____________________
16 ሰፈር 1436  Abufewzan 09 Dec 14

Post a Comment

0 Comments