Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በልደት ቀናቸው ቢፆሞ ኖሮ ታድያ ለምንድን ነው አመት ጠብቀው ያቺ የተወለዱባትን ቀን ያልፆሙት?????

በልደት ቀናቸው ቢፆሞ ኖሮ ታድያ ለምንድን ነው አመት ጠብቀው ያቺ የተወለዱባትን ቀን ያልፆሙት?????
================================

የተለመደው የሱፍዬች እና የአህባሾች ማምታቻ መውሊድን በተመለከተ ሲጋለጥ
እንዲህም ይላሉ ‹‹ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን በመፆም የተወለዱበትን ቀን አክብረዋል››

ይሄ በመውሊድ ወቅት ሰው ዘንድ የተሰራጨ ብዥታቸው ነው ‹‹መውሊድ ማክበር ችግር የለውም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እራሳቸው ሰኞን በመፆም ስላከበሩት፡፡›› ነገር ግን ይሄ ቅጥፈት ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ ላይ ውሸትን የሚቀጥፍ ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
ሀዲሱ እንዲህ ነው የሚለው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን ስለመፆማቸው ተጠየቁ እሳቸውም ‹‹በዛ (ቀን) ተወለድኩ እናም በዛው ቀን ወህይ (መለኮታዊ ራዕይ) ወረደልኝ›› ሰሂህ ሙስሊም (1162)
እውነታው የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደታቸውን አላከበሩም፡፡ የተወለዱበትን ቀን ሰኞ ፆሙ እንጂ በልደት ቀናቸው አልፆሙም፡፡ በሁለቱ መሃል በጣም ሰፊ ልዩነት አለ ድጋሚ አንብቡት ወንድም እና እህቶች፡፡

‹የፆሙት በተወለዱበት (ሰኞ) ቀን እንጂ አመት ተጠብቆ የምትመጣዋን የልደት በዓልዋ ቀን አይደለም›
የተወለዱበት ቀን በሚለው ላይ በኡለማዎች መሃል ልዩነት አለ፡፡ ለምሳሌ ረቢዑል አወል 12, 9 እና የመሳሰሉትን) የሞቱበት ቀን ግን በቁርጥ ረቢዑል አወል 12 ነው፡፡

ጥያቄዎች
=====
የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን ፆመዋል፡፡ በልደት ቀናቸው ቢፆሞ ኖሮ ታድያ ለምንድን ነው አመት ጠብቀው ያቺ የተወለዱባትን ቀን ያልፆሙት?????

ይልቁንስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብዙ ሰኞዎችን ፆመዋል፡፡ በሱፍዬች እና በአህባሾች ሎጂክ መሰረት ‹‹በአመት ውስጥ በተለያየ ግዜ ነው የተወለዱት›› ማለት ነው?????
ማጠቃለያ
======
ሰኞ ቀናቶችን የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በመከተል እንፆማለን እንጂ ስሜታችንን ለመከተል ሀዲስ አናጣምም፡፡

መውሊድ ውስጡ ሽርክ ያቀፈ ቢድዓ ነው፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! እንሽሸው፡፡ ከሃቅ ባኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Post a Comment

0 Comments