Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን የታሉ እነዛ ኳስ ጨዋታ .......

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
የታሉ እነዛ ኳስ ጨዋታ ያለ ቀን መስጂዶችን ትተው በየዲሽ ቤቱ የሚያዘወትሩት?????
እኮ የት ሄዱ የአላህን ቤት ባዶ አድርገው በየዲሽ ቤቱ ጀመዓ ሰላት የሚያስመልጡ??? አረ ብሎም ለኳስ ሲሉ ሰላት የማይሰግዱት የታሉ???
አንተ የአላህ ባርያ ሆይ! ጀመዐ ሰላትን ትተህ (በወንድ ልጅ ላይ ግዴታ የሆነውን) ኳስ እየተመለከትክ ካለንበት ፈተና መውጣት ታስባለህን??? ነፍስህን አታታላት። ሙስሊም አደለም በዚህ በፈተና ወቅት በሰላሙም ጊዜ
1) የሽርክ መንዙማ እየሰማ አይደለቅም፣
2) ቢድአ ላይ አይዘፈቅም፣
3) ኳስ ብሎ በወቅቱ አያላግጥም፣
4) የትኛውም ቻናል ያስተላልፈው (የካፊርም ይሁን የሙስሊም ጣቢያ) ድራማ እያለ ውሸትን፣ ቅጥፈትን አይመለከትም፣
5) ሴቷ ለብሳ ያለበሰች የተባለውብ አለባበስ አታደርግም፣

ይልቁንስ ባለንበት ዘመን ወደ አላህ ቁርአን በመቅራት፣ በማልቀስ፣ ምህረትን ከአላህ በመጠየቅ፣ አላህ ያዘዘውን ሁሉ በመስራት፣ የከለከለውን ሁሉ በመከልከል ወደ እርሱ የምንቃረብበት ነበር።
አላህ ልብ ይስጠን። አላህ ሆይ! የኳስን ፍቅር ከወንድሞቻችን ልብ ውስጥ ነቅለህ አውጣው፣ አንተ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነህ እና።