Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነሺዳ

======== ነሺዳ======
ዑለማዑል ሱና ግጥምን ነሺዳም ብለው ይጠሩታል ፤ ነሺዳ በሚል ስም ሁክም የሰጡት ሁሉ ለዘንድሮ በሲዲ የሚሰራጨውን አልፎ ተርፎ በኮምፒዩተር የድምፁ ቃና ተቀይሮ ሳውንድ ኢፌክት ተከቶበት በቅላፄ የሚያቀነቅኑትን ነው ለማለት አያስይዝም ።
አንዳንዶች ነሺዳ ለመፈቀዱ የሚያነሷቸው የዑለማዎች ፈታዋ እጅጉን የቆዩና በዛን ወቅት ነሺዳ የተባለው ዜማ እንዲህ ቁርዓንን አስጥሎ ወጣቱ በቃሉ እያፈዘው በሞባይሉ እያደመጠው ፤ አልፎተርፎ የሚገባበዘውን አይደለም ፤ እነርሱ (ዑለማዎች) ነሺዳን እዚህ ጋር መግለፅ የፈለጉበት መልካም መልዕክትን ያዘሉ ከካፊሮች ጋር በማይመሳሰልና በ ኤዲት ኢፌክት ያልታጀበ በጥሩ ይዘት የተቀነቀነ ግጥምን ነው ።
አንዳንዶች ለነርሱ የነሺዳ መልካም ፍቃድነትና ከሸሪዓ አይጋጭም ብለው የሚያመጧቸው ፈታዋዎችን የሰጧቸው ዑለማዎች ግጥምን በነሺዳ ስም ከመጥራታቸው አንስቶ እነዚህን ፈታዋዎች የሰጡባቸውን ዐመታትን ብንመለከት በጣም የቆዩና ከዛም ብኋላ ይሄ ኢስላማዊ አናሺድ ወደ ገንዘብ ችብቸባ በተገባበት አሁን ያለንበትን ዘመን ይመስል ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎች ተጠይቀው በሚገርም ሁኔታ አንዳንዱ እስከ ሃራም ደረጃ ያደረሰውም እንዳለ ማየቱ ተገቢ ነው ።
ዊኪፒዲያ እንደሚጠቁመን ከሆነ የመጀመሪያው ሲዲ የተመረተበትንና የዑለማዎቹን ፈታዋ በምናስተያይበት ወቅት ዑለማዎች በዛን ወቅት የሰጡት ፈታዋ አሁን ላይ በኢስላም ስም ቢዝነስ ተደርጎ የተያዘውን የኢስላማዊ ነሺዳ እንደማይወክል በቀላሉ መረዳት ያስችለናል።
_____________
ይሄን ለመረዳት ኢስላማዊ ነሺዳ በሚል ስም በ አሁኑ ወቅትን የሚሰራጨውን ያወገዙበትን የተለያዩ ዑለማዎች ፈታዋ በድምፅ ለመስማት ቀጥለው የሚታዩትን ሊንኮች በመጫን መስማት ይቻላል
___________
ኢብኑ ባዝ
https://app.box.com/shared/k8su03a6hm
ዑሰይሚን
https://app.box.com/shared/lgkplx1z9k
ፈውዛን
https://app.box.com/shared/ic8rt8c98x
አህመድ አነጅሚ
https://app.box.com/shared/bae9vvnntt
አል አልባኒ
https://app.box.com/shared/uillxjvexa
ረህመቱላሂ አለይሂም ጀሚዐን

Post a Comment

0 Comments