Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰለፎቻችን ልጆቻቸውን ለሽርክና ለቢድዐ አሳልፈው አይሰጡም ነበር !


ሰለፎቻችን ልጆቻቸውን ለሽርክና ለቢድዐ አሳልፈው አይሰጡም ነበር !

--------
ቢድዐ የነገራቶች ሁሉ ክፉ ራስ ነው ። ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሳቸው ጊዜ አንዲትም ቢድዐ ሳይኖር በየሳምንቱ ኹጥባ ሚንበር ላይ ሰሐቦችን “መጤ ነገር ሁሉ ቢድዐ ነው፡፡ ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፡፡ ጥመት ሁሉ ወደ እሳት ነው” ብለው ያስጠነቅቋቸው ነበር ። ሆኖም ጊዜ አልፎ አሁን ያለንበት ጊዜ ላይ ተገኝተናል ። ቢድዐው እንደ ሱና ሱናው እንደ ቢድዐ የተቆጥረበት ዘመን ። ታዲያ ይሄን መጤ የዲን ላይ ፈጠራ እራሳችን ተጠንቅቀን ቤተሰቦቻችንን ማስጠንቀቅ በኛ ላይ ግዴታ ነው ። ለአብነት ያክል ሰለፎች ልጆቻቸውን እንዴት እንደነበሩ እንቃኝ ።
-------

ጠቢቡ ሉቅማን ዐለይሂ ሰላም ለልጁ እንዲህ ብሎ መክሮታል ብሎ አላህ ይነግረናል
« ልጄ ሆይ፦ በአላህ ላይ ማንንም አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና አለው »
[ሉቅማን ]

መዕማር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላል:- « ጣውስ ረሒመሁላህ እና ልጁ ቁጭ ባሉበት አንድ ከሙዕተዚላ (የቢድዐ አንጃ) የሆነ ሰው ወደነርሱ ገባ ከዚያም ጣውስ የእጆቹን ጣቶች ወደ ጆሮው ውስጥ አስገባና ለልጁ እንዲህ አለው:- “ልጄ ሆይ ጣቶችህን ወደ ጆሮህ ስደድ! ምንም ነገር ከዚህ ሰውዬ እንዳትሰማ! ይህ ልብ ደካማ ነው!” ። ከዚያም እንዲህ አለው:- “ልጄ ሆይ ጣቶችህን በደንብ አስገባ! በደንብ.. በደንብ.. ” ሰውየው (ሙዕተዚሊው) ተነስቶ እስኪወጣ ድረስ “ በደንብ ..” ማለትን አላቋረጠም ..»
[አል ላሊካዒ ሸርሑ ዑሱሉል ኢዕቲቃድ በቁጥር (1/247)በተለየ አገላለፅ ዘግበውታል ]

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:-
« የሚወዳትን ሴት ልጁን ለቢድዐ አራማጅ የዳረ ከሷ ጋር ያለውን ግንኙንት አቋርጧል»
[አል በርበሐሪ ]

ኢማም አል በርበሐሪ ሸርሑ ሱንናህ የሚለው ኪታባቸው ላይ እንዲህ አሉ:-
« ዩኑስ ቢን ዑበይድ ረሒመሁላህ ልጃቸው ከአንድ የጥመት ሰው ቤት ሲወጣ ያዩታል ከዚያም እንዲህ ብለው ይጠይቁታል:- “ልጄ ሆይ! ከየት ነው የወጣከው ? ልጁም:- “ከአሚር ቢን ዑበይድ (የቢድዐ አራማጅ) ቤት” ይላቸዋል እሳቸውም:- “ ልጄ ሆይ ከዚህ ባለጌ እና ሐፍረተ ቢስ ከሆነ ሰውዬ ቤት ስትወጣ ከማይህ ከነዚህ (ቀጥሎ ከጠቀሷቸው) ሰዎች ቤት ወጥተህ አላህን ብትገናኝ እኔ ዘንድ ተወዳጅ ነው። ልጄ ሆይ! ከጥመት ሰዎች ንግግር ላይ ሆነህ ጌታህን ከምትገናኘው እንደ ዝሙተኛ ፣ እንደ ግልፅ አመፀኛ ፣ እንደሌባ ፣ እንደከዳተኛ ሆነህ ብትገናኘው ለኔ ተወዳጅ ነው” ..»

ለታላቁ ዓሊም ማሊክ ቢን ሙጝየል (ረሒመሁላህ) እንዲህ ተብሎ ተነገራቸው:-
« “ ልጅህ ከአዕዋፋት ጋር ሲጫወት አየውት” ማሊክም እንዲህ አሉ “ እንዴት መልካም ነው ከቢድዓ አራማጆች ጋር ጓደኛ ከመሆን ስላዘናጉት (አዕዋፋቱ)” ..»
[አሸርሑ ወል ኢባናህ ሊኢብኑ በጣህ (#90)]

አርታህ ቢኑል ሙንዲር (ረሒመሁላህ) እንዲህ አሉ
« “ ልጄ የስሜት ተከታይ (የቢድዐ ሰው) ከሚሆን ከፋሲቆች የሆነ ፋሲቅ ቢሆን እኔ ዘንድ የተሻለ ነው” ..»
[አሸርሑ ወል ኢባናህ]

ሐማድ ቢን ዘይድ (ረሒመሁላህ) እንዲህ አሉ:- « ዩኑስ ቢን ዑበይድ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብሎ ነገረኝ:-
“ሐማድ ሆይ! አንድን ወጣት ምንም እኩይን ሲሰራ ተስፋ አልቆርጥበትም! ከቢድዐ አራማጅ ጋር አብሮ እስካላየሁት ድረስ (ከቢድዐ ባለቤት ጋር) ካየሁት ግን እንደጠፋ አውቃለው” ..»
[አሸርሑ ወል ኢባናህ]

Post a Comment

0 Comments